219089 constitution-independence of the judiciary-human rights-UDHR-ICCPR

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 78 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ላይ ነፃ እና ገለልተኛ የዳኝነት አካል በየደረጃው ማቋቋም ያስፈለገው ሰዎች ነፃና ገለልተኛ በሆነ አካል ፊት ቀርበው መብታቸውን በማስከበር ዳኝነታዊ መፍትሄ ማግኘት እንዲችሉ፣ በህግ ፊት እኩል ጥበቃ እና ፍትህ የማግኘት መብታቸውን ለማስከበር እንዲሁም ሌሎች የሰዎችን ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ለማስከበር በመሆኑ የክልል ፍርድ ቤቶች በህግ በታወቀ ምክንያት በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸውን የውክልና ሥልጣን መጠቀምና ለዜጎች ፍትህ መስጠት በማይችሉበት ሁኔታ ላይ ሲሆኑ እና ጉዳዩም የፌደራል ጉዳይ ሲሆን የሰዎችን ፍትህ የማግኘት መብት፣ እኩል የሕግ ጥበቃ የማግኘት መብት እና ሌሎች መብቶችን ለማስከበር የፌደራል ፍርድ ቤቶች በቀጥታ ጉዳዩን ተቀብለው የመዳኘት ሥልጣን የሚኖራቸው ስለመሆኑ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 25፣ 37/1፣ እና አንቀጽ 78 እና ተከታዮቹ፤ የተባበሩት መንግስታት የሰበዓዊ መብቶች መግለጫ (Universal Declaration of Human Rights) አንቀጽ 7፣8 እና 10 እንዲሁም የዓለም አቀፍ የሲቪልና ፓለቲካ መብቶች ቃልኪዳን (International Covenant on Civil and Political Rights/ICCPR) አንቀጽ 2(3/ሀ እና ለ)፣ 26  

Download