እግድ እንዲሰጥ የተጠየቀው ክስ ሳይቀርብ ከሆነ ተከሳሽ የሚሆነው ወገን ላይ ያልተገባ የመብት ገደብ እንዳይደረግበት፤ ጊዜያዊ እግድ የሚጠይቀው ወገን ክስ ለማቅረብ ዝግጅት ላይ እንዳለና የክስ ዝግጅቱ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈለገበትን ምክንያት፣ ክሱ እስኪቀርብ ድረስ የእግድ ትዕዛዙ ባይሰጥ የሚያስከትለው ጉዳት ማሳየት ያለበት ሲሆን ፍርድ ቤቱም ክሱን ለማቅረብ የሚያስፈልገውን ምክንያታዊ ጊዜ ድረስ ብቻ በጊዜ ገደብ የተገደበ የእግድ ትዕዛዝ ሊሰጥ የሚችል ስለመሆኑ 

የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 154(ለ) 
የእግድ ትእዛዝ እንዲሰጥ የተጠየቀው ያለ ቅድመ ሁኔታ የሚከፈል የዋስትና ክፍያ ላይ ከሆነ፣ የገንዘብ ግዴታ/ዋስትና ሠነድ የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 648/2001 አንቀጽ 2(20)ን ጨምሮ በተለያዩ ሕጎች የፋይናንስ ቃል ኪዳን ወይም የፋይናንስ ግዴታን ለመፈጸም የሚሰጥ ወይም የሚያዝ ማንኛውም ሠነድ ሲሆን የግምጃ ቤት ሠነድን፣ የተስፋ ሠነድን እና ቦንድን ይጨምራል ተብሎ ትርጉም የተሰጠበትና፤ ዋስትናው የተሠጠው ያለ ቅድመ ሁኔታና የሚፈጸመውም ያለ ቅድመ ሁኔታ በመሆኑ፤ በዚህ ላይ የሚቀርብ ክስ የሚታገድ ከሆነ የውሉን ባሕሪ የሚቀይረው፣ ህግንና ተዋዋዮች ያሰቡትን ዓላማ ማሳካት የማይቻል ስለመሆኑ  
ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመክፈል የተገባን የዋስትና ግዴታ እንዳይከፈል እግድ ማቅረብ ህጋዊነት የሌለው ስለመሆኑ 

Download