- Hits: 2666
80343 labor dispute/ occupational accident/ extra contractual liability/ civil procedure/ res judicata
አንድ ሠራተኛ በሥራ ላይ እያለ የደረሰበትን የአካል ጉዳት በተመለከተ የጉዳት ካሣ ክፍያ እንዲከፈለው ለመጠየቅ የሚችለው በአማራጭ አንድም በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጁ መሠረት አሰሪውን ያለጥፋት በሥራ ክርክር ችሎት ከሶ በመጠየቅ ወይም የአሰሪውን ጥፋት መነሻ በማድረግ የጉዳት ካሣ ክፍያ ከውል ውጪ ኃላፊነትን የተመለከቱ ድንጋጌዎችን መሠረት በማድረግ በፍ/ሔር ችሎት በአሠሪው ላይ ክስ ለማቅረብ የሚችል ስለመሆኑ፣ በሥራ ላይ ጉዳት የደረሰበት ሠራተኛ የጉዳት ካሣን ለመጠየቅ በህጉ የተመለከቱትን መብቶች በአግባቡና በትክክል ተገንዝቦ እንደ ጉዳቱ ሁኔታ፣ አይነትና አግባብነት በተሻለ ሁኔታ የሚጠቅመውን የመብት አድማስ አውቆ በመለየት ተገቢው መብቱ ከመነጨበት የህግ አግባብ አንፃር ክሱን ሊያቀርብ የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.5 ድንጋጌ ይዘት አድማሱ በግልጽ በተወሰኑ ጭብጦች ላይ ብቻ ሣይሆን በተከራካሪ ወገኖች ቢነሱ ኖሮ ሊወሰኑ ይችሉ የነበሩ ጭብጦችን ጭምር የሚያካትት ስለመሆኑ፣