- Hits: 2215
88867 civil procedure/ execution of judgment/ priority of creditors
በአንድ የፍርድ ባለእዳ ንብረት ላይ ፍርድ እንዲፈፀምላቸው የሚጠይቁ የፍርድ ባለገንዘቦች ያሉ እንደሆነ አፈፃፀሙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 403 መሠረት ሊስተናገድ የሚገባ እንጂ በሌላ የፍ/ባለመብት ምክንያት በሌላ የአፈፃፀም መዝገብ ላይ የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተነስቶ የአፈፃፀም ጥያቄው ካልቀረበ በስተቀር ሊቀጥል አይችልም ለማለት የማይችል ስለመሆኑ፣ አፈፃፀሙ በሚካሄድበት ወቅት በንብረቱ ላይ የመያዣ ውልን መነሻ በማድረግ የቀዳሚነት መብት አለን የሚሉ ወገኖች ያሉ እንደሆነም ጥያቄው በቀረበ ጊዜ እንደየአግባብነቱ ታይቶ ሊወሰን የሚገባው ስለመሆኑ፣ አፈፃፀሙን የያዘው ፍ/ቤት በንብረቱ ባለቤት ላይ የገንዘብ ክፍያ ፍርድ አሰጥተው እና ገንዘቡም እንዲከፈላቸው ጥያቄ ያቀረቡ የፍርድ ባለገንዘቦችን አስቀርቦ ጥያቄያቸውን በመመርመር ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 403 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ አኳያ አገናዝቦ በመመልከት አፈፃፀሙ ሊመራ የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 403, 378