criminal law

  • ከአንድ የወንጀል ድርጊት ጋር በተያያዘ ንብረት የሚወረሰዉ ወይም ለመንግስት ገቢ የሚደረገዉ በወንጀል ህጉ እና በወንጀል ስ/ስ/ህጉ መሠረት በቅጣት መልክ በመሆኑ ንብረቱ የሚወረስ መሆን አለመሆኑ ዉሳኔ ማግኘት ያለበት በወንጀል መዝገብ እንጂ በወንጀል መዝገብ ላይ የተሰጠን ውሳኔ ብቻ መነሻ በማድረግ በአዲስ መልክ በሚቀርብ የፍትሐብሔር ክርክር ስላለመሆኑ የወንጀል ህግ አንቀጽ 98፤100(1) እና 140 

    Download

  • አንድ የባንክ ሠራተኛ በሥራው አጋጣሚ ያገኘውን የደንበኛ ገንዘብ ከህግ ውጭ ቀንሶ በማስተላለፍና በማውጣት መውሰዱ በተረጋገጠበት ሁኔታ ሰራተኛው የወሰደውን ገንዘብ ዋሶቹ ከእርሱ ጋር በአንድነትና በነጠላ ገንዘቡን የመክፈል ኃላፊነት ያለባቸው ስለመሆኑ
    የፍ/ሕ/ቁ 1920፣1922 እና 1933

    Download here

  • በአንድ ውል ምክንያት ለደረሰ የጉዳት ኪሣራ ምክንያት ግራቀኙ ተዋዋይ ወገኖች መሆናቸው ከተረጋገጠ ለደረሰው የጉዳት ኪሣራ ሁለቱም ሃላፊነቱን መሸከም ያለባቸው ስለመሆኑ
    ከፍ/ብ/ህ/ቁ. 1799(1) ፣1802 (1)፣2090፣2091 

    Download this

  • አንድ ቼክ በሚወጣበት ጊዜ በቼክ አውጭው ሂሣብ ቁጥር በቂ ስንቅ አለመኖሩ እየታወቀ ቼክ የተሰጠ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ከግል ተበዳዩ ጋር የቤተሰባዊ ግንኙነት ያላቸው ስለሆነና ቼኩን የሰጠው በመተማመኛ መልኩ ነው በማለት ድርጊቱ በቸልተኝነት የተፈፀመ ነው  በሚል በወንጀል ህግ ዓንቀፅ 693(1) መሰረት የቀረበ ክስ ወደ ወንጀል ህግ አንቀፅ 693(2) በመቀየር ተከሳሹን ጥፋተኛ ማለት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 23፤59 ድንጋጌ ያላገናዘበ ስለመሆኑ 

    Download here

     

  • “በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 27 መሰረት አግባብ ያለው አካል በሕገወጥ መንገድ የተያዘን የከተማ ቦታን የማስለቀቂያ ትዕዛዝ መስጠት እና ካሣ መክፈል ሳያስፈልግ የሠባት የሥራ ቀናት የጽሑፍ ማሥጠንቀቂያ ብቻ ለባለይዞታው በአካል በመስጠት ወይም በቦታው በሰፈረው ንብረት ላይ በመለጠፍ የማስለቀቅ ሥልጣን ይኖረዋል” በማለት የተቀመጠው ሀሳብ በሕጋዊ መንገድ ለተያዙ የከተማ ቦታዎችን ለማስለቀቅ የተቀመጠውን የማስለቀቂያ ትዕዛዝ የመስጠት እና ካሣ የመክፈል ሥርዓት ማሟላት ሳያስፈልግ በሕገወጥ መንገድ የተያዘን የከተማ ቦታን ማስለቀቅ የሚቻልበትን ሥርዓት የሚደነግግ እንጂ የከተማ ቦታን ወሮ ለያዘ ሰው የወንጀል ሀላፊነትን የሚያስቀር ስላለመሆኑ
    አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 26(4)፣27 

    Download here

  • በወንጀል ጉዳይ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ አዲስ የወጣ ህግ ተከሳሹን የሚጠቅም በሆነ ጊዜ ተከሳሹ አዲሱ ህግ ተፈፃሚ እንዲሆን አቤቱታ ባቀረበ ጊዜ አዲስ የወጣው ህግ ተፈፃሚ እንዲሆን መደረግ ያለበት ስለመሆኑና በዚሁ ጉዳይ አቤቱታ የቀረበበት ጉዳይ በባህሪው እንደመደበኛ የክርክር ጉዳይ የሚታይ ሳይሆን በቀረበ ጊዜ ሊስተናገድ የሚችል በመሆኑ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የቀረበ አቤቱታ ነው በማለት ተቀባይነት የለውም የማይባል ስለመሆኑ 

    የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 22(2)፣ የወ/ሕ/አንቀጽ 6 እና 9(1)፤ ዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት አንቀጽ15/1/ 

    Download here

  • የአንድ ቼክ ሕጋዊነት ጥያቄ ባላስነሳበት ፤በዋናነት ደግሞ ቼኩ ተጽፎ እና ተፈርሞ መሰጠቱ ባልተካደበት ሁኔታ እንዲሁም ቼክ እንደቀረበ ክፍያ የሚፈጸምበት ሰነድ ከመሆኑ አንፃር በወንጀል ጉዳይ ያለው ተጠያቂነት ቼክ በወጣበት ወይም ለክፍያ ለቀረበበት ጊዜ በቂ ስንቅ መኖር ያለመኖሩን መሠረት ያደረገ እንጂ ለዋስትና የተሰጠ መሆን ያለመሆን በወንጀል ጉዳይ እንደ ሕጋዊ መከላከያ የሚወሰድ ስላለመሆኑ
    የወንጀል ሕግ አንቀጽ 693(1) 

    Download here

  • አንድ ምስክር በፖሊስ በወንጀል ምርመራ ወቅት የሚሰጠዉ ቃል እንደመደበኛዉ የዳኝነት አካል ወይም የዳኝነት ነክነትወይም መሰል /quasi-judicial/ ተቋም ቃለ መሃላ ፈጽሞ የሚሰጥ የምስክርነት ቃል ባለመሆኑ ምስክሩ በፖሊስ የምርመራ መዝገብ የሰጠው የምስክርነት ቃል ፍ/ቤት ቀርቦ በመለወጡ ምክንያት የሀሰት ቃል የትኛዉ እንደሆነ በትክክል በሌላ ማስረጃ ሳይረጋገጥ የምስክሩ ቃል መለያየት ብቻዉን በቂ ማስረጃ በማድረግ ምስክሩ በሀሰተኛ የምስክርነት ቃል መስጠት ወንጀል የሚጠየቅበት የህግ መሰረት ስላለመኖሩ
    የወንጀል ህግ አንቀጽ 453/2/

    Download here

  • የማይንቀሳቀስ ንብረት ካለዉ ልዩ ባህርይ አንፃር ንብረቱን ከአንድ ወደ ሌላ ሰዉ በሽያጭ ለማስተላለፍ  የሚደረግ ዉል በሦስተኛ ወገን ላይ ህጋዊ ዉጤት ያስከትል ዘንድ ዉሉ በህግ አግባብ በሚመለከተዉ አካል ዘንድ ካልተመዘገበ ውሉ ፈራሽ የሚሆን ሲሆን ሻጩም በዉሉ ምክንያት የተቀበለዉን ገንዘብ የመመለስ ግዴታ ያለበት ሲሆን፣ ይህን እንዲያደርግ ሌላ ክስ ማቅረብ ሳያስፈልግ በዚያው መዝገብ ላይ መወሰን የሚቻል ስለመሆኑ
    በፍ/ሕ/ቁ አንቀጽ 2878 

    Download here

  • አንድ ተከሳሽ በአንድ ቸልተኝነትና በአንድ ድርጊት በደረሱ ጉዳቶች በተደራራቢ ወንጀሎች ሲከሰስ ሌላ የተለየ ሀሳብና ድርጊት መኖሩ እስካልተረጋገጠ ድረስ አንዱን በቸልተኝነት ሌላዉን ደግሞ ሆን ተብሎ ታስቦ በተፈጸመ ወንጀል ጥፋተኛ የሚደረግበት አግባብ እና ቅጣትን በሚመለከት ተደራራቢ ወንጀሎች ተፈጽመዉ ሲገኙ ቅጣት ሊወሰን የሚገባዉ ለእያንዳንዱ ወንጀል መነሻ ቅጣት ከተያዘ በኃላ እነዚህን በመደመር ድምሩ የቅጣት መጠን የሚያርፍበትን ዝቅተኛ የቅጣት እርከን በመለየት ስለመሆኑ  የተሻሻለዉ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 አንቀጽ 22(1/ሀ)  

    Download here

  • በአንድ የወንጀል ክስ ማመልከቻ ላይ ተጠቅሶ የቀረበ ድንጋጌና የክሱ ፍሬነገር ዝርዝር ላይ በስህተት የተጠቀሰ ወይም ሳይጠቀስ የታለፈ መሠረታዊ ነገር መኖሩ ሳይረጋገጥ ከወዲሁ አንቀጽ ካልተለወጠ በሚል ምክንያት ክስ እንዲሻሻል ትእዛዝ መስጠትና ይህ ካልተፈጸመ በሚል የክሱን መዝገብ መዝጋቱ ክስ እንዲሻሻል የሚደረግብትን ህጋዊ አላማ ያላገናዘበ ስለመሆኑ 

    አንድ ተከሳሽ ላይ የቀረበ ክስ ሁለት ሆኖ 1ኛዉ ክስ ቀደም ሲል ፍርድ ቤት በሰጠው ትእዛዝ መሰረት ተሻሽሎ ባለመቅረቡ የሚዘጋ ቢሆን ሁለተኛዉ ክስ ላይ ያለምንም ህጋዊ ምክንያት ዉሳኔ ሳይሰጥ ማለፍ ሥነ-ሥርዓታዊ ስላለመሆኑ
    በወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁ/112፣113/2/፣119

    Download here

  • አንድ የአሽከርካሪነት ሙያ ያለዉ ሰዉ የትራፊክ ደህንነት ደንብን ተላልፎ በተሽከርካሪዉ የኋላ የዉጭ አካል ላይ ሰው አሳፍሮ ሲያሽከረክር ተሳፋሪው ለመዉረድ ሲል መዉደቁ ወይም ለመዉረድ ሲል ዘሎ በመዉደቁ ለደረሰበት ጉዳት አሽከርካሪውን በቸልተኝነት ተጠያቂ ከመሆን የማያስቀረው ስለመሆኑ
    የወ/ሕ/አንቀጽ 24፣ 59፣543(3)፣ በትራፊክ ደህንነት ደንብ ቁጥር 208/2003 አንቀጽ 36(1)

    Download here

  • የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ ለይግባኝ ማቅረቢያና ተያያዥ ጉዳዮች የጊዜ ገደብ ቢያስቀምጥም በመታየት ላይ ያለ መዝገብ መዘጋቱ አስፈላጊ ሆኖ ከተዘጋ በኃላ እንደገና መከፈቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በምን ያህል ጊዜ ዉስጥ አቤቱታ ሊቀርብበት እንደሚገባ በግልፅ ስላላስቀመጠ የጊዜ ገደቡ የሚወሰነው  የጉዳዩን ሁኔታዎችና የአቤቱታዉን ዓይነት በመመልከት እንጂ መዝገቡን ለማንቀሳቀስ የቀረበዉ አቤቱታ ከተወሰነ ጊዜ በኃላ የቀረበ ነው በማለት አቤቱታውን ውድቅ ማድረግ የይግባኝ ባዩን መብት የሚጣብብ ስለመሆኑ በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 22(2)፤በወ/ሕ/አንቀጽ 6፣ 9(1) 

    Download here

  • የዳኝነት ስራ አካሄድ ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች በተለይም አንድ ችሎት በያዘዉ መዝገብ ላይ ችሎት መድፈርን በተመለከተ ወዲያዉኑ ቅጣት ሊወስን ስለሚችልበት አግባብ የወንጀል ህጉ አንቀጽ 449 ፣ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ/480 እና 481 

    Download here

     

  • በወንጀል ህግ አንቀጽ 693(1) መሰረት የሚያዝበት በቂ ገንዘብ ሳይኖር ቼክ ማውጣት ወንጀል የተከሰሰ ቼክ አውጪ ቼኩን ለመመንዘር ሳይሆን በግለሰቦች መካከል በነበረው የንግድ ግንኙነት መነሻነት ለመተማመኛ የሰጠ በመሆኑ ከወንጀል ኃላፊነት ነፃ ሊወጣ የሚችለው ቼኩን ለዋስትና ወይም ለመያዥያነት የሰጠ ለመሆኑ እና የዋስትና ወይም የመያዥያ ውሉም በንግድ ህግ እና በፍትሐ ብሔር ህግ በተመለከተው መመዘኛ መሰረት ስለመፈፀሙ በማስረዳት ከመሆኑ በቀር በሰው ምስክር የሚሰጥ ማረጋገጫ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ  
    የንግድ ህግ አንቀፅ 952 እና የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 2864-2866   
    (በፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሰረት 
    በፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀደም ሲል በሰ/መ/ቁ. 67947 ተሰጥቶ የነበረው የህግ ትርጉም ተሻሽሏል)

    Download

  • አንድ ተከሳሽ አስቀድሞ በፈጸመዉ ወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ በአመክሮ ከተፈታ አምስት ዓመት ያለፈዉ ቢሆንም ለፍ/ቤት የመሰየም ጥያቄ አቅርቦ ባልተሰየመበትና ቅጣቱም ከፍርድ መዝገብ ተሰርዞ እንዳልተሰጠ ባልተቆጠረበት ሁኔታ የጥፋተኝነቱ ሪከርዱን በቅጣት ማክበጃነት መያዝ ተገቢ ስለመሆኑ
    በወ/ሕ/አንቀጽ 82(1/ሀ) ፣84(1/ሐ)፣ 232፣ 233

    Download

  • የወንጀል ሕግ አንቀጽ 23/2 ድንጋጌ እና የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 መሰረት ዓቃቤ ሕግ መደበኛውን የወንጀል ሕግ ወይም ወንጀል መፈጸሙን ለማስረዳት ልዩ መስፈርትን የማያስቀምጡ ልዩ ሕጎችን መሠረት በማድረግ ክስ ሲያቀርብ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 23/2 መሠረት የአንድ ተከሳሽን የሀሳብ ክፍል እንዲያረጋግጥ የተጣለበት የማስረዳት ሸክም ለሙስና ወንጀሎች በተመሳሳይ ተፈጻሚ የማይሆን ስለመሆኑ እና በሙስና ወንጀሎች አዋጅ በተደነገገው መሠረት ግዙፋዊ ፍሬነገር መፈጸሙ በተረጋገጠ ጊዜ ተከሳሹ በድንጋጌው የተመለከተውን ግዙፋዊ ፍሬነገር ለመፈጸም የነበረውን የሀሳብ ክፍል ተቃራኒ ማስረጃ በማቅረብ እንዲያስተባብል የማስረዳት ሸክሙ ወደ ተከሳሹ የሚዛወር ስለመሆኑ 

    የወንጀል ህግ አንቀጽ 23/2/፣የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007አንቀጽ 3 ፣አንቀጽ 13/3 እና 13/1/ሐ 

    Download

  • በአንድ ውል ላይ የገደብ (የመቀጫ)ስምምነት በተደረገ ጊዜ ባለገንዘቡ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር ውሉ እንዲፈፀም እንዲሁም የመቀጮ ገንዘብ እንዲከፈል ለመጠየቅ የሚችል ሲሆን ነገር ግን መቀጮ የሚከፈለው የውሉ መዘግየት ወይም ተጨማሪ ግዴታዎች ካሉ የእነሱ አለመፈፀም የመቀጮውን ክፍያ የሚያስከትል ሲሆን ስለመሆኑ
    ፍ/ብ/ህ/ቁ 1890(1)(2) 

    Download here

  • አንድን ዕቃ ከውጪ የሚያስመጣ ሰው ለጉምሩክ ሥርዓት አፈጻጸም ሲባል ስለሚያስመጣው ዕቃ አስፈላጊ የሆኑ መግለጫዎችን በመስጠት በዲክላራሲዮን ላይ በማስመዝገብ ወደ ሐገር ውስጥ የሚገቡ ዕቃዎች በላኪው እና በአስመጪው መካከል በሚደረግ ስምምነት ወደ ሐገር ውስጥ የሚገቡ ከመሆናቸው አኳያ ወደ ሐገር ውስጥ እንዲገባ የተደረገው ዕቃ አስመጪው በዲክላራሲዮን ካስመዘገበው ዕቃ የበለጠ ዋጋ ያለው ሆኖ በተገኘ ጊዜ አስመጪው የተላከውን ዕቃ ሊያውቅ የሚችልበት ሁኔታ የለም ተብሎ ከወንጀል ተጠያቂነት ነፃ ሊደረግ የማይገባ ስለመሆኑ
    የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06 አንቀጽ 13/4/፣169/2/

    Download

  • በወንጀል ሕግ አንቀጽ 539/1/ሀ መሰረት በሰው መግደል ወንጀል በተመሰረተ ክስ ላይ የግል ተበዳይ ህይወት በጠፋበት እና ወንጀሉ የአካል ጉዳት ማድረስ ስለመሆኑ በማስረጃ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የተከሳሾች የሀሳብ ክፍል ከባድ የአካል ጉዳት ለማድረስ ነው በሚል የክሱን የህግ ድንጋጌ ወደ አንቀጽ 556/2/ሀ ዝቅ በማድረግ የሚሰጥ የቅጣት ውሳኔ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ 

    Download