criminal law

  • ዓቃቤ ሕግ የሚያቀርበው የክስ አቤቱታ በወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ መሠረት ያልቀረበ ሆኖ ሲገኝ ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት በራሱ አነሳሽነት ክሱ በህጉ አግባብ ተሻሽሎ እንዲቀርብ ማድረግ ያለበት ስለመሆኑ እና ዓቃቤ ሕግ ክሱን አሻሽሎ እንዲቀርብ ሳይደረግ በሕጉ አግባብ ተዘጋጅቶ ያልቀረበው ክስ የተከሳሹን የመከላከል መብት የሚያጣብብ በመሆኑ ተከሳሹ በሕግ አግባብ ተዘጋጅቶ ባልቀረበው ክስ ጥፋተኛ ሊባል የማይገባ ስለመሆኑ
    በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ ቁጥር 118 እና 119/1/

    Download

  • አንድ ሰው ለብዝበዛ ዓላማ ሲባል በሕገ-ወጥ መንገድ ሰዎችን የማዘዋወር ወንጀል ፈፅመኻል ሊባል ስለሚችልበት አግባብ
    ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ስደተኞችን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 909/07 አንቀጽ 3/2/ሀ/

    Download

  • አንድ ተከሳሽ ማንኛውም የንግድ ዕቃን ከመደበኛው የግብይት አሰራር ውጭ በማናቸውም ማጓጓዣ ከተፈቀደ የስርጭት መስመር ውጭ ሲያጓጉዝ  የተያዘ ስለመሆኑ ሳይረጋገጥበት፤ዕቃውም የተፈቀደ የስርጭት መስመር ያለው መሆን አለመሆኑና ከመስመር ውጪ ሲጓጓዝ የነበረ መሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ በወንጀል ጥፋተኛ ሊባል የማይገባው ስለመሆኑ የነጋዴዎች እና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀጽ 24/3/ እና 43/4/ 

    Download

  • አንድ ከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ፈፅመሃል ተብሎ የተከሰሰ ተከሳሽ ድርጊቱን ለመፈጸም የተጠቀመበት መሳሪያ የሌለ መሆኑ በማስረጃዎች በተረጋገጠበት ሁኔታ በከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ጥፋተኛ ሊባል የማይገባ ስለመሆኑ
    የወንጀል ህግ አንቀፅ 555 ፣556(1)

    Download

     

  • በአንድ የወንጀል ጉዳይ ተከሳሽ የሆነ ሰው የቀድሞ የጥፋተኝነት ሪኮርድ ያልቀረበበት፣ ጥፋቱን አምኖ የተፀፀተና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኑ ሲታይ ቅጣትን በገደብ ለማቆም የተመለከቱትን ቅድመ ሁኔታዎች በአብዛኛው ያሟላ ቢሆንም የስር ፍ/ቤት የቅጣቱ መገደብ ላይ ባለማመኑ የቀረበለትን የገደብ ጥያቄ ውድቅ ሲያደርግ ቅጣቱ እንዳይገደብ የሚያደርጉ ምክንያቶችን ባለመግለፁ ብቻ ጉዳዩ ወደ ስር ፍ/ቤት መመለስ አስፈላጊ ስላለመሆኑ

    Download

  • ቅጣት ሊገደብ የሚችለው ጥፋተኛ የተባለን ሰው ለጥፋቱ መነሻ የሆኑትን ምክንያቶችን በጠቅላላው በመመልከት፤ የወንጀሉ ከባድነት/ the gravity of the crime/ በማየት፤ በጥፋተኛው ላይ የተወሰነውን ቅጣት ለጊዜው በገደብ እንዲታገድ በማድረግ የወንጀለኛውን ጠባይ ለማረምና ለማሻሻል እንዲሁም ወደ መደበኛ ማህበራዊ ኑሮው ለመመለስ ጠቃሚ መሆኑ ሲታመን እና በአጠቃላይ ቅጣት ስለሚገደብባቸው ሁኔታዎች በወንጀል ሕጉ የተቀመጡት መስፈርቶች መሟላታቸው ሲረጋገጥ ስለመሆኑ
    የወንጀል ሕግ አንቀጽ 192፣194፣196/2/ እና 197

    Download

  • አንድ ጉዳት የደረሰበት ሰው ጉዳት አድራሹ በህግ ቁጥጥር ሥር ውሎ በዋስ በመፈታቱ ላይ ቅሬታ ቢኖረው በህግ በተቀመጠው ሥነሥርዓት መጠየቅ እንጂ ለምን በዋስ ተፈታ፣እንደገና ጉዳት ያደርስብኛል በሚል ትንበያ፣እንዲሁም ፍትህ ተደክሟል በሚል በራሱ ፍትህን ለማስፈጸም ግድያ በፈፀመበት ሁኔታ የደረሰበት ጉዳት ወንጀል ለመፈጸም ቀስቃሽ ሆኗል በሚል ቅጣትን አቅልሎ መወሰን ተከሳሹን የማያስተምር እና ፍትህን በራሱ መፈጸሙ ምክንያታዊ እንደሆነ እንዲሰማው የሚያደርግ ፣ሌላውን ማኅበረሰብ ፍትህን በራሱ እንዲያስፈጽም የሚገፋፋ ወይም መጥፎ አርአያ የሚሆን፣ዋነኛው የወንጀል ህግ ዓላማ የሆነውን የህዝብን ሠላምና ደኅነት የማስጠበቅ ዓላማ እንዳይሳካ የሚያደርግ ስለመሆኑ  

    Download

  • አንድ ተከሳሽ በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎለት ክስ የቀረበበት ስለመሆኑ አውቋል የሚል ግምት ሊወሰድ የሚገባው ሐገር አቀፍ ስርጭት ባለው ጋዜጣ ጥሪ የተደረገለት መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ እንጂ በአንድ ክልል ብቻ ተደራሽ በሆነ ጋዜጣ ብቻ ጥሪ መደረጉን መጥሪያ እንደደረሰው ማረጋገጫ አድርጎ በመውሰድ እና መጥሪያ ደርሶታል የሚል ግምት በመውሰድ ጉዳዩን ተከሳሹ በሌለበት አይቶ ውሳኔ መስጠት በሕገ-መንግስቱ ለተከሰሱ ሰዎች የተጠበቁላቸውን መሠረታዊ መብት የሚነካ ስለመሆኑ
    የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 161፣199(ሀ)

    Download

  • አንድ ሰው በፈጸመው ወንጀል ምክንያት በማረሚያ ቤት በመሆኑ በሕፃናት ልጆቹ ላይ የሚደርሰውን ቁሳዊም ሆነ ኅሊናዊ ጫና ለማስቀረት ሲባል እንዲሁም ሕጻናቱ የወላጆቻቸውን እንክብካቤ እና ድጋፍ አግኝተው እንዲያድጉ ለማድረግ ሲባል፤ ፍ/ቤቶችም የሕጻናት ደኅንነት በቅድሚያ የማረጋገጥ ሕገመንግስታዊ ግዴታ ያለባቸው በመሆኑ በወንጀለኛው ላይ የተወሰነውን ቅጣት በመገደብ ህፃናቱ ተገቢውን የወላጅ እንክብካቤ እንዲያገኙ ለማድረግ ያስችል ዘንድ በወንጀል ህጉ ቅጣት ለማገድ የተቀመጡትን ሁኔታዎች በማረጋገጥ የተወሰነውን ቅጣት እንዳይፈጸም ማገድ የሚገባ ስለመሆኑ
    የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገመንግሥት አንቀጽ 36/2፤የወንጀል ህግ አንቀጽ 192፣194፤የዓለም አቀፉ የህፃናት መብቶ፤ች ስምምነት የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ቁጥር 44/25 እንደ ኤሮፓውያን አቆጣጠር 1989 የወጣው አንቀጽ 7 (1)፤ የህፃናት መብቶች ኮንቬንሽን አንቀጽ 18

    Download

  • በቸልተኝነት የሚፈፀሙ ድርጊቶች እንደ ሙከራ ሊቆጠሩ ይችላሉ የሚል አስተያየት ቢኖርም አንድን የወንጀል ድርጊት ሙከራ ነው ለማለት ድርጊቱ በእውቀትና በፍላጎት የተፈፀመ መሆኑን ማረጋገጥ መሰረታዊ መስፈርት ስለሆነ በቸልተኝነት የሚፈፀሙ ድርጊቶችን እንደ ሙከራ መቁጠር በአሁኑ ጊዜ ብዙም ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ የወንጀል ህግ አንቀፅ 27(1)፣ 23(2) እና 58(1) (ለ) 

     

    Download

  • ከተገኘ ገቢ የሚከፈል ግብርንና የተሰበሰበን ተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ ደረሰኞች ሐሰተኛ መሆናቸው ብቻ አንድን ተከሳሽ ጥፋተኛ ሊያስብለው የማይችልና ሐሰተኛ ደረሰኝ ናቸው የተባሉት ደረሰኞች አፈጣጠርና ለገቢ ሰብሣቢው መስሪያቤት አቀራረብ ሂደት ላይ የተከሳሹን ድርሻና በሕግ የተጣለበት ግዴታ ከወንጀል ህግ መሰረታዊ መርህና የወንጀል ማስረጃ ምዘና መርህን በተከተለ መንገድ ሊመረመር የሚገባው ስለመሆኑ
    ከወንጀል ሕግ አንቀፅ 23(1) ፤የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር
    285/94 አንቀፅ 22፣49፣50 (1) 

    Download

  • በሙስና ወንጀሎች አዋጅ መሰረት በተመሰረት ክስ ተከሳሹ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ ይህ ብይን የተሰጠበት ድንጋጌ አማራጭ ቅጣትን ያስቀመጠ ሆኖ በተሻሻለው የፀረ-ሙስና ልዩ የስነ ስርአትና የማስረጃ ህግ (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3/1 ሁለተኛ ሀሳብ ላይ ከአራት አመት በላይ በሚል የተደነገገውን ቅጣት እንደ መነሻ ቅጣት በመውሰድ የቅጣት መነሻቸው አራት ዓመት የሆነ በጽኑ እሥራት የሚያስቀጡ ወንጀሎችን የሚመለከት እንደሆነ አድርጎ በመውሰድ ዋስትናን መፍቀድ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ 

    የተሻሻለው የጸረ-ሙስና ልዩ የሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 4/1/ 

    ተከሳሹ በፈፀመው የወንጀል ድርጊት ምክንያት የደረሰው የጉዳት መጠንን በተመለከተ አቃቤ ህግ ክስ በመሰረተበት የህግ አንቀጽ በተከሳሹ የወንጀል ድርጊት ምክንያት የደረሰውን የጉዳት መጠን አለመግለጹ ተከሳሽ በዋስትና ቢለቀቅ ዋስትናውን አክብሮ ሊቀርብ አይችልም የሚል ግምት በመውሰድ የዋስትና መብትን የማያስከለክል ስለመሆኑ

    የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67 

    Download

  • የቅጣት ውሳኔ እንዳይገደብ በወንጀል ህግ አንቀፅ 194 ስር የተቀመጠው ክልከላ ባልተሟላበት ሁኔታ ተከሳሽ ክሱን ክዶ ከመከራከሩም በላይ ከተበዳይ ጋር ታርቆ ለመካስ እና የፍርድ ቤትን ወጪ ለመሸፈን የሰጠው ማረጋገጫ የለም በሚል በመልካም ጠባይ የሚመራ ለመሆኑ በፍርድ ቤት እንዲያቀርብ የሚጠየቅ የዋስትና ማረጋገጫ ትዕዛዝ ቅጣትን ለመገደብ ቅድመ ሁኔታ ተደርጎ የሚወሰድ ስላለመሆኑ 

    በተደጋጋሚ ወንጅል ፈጽሞ የተቀጣ ተከሳሽ አዲስ ወንጀል ፈጽሞ በተገኘ ጊዜ ፍርድ ቤት ቅጣቱን ለማክበድ በወንጀል ሕግ ልዩ ክፍል ከተደነገገው ጣራ ቅጣት በማለፍ የዚህን መጠን እጥፍ በመያዝ መወሰን የሚችል ቢሆንም ይህ የሚቻለው ወንጀሉ የተደጋገመ መሆኑን ብቻ በማየት ሳይሆን ጥፋተኛው የፈጸማቸው ወንጀሎች ዓይነት፣ ክብደት እና ብዛት እንዲሁም ወንጀል ለመፈጸም የነበረው የአደገኝነት መጠን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ስለመሆኑ 
    የወንጀል ሕግ አንቀጽ 188 (1) እና (2)፣ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 አንቀጽ 22/2 

    Download

  • በተደጋጋሚ ወንጅል ፈጽሞ የተቀጣ ተከሳሽ አዲስ ወንጀል ፈጽሞ በተገኘ ጊዜ ፍርድ ቤት ቅጣቱን ለማክበድ በወንጀል ሕግ ልዩ ክፍል ከተደነገገው ጣራ ቅጣት በማለፍ የዚህን መጠን እጥፍ በመያዝ መወሰን የሚችል ቢሆንም ይህ የሚቻለው ወንጀሉ የተደጋገመ መሆኑን ብቻ በማየት ሳይሆን ጥፋተኛው የፈጸማቸው ወንጀሎች ዓይነት፣ ክብደት እና ብዛት እንዲሁም ወንጀል ለመፈጸም የነበረው የአደገኝነት መጠን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ስለመሆኑ 
    የወንጀል ሕግ አንቀጽ 188 (1) እና (2)፣ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 አንቀጽ 22/2 

    Download

     

  • በወንጀል ህግ አንቀጽ 670፣ 672ና 240፣ የተደነገጉት ውንብድና፣ ዘረፋ እና ሽፍታነት የሚሉት ቃላት ቴክኒካዊ ልዩነት በመካከላቸው ያለና በተናጠል የወንጀል ኃላፊነትን የሚያስከትሉ በመሆኑ የአንድ ተከሳሽ የወንጀል ድርጊት “ውንብድና ነው” ወይም “ዘረፋ ነው” ወይም 
    “ሽፍታነት ነው” ለማለት ከመነሻው አጠቃላይ የተፈፀመው ድርጊት እና የተከሳሹ ተሳትፎ በተገቢው መንገድ ተለይቶ ሊታወቅ እና ሊረጋገጥ፤ በእምነት ቃል መሰረት ውሳኔ ለመስጠትም የተሰጠው ቃል ተከሳሹ ከተከሰሰበት ወንጀል ዝርዝር ጋር አንድ ሊሆን፤ ዝርዝር ቃሉም ተከሳሹ ወንጀሉን ለመፈፀሙ የማያጠራጥርና ሙሉ እምነት ሊጣልበት የሚገባ  ስለመሆኑ 
    የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀፅ 20፣ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 134 (1) እና 141  

    Download

  • በወንጀል ህግ የሃሳብ ክፍል የሚረጋገጠው ከወንጀል ድርጊት አፈፃፀሙ በመነሳት ስለመሆኑ የወ/መ/ህ/ቁ. 522 /1/ /ሀ/

    Cassation Decision no. 22069

  • በወ/መ/ህ/ቁ. 522/1/ /ሀ/ ሥር የተመለከቱት የወንጀል ማቋቋሚያ ነጥቦች ለየራሳቸው የሚቆሙ ስለመሆናቸው የወ/መ/ህ/ቁ. 522/1/ /ሀ/

    Cassation Decision no. 22452

  • የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ሳይፈፀምበት የመንግስት ቀረጥ ያልተከፈለበት መኪና ይዞ የተገኘ ግለሰብ በወንጀል ተከስሶ ጥፋተኛ ያልተባለ ቢሆንም ግለሰቡ ተገቢውን ቀረጥ ከፍሎ መኪናውን መረከብ አልያም ደግሞ መኪናው መወረስ ያለበት ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 60/89 አንቀጽ 74 አዋጅ ቁ. 388/95 አንቀጽ 80/3/

    Cassation Decision no. 23855