divorce

  • በጋብቻ ተሳስረው የነበሩ ሰዎች ግንኙነታቸው እስካልተቋረጠ ድረስ ለረጅም ጊዜ ተለያይተው በመኖራቸው ብቻ በመካከላቸው ያለው የትዳር ግንኙነት ፈርሷል ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣

    Download Cassation Decision

  • የጋብቻ ፍቺ ውጤት በስምምነት በሚያልቅበት ወይም በሽማግሌዎች ወይም በባለሞያዎች በሚወሰንበት ጊዜ ውሣኔው ተፈፃሚነት የሚኖረው ለፍ/ቤት ቀርቦ ተቀባይነትን ሲያገኝ ብቻ ስለመሆኑ ፍቺን እና የፍቺን ውጤት በተመለከተ ውሣኔ የመስጠትና የማፅደቅ ስልጣን የፍ/ቤት ብቻ ስለመሆኑ፣ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ.213/92 አንቀፅ 83(3), 117 የኦሮሚያ ብ/ክ/መ/የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ.69/95 እና አዋጅ ቁ.83/96 አንቀፅ 110(5)

    Download Cassation Decision

  • በንብረት ላይ በፍ/ቤት የተሰጠን የእግድ ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 158 መሠረት መልሶ ለማንሳት ስለሚቻልበት አግባብ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 158

    Download Cassation Decision

  • ከባልና ሚስት ጋብቻና ፍቺ ጉዳይ ጋር በተገናኘ የቀረበን ጉዳይ ስልጣን ያለውና ተከራካሪዎቹ ለመዳኘት ፈቃዳቸውን የገለፁለት የሽሪአ ፍ/ቤት ለመዳኘት ፈቃደኛ አለመሆኑን በመግለጽ መዝገቡን የዘጋው እንደሆነ መደበኛ ፍ/ቤት ጉዳዩን ማስተናገድ የሚገባው ስለመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. አንቀጽ 37(1), 34(5), 78(5),

    Download Cassation Decision

  • ፍቺን በስምምነት ለመፈፀም ለፍ/ቤት አቤቱታ ያቀረቡ ባል እና ሚስት የፍቺ ውጤትን በተመለከተ ያደረጉትን ስምምነት ፍ/ቤት ለህግና ለሞራል የማይቃረን መሆኑን በማረጋገጥ ያፀደቀው እንደሆነ ስምምነቱ ተፈፃሚ መደረግ ያለበት ስለመሆኑ፣ የተሻሻለው የፌዴራል የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 80,83(3) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 277(2)

    Download Cassation Decision

  • የኮንዶሚኒየም ቤትን በጋብቻ ወቅት እያሉ የደረሳቸው ባልና ሚስት የቤቱ ቅድመ ክፍያ በጋብቻ ወቅት ከተፈራ የጋራ ሀብት የተከፈለ እንደሆነና ቤቱን ለማሳመርና ለሌሎች ተያያዥ ወጪዎች ከጋራ ሀብቱ ወጪ በማድረግ ጥቅም ላይ በዋለበት ሁኔታ ጋብቻው በፍቺ የፈረሰ እንደሆነ ቤቱ ለተጋቢዎቹ፣ ሊከፋፈል ስለሚችልበት አግባብ፣ እንዲሁም በፍቺ ጊዜ እኩል መብት የሚኖራቸው ስለመሆኑ፣ የኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 35(1)  በህገ መንግስቱ የተረጋገጠላቸውን ቤተሰብ የመመስረት መብት በመጠቀም ጋብቻ የፈፀሙ ወንዶች እና ሴቶች በጋብቻው አፈፃፀም፣ በጋብቻው ዘመን

    Download Cassation Decision

  • በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህጉ ውስጥ የተመለከቱት የይርጋ ድንጋጌዎች የሚታዩበት አግባብ በፍ/ብ/ህጉ በተመለከቱት የይርጋ ጊዜ አቆጣጠር ድንጋጌዎች ስለመሆኑ፣ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 78 መሠረት በሌለሁበት የተሰጠ ፍርድ ይነሳልኝ በሚል ጥያቄ በቀረበ ጊዜ በህጉ የተመለከተው የአንድ ወር ግዜ ገደብ በፍታብሔር ህጉ የይርጋ ጊዜ አቆጣጠር ስሌት መሠረት ሊሰላ የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1848, 1856(2) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 78, 195

    Download Cassation Decision

  • ተጋቢዎች የጋብቻቸውን ፍቺ አስመልክቶ ጉዳዩ በመደበኛው ፍ/ቤት ቀርቦና ክርክር ተካሄዶ ውሣኔ ከተሰጠበት በኋላ በሌላ ጊዜ በተመሳሳይ ጉዳይ ሀይማኖታዊ ስርዓትን በመጠቀም በሸሪአ ፍ/ቤት የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 5(1)(2), 244(2)(ለ), 245(2) አዋጅ ቁጥር 188/92 አንቀጽ 5(4), 6(2) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 34(5)

    Download Cassation Decision

Page 2 of 2