constitution (cassation)

 • አንድ ሠው በአንድ ወንጀል ድርጊት ክስ ቀርቦበት የመጨረሻ የሆነ ውሣኔ ተሰጥቷል በማለት በድጋሚ ልከሰስ አይገባም በሚል የሚያቀርበው ክርክር ከዚህ ቀደም ተጣርቶ ክስ የቀረበበትና የመጨረሻ ውሣኔ የተሰጠበት የወንጀል ድርጊትን በድጋሚ (ለሁለተኛ ጊዜ) ክስ ቀርቦበታል ከተባለው የወንጀል ድርጊት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለመሆኑ ተገናዝቦ ሊታይ የሚገባው ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 2(5), 678, 696(ሐ) እና 378 ህገ መንግስት አንቀጽ 23

  Download Cassation Decision

 • የአንድ እምነት ወይም ሐይማኖት ተከታይ ወይም አማኝ በመሆን በሐይማኖታዊ ተቋሙ ውስጥ የመቃብር ቤት ገንብቻለሁና የቤቱን ግምት ይከፈለኝ በሚል ከሚቀርብ ጥያቄ ጋር በተገናኘ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1179 ድንጋጌ ተፈፃሚ ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1179 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 11,27 (1-3) UDHR-Art. 18 ICCPR.Art. 18(1)

  Download Cassation Decision

 • አንድ ሰው ለሌላ ሰው ለማስተላለፍ የሚችለው በህግ ጥበቃ የሚደረግለትንና ያለውን መብት እንጂ የሌላውን መብት ስላለመሆኑ፣  በህግ ጥበቃ የሚደረግለት መብት ሣይኖር በስሙ የተመዘገበ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት የምስክር ወረቅተ ከያዘ ሰው ንብረቱን በመንደር ውል የገዛ ገዢ ተገቢውን ማጣራት በማድረግና፣ በጥንቃቄ፣ የገዛና የቅን ልቦና ያለው ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣  የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ የተሰጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ደንብና አሰራርን መሠረት ያላደረገ እንዲሁም ከስልጣን ውጪ የተሰጠና በህግ ፊት የማይፀና ስለመሆኑ በማናቸውም ማስረጃ ለማረጋገጥ የተቻለ እንደሆነ በተሰጠው የምስክር ወረቀት የተፈጠረውን የህጉን የህሊና ግምት ማፍረስ የሚቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1195, 1196, 2884, 2882-2884 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 40(1)(2)

  Download Cassation Decision

 • በህብረት ሥራ ማህበራትና በአባሎቻቸው ወይም በቀድሞ አባላቸው ወይም በህብረት ስራ ማህበር አባላት ወይም የቀድሞ አባላትና በማህበሩ አመራር መካከል የሚነሳ ክርክር በመጀመሪያ ደረጃ የሽምግልና ጉባኤው ውሳኔ ሳይሰጥበት ፍርድ ቤቶች ተቀብለው ዳኝነት ለማየትና ለመወሰን የማይችሉ ስለመሆኑ፣የኢ.ፌ.ዲ.ሬ ህገ መንግስት አንቀጽ 37፣ አንቀጽ 79(1) እና አዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 49

  Download Cassation Decision

 • ጥቅምን መሠረት ባላደረገ ሁኔታ ህፃናትን (እድሜው ለአካለ መጠን ያልደረሰ ሰውን) አሳፍሮ በመጓዝ ወቅት በደረሰ አደጋ ምክንያት በህፃናቱ ላይ ጉዳት የደረሰ እንደሆነ የተሽከርካሪው ባለቤትና በወቅቱ በተሽከርካሪው ሲገለገል የነበረ ወይም ሹፌሩ የጉዳት ካሣ የመክፈል ኃላፊነት የሚኖርባቸው ስለመሆኑ፣  የተሽከርካሪ ባለቤት የሆነ ሰው ጥቅም በሌላው ግንኙነት መነሻ በተሽከርካሪው ተሳፍሮ ሲጓዝ በነበረ ሰው ላይ ለሚደርስ የአደጋ ጉዳት ካሣ ለመክፈል የማይገደድ ቢሆንም ጉዳቱ የደረሰው ከፍተኛ ጥንቃቄና እንክብካቤ ሊደረግላቸው በሚገባ ህፃናት ላይ በሆነ ጊዜና ህፃናቱም ጥንቃቄ ባልተሞላበት ሁኔታ በተሽከርካሪው ላይ የተጫኑ (የተሣፈሩ) እንደሆነ የተሽከርካሪው ባለቤት የጉዳት ካሣ የመክፈል ኃላፊነት የሚኖርበት ስለመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 36(2), 15, 25 የህፃናት መብቶች ስምምነት አንቀጽ 3, 6(1) የአፍሪካ ህፃናት መብቶችና ደህንነት ቻርተር አንቀጽ 4(1), 5(1) የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2126(2), 2127, 2130 2131, 2089(2), 2081(1)

  Download Cassation Decision

 • በሕጉ አግባብ ስልጣን ባለው አካል ያልተከፈለ ቀረጥና ታክ እንደተከፈለ የሚቆጠርበት የሕግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣ ---ቀረጥና ታክሱን የማስከፈል ስልጣን በህገ መንግስቱ ተለይቶ የተቀመጠ ስለመሆኑ፣ የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 96(1) አዋጅ ቁጥር 578/2ዐዐዐ አንቀጽ 6(8)፣9 እና 1ዐ፣ ከአዋጅ ቁጥር 622/2ዐዐ1 አንቀጽ 2(6)፣(2(11)፣2(17) እና 91 ፣15(1)፣ 82 (1ሀ))((ለ))

  Download Cassation Decision

 • ጉዳዩ ከይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እና ከሰነዶች ጋር የተያያዘ በመሆኑ ብቻ በፍርድ ሊወሰን የሚችል አይደለም ሊባል ስላለመቻሉ፤ እንዲሁም የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ካርታ ወይም ሌሎች ሰነዶች ተወስደውብኛል ተብሎ ክስ በሚቀርብበት ጊዜ የተወሰዱበት አግባብ ህጋዊ መሆን አለመሆኑ በፍርድ ቤት ሊጣራ የሚችል ጉዳይ ስለመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 37(1)፣ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.4

  Download Cassation Decision

Page 4 of 4