Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • በመሬት ይዞታዬ ላይ ጉዳት ደርሶብኛል በማለት የሚቀርብ ክስ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ መቅረብ ያለበት ሰለመሆኑ ፍ/ሕ/ቁ 2143

    Download Cassation Decision

  • የአሰሪውን ትእዛዝ አልፈፀመም ተብሎ የስራ ስንብት ያደረገ አሰሪ ትእዛዙ ያለመፈጸሙን የማስረዳት ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 13

    Download Cassation Decision

  • አሰሪ የተጠየቀን የስራ ስንብት ክፍያን በተመለከተ አጠቃላይ ተቃውሞ አቀርቦበት እያለ ፤ ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤት ሰሌቱን በተመለከተ አልተቃወመም በሚል በመተርጎም በሰራተኛው የተጠየቀን የስንብት ክፍያ ዳኝነት ሙሉ በሙሉ በመወሰን የሚሰጥ ዳኝነት ተገቢ ስላለመሆኑ ፤ፍ/ቤቱ በሕጉ አግባብ አስልቶ መጠኑን ሊወሰን የሚገባ ሰለመሆኑ ፤ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 40 (1 እና 2)

    Download Cassation Decision

  • ከፊል የዳኝነት ሰልጣን ላለው አካል በፍሬ ነገር ደረጃ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ መሆኑ በግልፅ ተቀምጦ እያለ፤ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በሕግ አተረጎጎም ረገድ ብቻ የተሰጠውን ስልጣን በማለፍ ማሰረጃን በመመዘን በፍሬ ነገር ላይ የሚሰጠው ድምዳሜ ሰርዓቱን የተከተለ ስላለመሆኑ ፤ የአ/ብ/ክ/መ/ መገናኛ ብዙሀን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ 200/2005 አንቀፅ 13(2)

    Download Cassation Decision

  • የአንድ ድርጅት ከሌላ ጋር መቀላቀል ወይም  መከፋፈል  ወይም የባለቤትነት መብት ወደ ሌላ መተላለፍ የስራ ውልን የማቋረጥ ውጤት የማይኖረው ስለመሆኑ

    አዋጅ ቁ. 377/1996 አንቀፅ 23(2)

    የሰ/መ/ቁ. 119734

    አንድ ከሳሽ ክስ ሲያቀርብ ለክሱ ምክንያት የሆኑት ነገሮች በሙሉ አጠቃሎ ማቅረብ ሲችል ቀንሶ ባስቀረው ጉዳይ ላይ ድጋሚ ክስ ሊያቀርብ የማይችል ስለመሆኑ
    ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 216(3)፤218

    አንድ ጉዳይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343 መሰረት ወደ ስር ፍ/ቤት ተመልሶ ፍሬ ነገሩ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በመቃወሚያው ላይ አስቀድሞ በተሰጠ ብይን ላይ ተጠቃሎ የሚቀርብ የሰበር አቤቱታ ህጉን መሰረት ያደረገና ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ
    የፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 320(3)፤
    /የፌ/ፍ/ቤቶችን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2(1) በፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀደም ሲል በሰ/መ/ቁ 90810 ፣ 76963፣ 125165 እና ሌሎችም በርካታ መዛግብት ተሰጥቶ የነበረው የህግ ትርጉም በዚህ መዝገብ ውሳኔ ተለውጧል፡፡/

    Download here

  • የእርሻ መሬት ይዞታን ከማስለቀቅ ጋር በተገናኘ የሚቀርብ ክስ ከእርሻ መሬት ልዩ ባህሪ አንጻር ከንብረቱ የሚገኘውን አላባ ወይም ሌላ ጥቅም ጭምር ከዋናው ክስ ጋር አጣምሮ ይክሰስ ሊባል ስለማይችል፣ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 216/3/፣218/ሀ/ አዋጅ ቁ. 452/1997 አንቀጽ 12 የአ/ክ የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 130/1999 አንቀጽ 16 ደንብ ቁ. 151/2005 አንቀጽ 18

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል ጉዳይ ተከሳሽ በሌለበት ጠበቃ ብቻውን ሊቀርብ አይችልም የሚለው ጉዳይ ተፈፃሚ የሚሆነው ለተፈጥሮ ሰዎች እንጂ የህግ ሰውነት ላላቸው ሰዎች ስላለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.127

     

    የሰ/መ/ቁ/120762 የካቲት 25 ቀን 2008 ዓ.ም

    ዳኞች፡-አልማው ወሌ

    አንድ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ወራሽነት መብቱን ለአካላ መጠን ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 15 ዓመት ባለው ጊዜ ውሰጥ የውርሱን ንብረት ለመጠየቅ በይርጋ የማይታገድበት ስለመሆኑ ፤ ፍ/ብ/ሕ/ቁ 198 ፣ 1000(2) የተሰጠ ወራሽነት ማረጋገጫ የተሰረዘ ከሆነ ፤በይግባኝ ካልተሻረ ከዚህ ጋር ተያይዞ የተሰጠ የውርስ ባለቤትነት ውሳኔ የሰረዝልኝ ጥያቄን ክርክር ስምቶ መወሰን ያለበት እንጂ በቀድሞ ያልተነሳ የይርጋ ተቃውሞ በመቀበል ጥያቄው ውድቅ ሊደረግ የማይገባ ሰለመሆኑ ፤

    Download Cassation Decision

  • የመጀመሪያ ሚስት በንብረትዋ ላይ ስምምነት ባላደረገችበት ፤ባል ሁለተኛ ሚስት ሲያገባ መቃወሚያ አላቀረበችም በማለት በንብረትዋ ላይም ስምምነት አድርጋለች በማለት በመደምደም ፤ሁለተኛ ሚስት እኩል እንድትካፈል በማለት የሚሰጥ ውሳኔ ህጋዊ ስላለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ በግልጽ በተቀመጡ ሁኔታዎች ካልሆነ በስተቀር አንዲት ሰፍሰጡር ሴት ከወሊድ በኋላ አራት ወራት ውስጥ ከስራ ያለመባረር መብት ያላት ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 25፣27፣29/3/ እና 87/5//6/

    Download Cassation Decision

  • ፍ/ሥ/ሥ/ሕጉ በግልፅ ያልተካደ ፍሬ ነገር እንደታመነ ይቆጠራል የሚለው ድንጋጌ በልዩ ስርዓት( በአጭር ሁኔታ) ለሚመሩ ክርክሮች ላይ ጭምር ለቀረበ መልስ ላይም ተፈፃሚ የሚሆን ስለመሆኑ፤ ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 284 (ሀ)

    Download Cassation Decision

  • የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ነው የተባለ ንብረትን አፈፃፀምን በተመለከተ የንብረቱ ሕጋዊነት ላይ የሚመለከተው አስተዳደር አካል አግባብ ያለው ውሣኔ እስኪሰጥ ድረስ መሸጥ መለወጥ ባይቻልም ባለበት ሁኔታ የግራ ቀኙን እኩል ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ አግባብ በጋራ የሚያስተዳድሩበት ወይም ተከፋፍለው የሚጠቀሙበት ወይም አከራይተው ጥቅሙን እኩል የሚከፋፈሉበት ሁኔታ መመቻቸት ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ 386/2/

    Download Cassation Decision

  • የአዲስ አበባ ከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ቀደም ብሎ በሰጠው ፍርድ ላይ የሚቀርብለትን የፍርድ መቃወሚያ ተቀብሎ የመዳኘት ስልጣን ያለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358፣የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 37/1/ አዋጅ ቁ. 721/2004

    Download Cassation Decision

  • በህግ የሰውነት መብት የተሰጣቸው ተቋማት በድሃ ደንብ ዳኝነት ሳይከፍሉ ለመስተናገድ በማስረጃ ሊያቀርቡት ስለሚገባቸው ጉዳዮች የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.467-479

    Download Cassation Decision

  • "

    ከሳሽ ያቀረበው ክስ እና የክሱ ዝርዝር ይዘት የተለያየ ሆኖ የተገኘ ከሆነ ፤ ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤት ክሱ ተሻሽሎ እንዲቀርብ በማዘዝ ፤የክርክሩን ሂደት መምራት ያለበት ሰለመሆኑ፤ ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 90(1)

    Download Cassation Decision

    "

  • ማንኛውም የቀበሌ መኖሪያ ቤት የተከራየ ሰው የራሱ ቤት ከገነባ ወይም የጋራ ሕንጻ ቤት ከገዛ ወይም የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲን ቤት ካገኘ ወይም በሌላ በማናቸውም ምክንያት ቤቱን የለቀቁ ከሆነ ቤቱን ባለበት ሁኔታ ለአስተዳደሩ ማስረከብ ያለበት ስለመሆኑ፣ የአ.አ.ከ.አስተዳደር ባወጣው የመንግስት ቤቶች አስተዳደር መመሪያ ቁ. 3/2007 አንቀጽ 42/ሀ

    Download Cassation Decision

  • በክስ አቀራረብ ሥርዓት ላይ ጉድለት ያለበት መሆኑ ተረጋግጦ የተዘጋ መዝገብ ምንም አይነት ክስ እንዳልቀረበ የሚያስቆጥርና የይርጋ ጊዜ የማቋረጥ ውጤት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 278 (2) (ሀ) እና (3)

    Download Cassation Decision

  • በክርክር ተሳታፊ ያልሆነ ወገን በስር ፍርድ ቤት በተሰጠ እግድ ትዕዛዝ የዕግድ ትዕዛዙን ለሰጠው ፍ/ቤት የዕግድ ይነሳ አቤቱታ ሳያቀርብ በቀጥታ ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ይግባኝ የሚያቀርብበት እና የዕግድ ትዕዛዙ ላይ ውሣኔ የሚያሰጥበት ስርዓት የሌለ ስለመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/ 154፤158

    Download Cassation Decision

  • የተጨማሪ እሴት ታክስ የፌዴራል ታክስ በመሆኑና የክልል የገቢዎች ቢሮዎች ታክሱን የሚያስተዳድሩት በዉክልና ስልጣናቸዉ በመሆኑ ምንም እንኳ ታክሱ የተወሰነዉ በክልሉ የገቢዎች ቢሮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እና የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ቢሆንም የሕግ ስህተት አለበት የሚል ወገን ይግባኝ ማቅረብ የሚገባዉ ስልጣን ላለዉ የፌዴራል ፍ/ቤት ወይም የዉክልና ስልጣን ላለዉ የክልል ፍ/ቤት ሥለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 28(2) እና አንቀጽ 30፣አንቀጽ 43(3)፣ 112

    Download Cassation Decision