Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • የ ተፋጠነ ሥነ-ሥርዓት የክርክር አመራር የሰዎችን የመከላከልና የመሰማት ሕገ መንግስታዊ መብትን በሚነካ መልኩ መተርጎም እና ሥራ ላይ መዋል የማይገባው ስለመሆኑ፡- ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.284-287

    Download Cassation Decision

  •  አንዱን የፍትሓብሔር ክስ ባንድ ወይም ካንድ በበለጡ ፍርድ ቤቶች ዘንድ ለማቅረብ የሚቻል ሲሆን የክሱ ማመልከቻ በቀደምትነት የቀረበለት ፍርድ ቤት ብቻ የዳኝነት ሥልጣን እንዳለው ተቆጥሮ ለክርክሩ ውሳኔ ሊሰጥ የሚችል ሥለመሆኑ  አንድን ሰው በመወከል በፍርድ ቤት ቀርቦ ለመሟገት በህጉ የተቀመጠውን የዝምድና ደረጃ ወይም በህጉ የተቀመጡትን መስፈርቶች የሚያሟላ የውክልና ስልጣን የሚያስፈልግ ስለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 7(2)፣32፣57፣58 እና 63

    Download Cassation Decision

  • አንድ ተከሳሽ በወንጀል ተጠርጥሮ የጣት አሻራ ሰጥቷል በመባሉ ብቻ እንደጥፋተኛ ተቆጥሮ የወንጀል ጥፋት ሪከርድ እንዳለበት ተደርጎ ግምት በመውሰድና እንደ ቅጣት ማቅለያ ሳይያዝ የሚሰጥ ውሳኔ መሰረታዊ የህገ መንግስት መርህን የሚጣረስ ስለመሆኑ የወንጀል ህግ አንቀጽ 82

    Download Cassation Decision

  • በ ትግራይ ክልል የጎጆ መውጫ ይዞታና ቤት የሚመለከትን ጉዳይ የቀበሌ መሬት ዳኝነት ኮሚቴ ጉዳዩን ተቀብሎ አይቶ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ በተሰጠዉ ዉሳኔ መብቴን ይነካል በማለት የመቃወሚያ ማመልከቻ ሲቀርብ የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻውን ተከትሎ የቀደመዉን ዉሳኔ የማጽደቅ ወይም የማሻሻል ወይም የመለወጥ ወይም የመሰረዝ ስልጣን ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው የቀበሌ መሬት ዳኝነት ኮሚቴ ስለመሆኑ፡- የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.358 ፣ 360(2)

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል ተጠርጥሮ በህግ ከለላ ስር የሚገኝን ተጠርጣሪ በዋስትና የመለቀቅ ጥያቄ ባነሳ ጊዜ ተጠርጣሪው በከተማው ውስጥ ቋሚ የመኖሪያ /የመታወቂያ/ አድራሻ የለውም በማለት የዋስትና መብቱን መከልከል ህገ መንግስታዊ ስላለመሆኑ፣ አንቀጽ 19/6/፣ 25 እና የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 69/ሀ/

    Download Cassation Decision

  • በ ቀድሞ ክርክር ጊዜ በግልጽ ዳኝነት ተጠይቆበት በዝምታ የታለፈ ጉዳይ በሌላ ጊዜ የክስ እና የክርክር ምክንያት ሊሆን አይችልም ማለት እንጂ ፍ/ቤቶች በተከራካሪ ወገኖች በግልጽ ዳኝነት የተጠየቀበትን ጉዳይ በዝምታ ማለፍ የማይችሉ ስለመሆኑ የፍ/ስ/ስ/ሕ ቁጥር 5 (3) ፤182 (1)

    Download Cassation Decision

  • አ ንድ ሠራተኛ መደበኛ የጡረታ ዕድሜው ደርሶ የመብቱ ተጠቃሚ መሆኑ በተረጋገጠበት አግባብ ለጡረታ መብት ላልተያዘለት ጊዜ የሥራ ስንብት ካሳ ሊከፈለኝ ይገባል በማለት የሚያቀርበው ጥያቄ የህግ መሰረት የሌለው ስለመሆኑ፡- የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 39፤ 43 (4)ፈ አዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀጽ 2/2/ሰ/ እና /ሸ/፤

    Download Cassation Decision

  • በመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚፈጸም ጊዜያዊ ቅጥር ውል ሊከተላቸው ስለሚገባ መስፈርቶች መንግስት መስሪያ ቤት የሚደረግ የጊዜያዊ ሰራተኛ ቅጥር ውል ለፕሮጀክት ስራ ካልሆነ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 515/99 አንቀጽ 22/3/፣93 የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ህዳር 18/2005 በቁጥር መ80-893/1/ የተጻፈ ደብዳቤ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር በቁጥር ሲሰመ30/መ/18/22/459 በ16/04/2005 የተጻፈ ደብዳቤ

    Download Cassation Decision

  • ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ቢያንስ 10 ዓመት ያገለገለ እና በራሱ ፈቃድ ወይም በአዋጅ ከተጠቀሱት ውጪ በሆነ ምክንያት አገልግሎት ካቋረጠ የጡረታ መውጫ እድሜው ሲደርስ የአገልግሎት ጡረታ አበል ለዘለቄታው ሊከፈለው የሚችል ስለመሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ጡረታ(ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር907/2007 አንቀጽ 5/2/፤በአንቀጽ 18

    Download Cassation Decision

  • አ ንድ ወራሽ በሟች የውርስ ንብረት ከሌሎች ወራሾች ጋር እንዲጣራ በግልፅ ተስማምቶና ውክልና ሰጥቶ በሚጣራው የውርስ ፋይል ተሳታፊ ሆኖ እያለ ከሚጣራው ንብረት ላይ የግል ንብረት ያለ በመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.41 መሰረት ጣልቃ ገብቼ እንድከራከር እንዲፈቀድልኝ በማለት የሚያቀርበውን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ በውርስ አጣሪ ተጣርቶ የቀረበውን ሪፖርት ተቀብሎና መርምሮ ተገቢውን ውሳኔ ከመስጠት ባለፈ የጣልቃ ገብ ክርክሩን ሊቀበለው የማይገባ ስለመሆኑ፡- የፍ/ሕ/ቁ. 947

    Download Cassation Decision

  • በሥራ ላይ የደረሰ የአካል ጉዳት ወደ ዘላቂ የአካል ጉዳት ከተሸጋገረ የካሣ ጥያቄው የይርጋ ጊዜ መነሻ መቆጠር ያለበት ጉዳቱ ከደረሰበት ጊዜ ሳይሆን ዘላቂ የአካል ጉዳት መሆኑ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 162(1)

    Download Cassation Decision

  • የዋስትና መብት የሚነፈግባቸው ምክንያቶች ፍርድ ቤቶች ከተለያዩ ሁኔታዎች አንፃር እየተመለከቱ ሊመዝኗቸው የሚገባቸው ስለመሆኑ አንድ ተከሣሽ የዋስትና መብት ቢከበርለት ግዴታውን የሚፈጽም የማይመስል ነው ተብሎ ግምት የሚወሰደው በቂና ህጋዊ ሊባሉ በሚችሉ ምክንያቶች ሊሆን እንደሚገባ፤ እንዲሁም ምክንያቶቹ በቂና ህጋዊ ናቸው የሚለው ጉዳይ ከተለያዩ ከባባዊ ሁኔታዎችና ከጉዳዩ ልዩ ባህርይ አንፃር ፍርድ ቤቱ ሊገነዘበው የሚችለው ተደርጎ ሊወሰድ የሚገባ ስለመሆኑ የወ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 67(ሀ)

    Download Cassation Decision

  • በ አንድ ክርክር ከሳሽ የሆነው ወገን ጣልቃ በገባ ተከራካሪ ወገን ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክርክር ከማንሳት የሚከለከልበት የሕግ መሰረት የሌለ ስለመሆኑ የፍ/ብሥ/ሥ/ሕ/ቁ.39፤40፤በ አንድ ክርክር ከሳሽ የሆነው ወገን ጣልቃ በገባ ተከራካሪ ወገን ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክርክር ከማንሳት የሚከለከልበት የሕግ መሰረት የሌለ ስለመሆኑ የፍ/ብሥ/ሥ/ሕ/ቁ.39፤40፤41

    Download Cassation Decision

  • የዕግድ ትእዛዝ በባህሪው ጊዜያዊ በመሆኑ ለዕግዱ ምክንያት የሆነው ክርክር ዕልባት ሲያገኝ የሚነሳ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 154

    Download Cassation Decision

  • ፍ/ቤት የሟችን ኑዛዜ ፈራሽ መሆን አለመሆን ላይ ተመስርቶ በሚቀርብለት የዳኝነት ጥያቄ ላይ አግባብ ያለው ዳኝነት ከመስጠት አልፎ በኑዛዜ የሚደርሳቸውን ድርሻ በትክክል ለይተው ሳይጠይቁ የውርስ ንብረት መጠን ግምት በመቀመጡ ብቻ ይኼው ግምት መሰረት ተደርጎ ሊፈጸም የሚችል ዳኝነት ስላለመኖሩ ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 182(1)

    Download Cassation Decision

  • በ ትምህርት ደረጃው ከፍተኛ የሆነና በባህሪው ለህብረተሰብ አርአያ ሊሆን የሚገቡ ሰዎች ፍፁም ነውረኛ በሆነና ጨካኝነት በተሞላበት ሁኔታ የፈፀሙት ከባድ የወንጀል ድርጊት የወንጀል አፈጻጸሙን ከባድነት እና የወንጀለኛውን አደገኛነት የሚያሳይ በሆነ ጊዜ ወንጀለኛው ላይ የቀረበ የቀደመ የወንጀል ሪከርድ ያለመኖር ወንጀለኛው ጥሩ ፀባይ ወይም መልካም ፀባይ ያለው ነው የሚል ግምት ለመውሰድ የማያበቃ ስለመሆኑ፣ -የወ/ህ/ቁ. 184/1/ሀ/ እና ለ ቁ. 539 ቁ. 671/1/0/ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ. 2/2006 የኢ.ፌ.ዲ.ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት በአንቀጽ 15 እና የወ/ህ/ቁ. 117

    Download Cassation Decision

  • በ ሀራጅ አካሄድና ሽያጭ ስርዓት ተገቢ ያልሆነ ድርጊት፣ ማጭበርበር ወይም ማታለል መኖሩ በማስረጃ ከተረጋገጠ ጨረታውን ለማፍረስ በቂ ምክንያት ስለመሆኑ፣ የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁበ ሀራጅ አካሄድና ሽያጭ ስርዓት ተገቢ ያልሆነ ድርጊት፣ ማጭበርበር ወይም ማታለል መኖሩ በማስረጃ ከተረጋገጠ ጨረታውን ለማፍረስ በቂ ምክንያት ስለመሆኑ፣ የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 445

    Download Cassation Decision

  • ሠ ራተኛ በህይወቱ ላይ አደጋ ሊደርስበት በሚችል አኳኋን እንዲሰራ ማድረግ ህገወጥ ድርጊት ስለመሆኑና ሠራተኛው ያለማስጠንቀቂያ ውል እንዲያቋርጥ በቂ ምክንያት ስለመሆኑ፣ የአ/ቁ. 14/ሠ/ እና አንቀጽ 32/1/ለ

    Download Cassation Decision

  • በፍርድ ቤት የቀረበ ጉዳይ የክስ ምክንያት አለው ብሎ ለመወሰን የሚቻለው በክሱ ላይ የተገለፀው ነገር ቢረጋገጥ ከሳሹ የጠየቀውን ዳኝነት ለማግኘት ሕግ የሚፈቅድለት የሆነ እንደሆነ ስለመሆኑ፡- ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በህግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብ እና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ፡- የኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 37(1)

    Download Cassation Decision

  • አ ንድ ጉዳይ በማንኛውም የክርክር ደረጃ ላይ በሚገኝበት ወቅት ተከራካሪ ወገኞች በእርቅ ወይም በግልግል ስምምነት የመጨረስ መብት ያላቸው ቢሆንም፤ ክሱን በእርቅ ለመጨረስ ቀጠሮ ያስለወጠ ወገን ቀጠሮ በተሰጠበት ቀን ፍ/ቤትን ቀርቦ የተደረሰበትን ደረጃ ያለማሳወቅ እና ለረጅም ጊዜ ጉዳዩን ያለመከታተል ኪሳራ እንዲከፈል ሊወሰንበት ከመቻሉ በላይ አዲስ ክስ መመስረት የማይቻል ስለመሆኑ፡- የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ. 69 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ቁ. 275 እና 79/1/

    Download Cassation Decision