Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • ከቅጥር ውል በመነጨ ግንኙነት የሚጠየቅ ማንኛውም ክስ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ ፣ የይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው በመብቱ ለመጠቀም ከሚችልበት ቀን ቀጥሎ ካለው ቀን ጀምሮ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 162/1/፣163/1/

    Download Cassation Decision

  • በ ከተማ አስተዳደር ወይም በቀበሌ ያላግባብ የተያዘን የምርጫ ቤት ለማስመለስ የሚቀርብን ክስ የማየት ስልጣን በህግ ለሌላ የመንግስት አካል ባልተሰጠበት ሁኔታ መደበኛ ፍርድ ቤቶች የማየት ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ፡- ኢ.ፊ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 37

    Download Cassation Decision

  • አ ንድ ሰው ቀድሞ በቀረበ ክርክር ጣልቃ ገብ በመሆን ክርክር ያቀረበ ወይም በጉዳዩ ተሳታፊ የነበረ መሆኑ በጣልቃ ገብነት በቀረበበት ክርክር ግልጽ ዳኝነት ባልተጠየቀባቸው ጉዳዮች በሌላ ጊዜ ክስ ለማቅረብ የሚችል ስለመሆኑና በዚህ አግባብ የሚቀርብን ክስ በቀድሞው ክርክር ተጠቃሎ መቅረብ የነበረበትና ተከፋፍሎ ዳኝነት ሊቀርብበት አይገባም በሚል አቤቱታን ዉድቅ በማድረግ የሚሰጥ ውሳኔ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 41፣216 እና 218

    Download Cassation Decision

  • አንድ ተከሳሽ በሕግ አግባብ መጥሪያ የደረሰዉ እና እርሱ በሌለበት ዉሳኔ መሰጠቱን ማወቁን አግባብነት ባለዉ ማስረጃ ባልተረጋገጠበት  ሁኔታ በሌለሁበት የተሰጠዉ ፍርድ ተነስቶ የመከላከያ መልስ ላቅርብ በማለት የሚያቀርበውን አቤቱታ በህግ በተቀመጠው አንድ ወር ጊዜ ዉስጥ አልቀረበም በሚል ምክንያት ብቻ መከላከያ መልስና ክርክር አቅርቦ የመሰማትና ፍትሕ የማግኘት ሕገ መንግስታዊ መብት መንፈግ ያልተገባና ህጋዊነት የሌለው ስለመሆኑ፡- 

    የኢ.ፌ.ዴ.ሪ.ሕገ መንግስት አንቀጽ 37፣የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.78፣95 /2/

    Download here

  • አንድ ተከሳሽ በሕግ አግባብ መጥሪያ የደረሰዉ እና እርሱ በሌለበት ዉሳኔ መሰጠቱን ማወቁን አግባብነት ባለዉ ማስረጃ ባልተረጋገጠበት  ሁኔታ በሌለሁበት የተሰጠዉ ፍርድ ተነስቶ የመከላከያ መልስ ላቅርብ በማለት የሚያቀርበውን አቤቱታ በህግ በተቀመጠው አንድ ወር ጊዜ ዉስጥ አልቀረበም በሚል ምክንያት ብቻ መከላከያ መልስና ክርክር አቅርቦ የመሰማትና ፍትሕ የማግኘት ሕገ መንግስታዊ መብት መንፈግ ያልተገባና ህጋዊነት የሌለው ስለመሆኑ፡- 

    የኢ.ፌ.ዴ.ሪ.ሕገ መንግስት አንቀጽ 37፣የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.78፣95 /2/

    Download here

  • •ይ ግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በተለይ ካልፈቀደ በቀር ይግባኝ ባይ በይግባኝ ማመልከቻ ላይ ዘርዝሮ ያልገለጸውን አዲስ ነገር በማንሳት ወይም መሠረት በማድረግ ለመከራከር የማይችል ስለመሆኑ፡- •ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በይግባኝ ማመልከቻ ተዘርዝሮ ከተገለጸ ወይም ክርክር ከተነሳበት ውጭ በሆነ ነገር ፍርድ መስጠት የማይችል ስለመሆኑ፡- የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 328 /2/፤328 /3/

    Download Cassation Decision

  • ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠረን ሠራተኛ የሥራ ውሉ የሚቋረጥበት ጊዜ ሲደርስ አሰሪው ማሰናበት የሚችል ሲሆን ስንብቱ ከህግ ውጪ ነው ሊያሰኝ የማይችል ሲሆን በዚህ አግባብ የተሰናበተን ሰራተኛ የሥራ ሥንብት ክፍያ ሊያገኝ ይገባል የማያስብል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 24/1/፣ አንቀጽ 30/1/

    Download Cassation Decision

  • ሁ ከት ተወግዶ ይዞታ እንዲለቀቅ ክስ ቀርቦ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ በድጋሚ ይዞታ ይለቀቅልኝ በሚል ክስ መመስረት ዳኝነት በተሰጠበት ጉዳይ ላይ በድጋሚ የቀረበ በመሆኑ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 5፣ 244(ለ)

    Download Cassation Decision

  • ባ ል እና ሚስት በጋራ ሲጠቀሙበት የነበረ መሬት ጋብቻው በአንደኛው ተጋቢ ሞት የተቋረጠ ቢሆንም ሌላኛው ተጋቢ በሌላ ህጋዊ ምክንያት መብቱ እስካልተቋረጠ ድረስ ይዞታው በስሙ ተመዝግቦ ደብተር ለማግኘት እና በይዞታው ለመጠቀም የሚችል ስለመሆኑ፣ ሴቶች መሬትን በመጠቀም፤በማስተላለፍ፤በማስተዳደርና በመቆጣጠር ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል መብት ያላቸዉ ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ሕ/መ አንቀጽ 35/7/፣ የኦሮሚያ የገጠር መሬት አዋጅ ቁ. 130/99 አንቀጽ 6/3/ እና ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀጽ 15

    Download Cassation Decision

  • ሰ በር ችሎቶች ሥነ ሥርዓታዊ የሆነ የህግ ጥያቄን ብቻ ለማየት ስልጣን እንዳላቸው ግንዛቤ በመውሰድ በአንድ ጉዳይ ላይ የተሰጠ ውሳኔ ስነ-ስርዓታዊ ሕጎችን መሰረት አድርጎ የተሰጠ መሆን ያለመሆኑን መመርመር አንጂ ከዚህ ውጪ መደበኛ ሕጎችን መሰረት አድርገው በሸሪዓ ፍርድ ቤት የተሰጠውን ውሳኔ ሊመረምሩ የሚችሉበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፡- በኢ.ፌ.ዲ.ሪፐብሊክ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ))፣ 80(3(ለ)) እና አዋጅ ቁጥር 53/94 እና አዋጅ ቁጥር 188/1992 አንቀጽ 6

    Download Cassation Decision

  • ለ ቀጠሮ ምክንያት የሆነ ጉዳይ ሳይፈፀም የቀረው ከተከራካሪዎቹ ወገኖች በአንደኛው ጉድለት የሆነ እንደሆነ መፈፀም ይገባው የነበረው ጉዳይ ያልተፈፀመ ቢሆንም እንኳ ፍርድ ቤቱ የጉዳዩን መፈፀም ሳይጠብቅ የመሰለውን ውሳኔ መስጠት ስለመቻሉ፡- የፍ/ብ/ስ/ሥ/ህ/ቁ 199(1)

    Download Cassation Decision

  • አ ንድ ተከራካሪ ወገን በመከላከያ መልስ ወይም በማናቸዉም ሌላ መንገድ የተከሰሰበትን ነገር በሙሉ ወይም በከፊል ያመነ እንደሆነ ሌላኛዉ ተከራካሪ ወገን በዚህ እምነት መሰረት ዉሳኔ እንዲሰጠዉ መጠየቅ እንደሚችል እና ፍ/ቤትም ሌላ በማስረጃ የሚረጋገጥ ነገር ቢኖርም እንኳን በታመነዉና ዉሳኔ እንዲሰጥበት በተጠየቀዉ ጉዳይ ብቻ ፍርድ መስጠት የሚገባው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.242

    Download Cassation Decision

  • በ አንድ ክርክር ውስጥ የከሳሾች ወይም የተከሳሾች ብዛት ከአንድ በላይ ሲሆንና ክርክሩም ከሳሾችን ወይም ተከሳሾችን በአንድ ዓይነት መልክ የሚመለከታቸው ሲሆን ከሳሾቹ ወይም ከተከሳሾቹ አንዱ በጠቅላላው ውሳኔ ላይ ይግባኝ ሲጠይቅና ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤት ፍርዱን በመለወጥ ያሻሻለው ወይም የለወጠው ወይም ያጸናው ፍርድ ይግባኙን ባላቀረቡት ከሳሾች ወይም ተከሳሾች ላይም በይግባኝ ደረጃም በቀረበው ጉዳዩ ከከሳሾቹ መካከል አንዱ ይግባኝ ጠይቆ የሚሰጠው ውሳኔ ሌሎችንም የሚያካትት ስለመሆኑ፡- የፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 35 እና 331

    Download Cassation Decision

  • አንድ ውል አይፈርስም ተብሎ ከተወሰነ በኋላ በተደረገው ውል መነሻነት የወጣ ወጭ ካለ በማጣራት በዚያው መዝገብ ላይ መወሰን የሚገባው እንጂ በሌላ መዝገብ አዲስ ክስ ቀርቦና እንዲከራከሩበት መወሰን ለተራዘመ የክርክር ሂደት ስለሚጋብዝ በዚህ መነሻነት መዝገቡን መዝጋት ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ 

    Dowload here

  •  አንድ ከሳሽ መብቱን ማግኘት የሚገባው ከየትኛው ተከሳሽ ላይ እንደሆነ ለይቶ ለማወቅ የሚያጠራጥር ሁኔታ ያጋጠመው ሲሆን አንዱን ወይም ከአንድ በላይ የሆኑትን ሰዎች በህብረት በመክሰስ ሀላፊነቱ የሚመለከተው የትኛው እንደሆነ ተለይቶ እንዲወሰንለት ማመልከት ስለመቻሉ
     ፍርድ ቤቶች በአንድ ክስ ላይ ስማቸው በተከሳሽነት ከቀረቡ መካከል ስማቸው ከመጠቀሱ ውጪ በግልፅ ዳኝነት አልቀረበባቸውም በሚል ምክንያት ብቻ አንዱን ወይም የተወሰኑትን ሀላፊነት የለባቸውም በማለት የሚደርሱበት መደምደሚያ ህጉን ያተከተለ ስለመሆኑ፡-  

    የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 36(5) 

    Download here

  • ለ አንድ ክርክር መነሻ የሆነ ቤትና ይዞታ በክልል የሚገኝ ሲሆንና የስረ ነገር ስልጣኑ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቢሆንም ጉዳዩ መታየት ያለበት ንብረቱ በሚገኝበት ክልል የዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስለመሆኑ፡-

    Download Cassation Decision

  • ሠ ራተኞች በሙሉ እውቀታቸውና ብቃታቸው ሰርተው እኩል የምርት ጥራትና መጠን ያመርታሉ ተብሎ የማይገመት ስለመሆኑና የአንደኛው ሠራተኛ ያመረተው ምርት መጠንና ጥራት ብቻ ለሌላው ሠራተኛ ከአቅም በታች ሰርቷል ለማለት በቂ መሰፈርት ሆኖ ሊወሰድ የማይገባ ስለመሆኑ፡-

    Download Cassation Decision

  • ለ አንድ ሠራተኛ ማስጠንቀቂያ መፃፍ ብቻውን “የስራ መሪ” የማያስብልና ጉዳዩ በስራ ክርክር ችሎት ሊታይ አይችልም የሚባልበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፡- አሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁ. 377/96 3/2/ /ሐ/ ስ እና ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀጽ 2/1/ /ሐ/

    Download Cassation Decision

  • አንድ አሠሪ የቀጠረውን ሠራተኛ በሙከራ ጊዜ አጥጋቢ ውጤት አላሳየህም በማለት የሥራ ውሉን ያለምንም ማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ መብት የሚኖረው በህጉ አግባብ የተደረገ የሙከራ ጊዜ ስምምነት መኖሩ ሲረጋገጥ ብቻ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 11/1/ /2/ እና /3/

    Download Cassation Decision

  • አ ንድ የመሬት ሽያጭ ውል ህገ ወጥ ውል መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ ገዥ ወገን በመሬቱ ላይ የሰራው ቤት በሻጭ ፈቃድ እንደተሰራ ተደርጎ የህግ ግምት የሚወሰድበት አግባብ የማይኖር ስለመሆኑ የኢፌድሪ ህ/መ አንቀፅ 40 (3) እና የፍ/ብ/ህ ቁጥር 1678 (ለ) እና 1716

    Download Cassation Decision