Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • የከተማ ይዞታን የማስተዳደር ስልጣን በህግ አግባብ የተሰጠው አካል ስልጣንና ኃላፊነቱን በህግ አግባብ አልተወጣም የሚል ክርክር ያለው ወገን ጉዳዩን ለፍ/ቤት የማቅረብ መብት ያለው ስለመሆኑ
    የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 37፣ 40(3)(4)፣79(1) እና 78(4)

    Download here

  • በአንድ ክስ አጠቃሎ ክስ ማቅረብ የሚቻለው በተቋቋመ መብት ላይ ተመስርቶ እንጂ ዳኝነት በተጠየቀበት ጊዜ ያልበሰለ ወይም ያልተረጋገጠ መብት ጭምር ማቅረብ የማይቻል ስለመሆኑ
    የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33/2/፤216

    Download here

  • ማንኛውም ወገን የይርጋው ጊዜ ካለፈ በኋላ የይርጋ ጊዜን እንደመቃወሚያ አድርጎ ለማንሳት ያለውን መብት ሊተው የሚችል ስለመሆኑ፣ ዳኞች በገዛ ስልጣናቸው የይርጋውንም ደንብ መከላከያ ለመጥቀስ የማይችሉ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 165/5/፤ የፍ/ሕ/ቁ. 1856/2/

    Download Cassation Decision

  • አንድ ድርጅት በመክሰር ወይም በሌላ ምክንያት ለዘለቄታው መዘጋት ሠራተኞችን የሥራ ውልን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለማቋረጥ የሚያስችል ሲሆን መረጋገጥ ያለበት መሰረታዊው ነጥብ የአሰሪው ድርጅት ለዘለቄታው መዘጋት ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 24(4)

    Download Cassation Decision

  • የቀበሌ የንግድ ሱቅ አላግባብ ተይዞብኛል ይመለስልኝ በሚል ለክስ ምክንያት የሆነው ጉዳይ በግለሰቦች መካከል የተደረገ ውል ሲሆን ጉዳዩን ተቀብሎ የማየት የዳኝነት ስልጣን የከተማ አስተዳደር ፍ/ቤቶች ሳይሆን የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ስለመሆኑ
    የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 4፤የድሬዳዋ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 416/1996 አንቀጽ 33(1)(ረ) 

    Download here

  • አንድ ለክርክር ምክንያት የሆነ ንብረት በአፈፃፀም ምክንያት በሐራጅ እንዲሸጥ የአፈፃፀም መዝገቡን የያዘዉ ፍርድ ቤት ወስኖ የሐራጅ ማስታወቂያ ወጥቶ ገዥ ካልተገኘ ንብረቱን ባለ ገንዘቡ የመረከብ መብት ያለው ሲሆን ይህን ግምት ማስተባበል የሚቻለዉ ደግሞ ባለገንዘቡ ቤቱን እንዲረከብ በሚል ተሰጥቶ የነበረዉ ትዕዛዝ ስነ-ስርዓት ህጉ በሚፈቅደዉ አግባብ በሌላ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሻሩ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ
    የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 428(2) 

    Download here

  • ክርክርን በመስማት ላይ ያለ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወገን በክርክሩ ጣልቃ  እንዲገባ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ፣ ጣልቃ ለመግባት የሚያስችል ህጋዊ ምክንያት አለመኖሩን ፍርድ ቤቱ ካመነበት ክርክሩ በየትኛዉም ደረጃ ላይ ቢሆን ጣልቃ ገቡ ከክርክሩ ዉጪ እንዲሆን ትዕዛዝ ከመስጠት የሚከለክለዉ ነገር የሌለ ስለመሆኑ
    የፍ/ሥ/ሥርዓት ህግ ከአንቀጽ 40-43 

    Download here

  • አንድ ኑዛዜ ከፀደቀ በኋላ በቀረበ ንብረት ክፍፍል ውስጥ ወራሾች ከአውራሻቸው በውርስ ሊያገኙት ከሚገባው ድርሻ ተገቢውን ያላገኙ መሆኑን ገልጸው በሚከራከሩበት ጊዜ ፍሬ ነገሩ ተጣርቶ ከሚለይ በስተቀር ኑዛዜው ፀድቋል በሚል ምክንያት ብቻ የሐብት ድርሻቸውን በተመለከተ የሥረ- ነገር ክርክሩ ቀድሞ ታይቷል ተብሎ ውድቅ ሊሆን የሚችልበት የስነ ስርዓት ሕግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ 

    የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 5

    Download here

  • የዕርቅ ስምምነት ውል እንደዉሳኔ ተቆጥሮ በፍርድ ቤት ለአፈፃፀም አቅርቦ ለማስፈፀም ስምምነቱ ግልጽና የፈፃሚዉን አካል ግዴታ በማያሻማ ሁኔታ የሚገልጽ መሆን ያለበት ሲሆን ግልጽ ያልሆነ የእርቅ ስምምነት ሲቀርብ፣ ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት የሌላ ተከራካሪ ወገን ክርክር እንኳ መስማት ሳያስፈልገዉ ክሱን ዉድቅ ማድረግ የሚችል ስለመሆኑ
    ፍትሐብሔር ህጉ አንቀጽ 3312(1)

    Download here

  • አንድ ሰው መብቴን ይነካል በሚል የመቃወም አቤቱታ ያቀረበበት ዉሳኔ በሌላ አግባብ ከተሻረ እና መብትን ሊነካ የሚችል ዉሳኔ በሌለበት የሚቀርብ የመቃወም አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ
    ፍ/ሥ/ሥርዓት ህግ አንቀጽ 358ፍ/ሥ/ሥርዓት ህግ አንቀጽ 358

  • የባለሙያ ማስረጃ ፍፁም ስላለመሆኑና ከሌሎች ማስረጃዎች ጋር ተገናዝቦ ብቃቱና ተአማኒነቱ ሊመዘን የሚገባ ስለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • የባለሙያ ማስረጃ ፍፁም ስላለመሆኑና ከሌሎች ማስረጃዎች ጋር ተገናዝቦ ብቃቱና ተአማኒነቱ ሊመዘን የሚገባ ስለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • በመርህ ዯረጃ ጋብቻ በፌቺ እንዱፇርስ መጠየቅ የሚገባው ከባሌና ሚስቱ አንዯኛው ተጋቢ ወይም ሁሇቱም ቢሆንም በህግ አግባብ ተቀባይነት ያሇው ውክሌና ማስረጃ ጋር የሚቀርብ የፌቺ ጥያቄ ተቀባይነት ያሇው ስሇመሆኑ
    በፌ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.58፤ በፌ/ብ/ህ/ቁ.2199

    Download here

  • ሠ ራተኞች በሙሉ እውቀታቸውና ብቃታቸው ሰርተው እኩል የምርት ጥራትና መጠን ያመርታሉ ተብሎ የማይገመት ስለመሆኑና የአንደኛው ሠራተኛ ያመረተው ምርት መጠንና ጥራት ብቻ ለሌላው ሠራተኛ ከአቅም በታች ሰርቷል ለማለት በቂ መሰፈርት ሆኖ ሊወሰድ የማይገባ ስለመሆኑ፡-

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል ጉዳይ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ አዲስ የወጣ ህግ ተከሳሹን የሚጠቅም በሆነ ጊዜ ተከሳሹ አዲሱ ህግ ተፈፃሚ እንዲሆን አቤቱታ ባቀረበ ጊዜ አዲስ የወጣው ህግ ተፈፃሚ እንዲሆን መደረግ ያለበት ስለመሆኑና በዚሁ ጉዳይ አቤቱታ የቀረበበት ጉዳይ በባህሪው እንደመደበኛ የክርክር ጉዳይ የሚታይ ሳይሆን በቀረበ ጊዜ ሊስተናገድ የሚችል በመሆኑ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የቀረበ አቤቱታ ነው በማለት ተቀባይነት የለውም የማይባል ስለመሆኑ 

    የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 22(2)፣ የወ/ሕ/አንቀጽ 6 እና 9(1)፤ ዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት አንቀጽ15/1/ 

    Download here

  • አንድ የሥራ ውሉ በገዛ ፈቃዱ የተቋረጠበት የሥራ መሪ ያልተጠቀመበት የአመት እረፍት በገንዘብ ተቀይሮ ስለሚከፈልበት የሕግ አግባብ
    የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2563

    Download here

  • አ ንድ ሠራተኛ የፕሮቪደንት ፈንድ ወይም የጡረታ መብት ተጠቃሚ ከሆነ አሰሪው የስራ ስንብት ክፍያ በተደራቢነት የመክፈል ግዴታ የሌለበት ሲሆን በራሱ ፍላጎት እና ፈቃደኝነት የስራ ስንብት ክፍያን በተደራቢነት እንዳይከፍል ክልከላ የሚያደርግ ስላለመሆኑ፡- አዋጅ ቁጥር 494/1998 አንቀጽ 2 (ሰ)

    Download Cassation Decision

  • የፍርድ አፈጻጸምን የሚመራ ፍ/ቤት በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ በተዘረጋው ሥርዓት መሠረት እንደፍርዱ ይዘት እና መንፈስ ውጤት ባለው መልኩ ፍርዱን ከማስፈፀም በቀር የፍርዱን ይዘት በመመልከት የፍርዱን ይዘት አድማስ በማጥበብም ሆነ በማስፋት ፍርድን የመተርጎም ስልጣን የሌለው ስለመሆኑ
    የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 372፤378

    Download here

  • ባልና ሚስት በጋብቻ ዉስጥ ያፈሩት ቤት ፍቺን ተከትሎ እንዲከፋፈሉ ዉሳኔ ተሰጥቶ በአፈጻጸም ሂደት አንደኛው ወገን ድርሻ ከፍሎ ለማስቀረት የጠየቀና የተወሰነ ገንዘብ ብቻ ይዞ ቀርቦ ቀሪዉን ለመክፈል ጊዜ ከመጠየቅ በቀር ግዥዉን ለመፈጸምና የቅድሚያ ግዥ መብቱን በጊዜው ሳይጠቀም ከቀረ የቅድሚያ ግዥ መብቱ ሊጠበቅ የሚችልበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ
    በፍ/ብ/ሥ/ስ/ሕ/ቁ 430(1)

    Download here

  • ፍቺ ውሳኔን ተከትሎ በአንደኛው ወገን በቀረበ የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ሌላኛው ወገን በጋብቻ ጊዜ ካፈሩት ገንዘብና ንብረት ከፊሉ ከኢትዮጵያ ውጪ ይገኛል በማለት የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ማቅረቡ  ብቻውን ጉዳዩ የግል ዓለም አቀፍ ሕግን ተፈጻሚነት ጉዳይን/ conflict of laws/ የሚያስነሳ ነው ከሚል ድምዳሜ ላይ የማያደርስ እና የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱን የማየት የሥረ-ነገር ሥልጣን የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከመሆን የማያስቀረው ስለመሆኑ የፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ቁጥር 9፣17 ፤አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 11 (2) (ሀ) 

    Download here