Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • ይግባኝ የማቅረቢያ የመጨረሻ ቀን የመንግስት ስራ ዝግ በሆነበት ቀን ላይ ያረፈ ሲሆንና በቀጣዩ የሥራ ቀን ይግባኙ ተዘጋጅቶ ሲቀርብ ይግባኙ እንዲከፈት መፍቀድ ሥነ-ሥርዓታዊ ስለመሆኑ
    የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1862፣ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 323/2 ፣326 

    Download here

  • ለአንድ ጉዳይ ለምስክርነት የተቆጠረ ሰው በፍርድ ቤት ጥሪ መሠረት ቀርቦ የመመስከር ግዴታ ያለበት ሲሆን ምስክሩ ሊቀርብ ካልቻለም ፍርድ ቤቱ ተገቢ መስሎ በታየው መንገድ ትዕዛዝ በመስጠት ምስክሩ በሕግ አግባብ ተገዶ ወይም ታስሮ እንዲቀርብ በማዘዝ ምስክርነቱን በመስማትና ተገቢ ነው ካለም በሌላ ማስረጃም ጭምር በማጣራት የቀረበለት ጉዳይ ላይ ተገቢውን ዳኝነት ሊሰጥ የሚገባ ስለመሆኑ
    የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 116፣118(2)(ለ)

    Download here

  • አንድ ተከሳሽ የቀረበበት ክስ በይርጋ የሚቋረጥ መሆኑን ከጠቀሰ ከሳሹ ክሱ በሕጉ የተመለከተው ጊዜ ገደብ (ይርጋ) ያላለፈው መሆኑን፣ ጊዜው አልፎ ከሆነም ይርጋውን ሊያቋርጥ የሚችል ሕጋዊ ምክንያት መኖር ያለመኖሩን በተገቢው ማስረጃ ለማስረዳት የሚችልበት እድል ሳይሰጠው የተከሳሽ መቃወሚያ ብቻ መሰረት ተደርጎ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው ተብሎ ብይን የሚሰጥበት አግባብ ስነ ስርዓታዊ ስላለመሆኑ
    ፍ/ብ/ሕ/ቁጥር1000፣1846፣1852እና1853፤የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 241፣ 244 እና 245(1)

    Download here

  • በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት በመጀመሪያ ጨረታ ሽያጭ ላይ ተወዳድሮ አሸናፊ የተባለ ገዥ ዋጋ ከፍሎ ግዥዉን ባለመፈጸሙ ድጋሚ ጨረታ ሲደረግ የሽያጭ ዋጋ ቢቀንስ በሁለተኛዉ እና በአንደኛዉ ጨረታ መካከል ለተፈጠረዉ የዋጋ ልዩነትና ኪሳራ የመክፈል ግዴታ ሁለተኛውን ጨረታ ተወዳድሮ አሸናፊ የሆነው ሰው ላይ የማይወድቅ ስላለመሆኑ 

    የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ./429 

    Download here

  • አንድ ተከሳሽ የቀረበበትን ክስና ማስረጃ በመመርመር ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ መልሱን አዘጋጅቶ እንዲያቀርብ የታዘዘው እና ቀጠሮ የተሰጠው ከ10 ቀን ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከሆነ የተከሳሹን የመከላከልና የመከራከር የመሰማት መብቱን የሚነፍግ በመሆኑ በቂ ጊዜ ተሰጥቶት የመከላከያ መልሱን እና ክርክሩን እንዲያቀርብ መደረግ ያለበት ስለመሆኑ
    ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 37፣
    የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.240[2] 

    Download here

  • የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ስልጣን

    Cassation 15531

  • ግራቀኝ ተከራካሪ ወገኖች በሚያደርጉት ስምምነት መሰረት  አለመግባባታቸውን በኢትዮጵያ መሰረታዊ ህግ (Substantive Law) እንዲሁም በውጪ ሃገር የሥነ-ሥርዓት ህግ መሰረት በሚቋቋም የግልግል ዳኝነት አካል በውጭ ሃገር ለመቋጨት በተስማሙት መሰረት የተቋቋመው የግልግል ጉባኤ የሰጠው ውሳኔ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ታይቶ እንዲታረም የሚቀርብ የሰበር ማመልከቻ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ
    የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3)(ሀ) እና በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 (በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2 እንደተሻሻለ)፤ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 458(ሀ) እና 461(1)(ሀ)  

    Download

  • የአንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት አከራይ የሆነ ሰዉ ላልተከፈለዉ የዉዝፍ ኪራይ ክፍያ አከፋፈል ሲባል ተከራዩ በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት በመጀመሪያ ጨረታ ሽያጭ ላይ ተወዳድሮ አሸናፊ የተባለ ገዥ ዋጋ ከፍሎ ግዥዉን ባለመፈጸሙ ድጋሚ ጨረታ ሲደረግ የሽያጭ ዋጋ ቢቀንስ በሁለተኛዉ እና በአንደኛዉ ጨረታ መካከል ለተፈጠረዉ የዋጋ ልዩነትና ኪሳራ የመክፈል ግዴታ ሁለተኛውን ጨረታ ተወዳድሮ አሸናፊ የሆነው ሰው ላይ የማይወድቅ ስላለመሆኑ 

    Download here

  • አንድ ክርክር ያስነሳ ንብረት በአፈፃፀም  ሂደት በጨረታ ከተሸጠና ገንዘቡም ለፍርድ ባለገንዘብ ከተከፈለ በኃላ በጨረታዉ ሂደት ጨረታዉን ሊያስፈርስ የሚችል ጉድለት ካልተገኘ እንዲሁም ንብረቱ ለ3ኛ ወገን እንዳይተላለፍ የተሰጠ ዕግድ በሕግ አግባብ ያልተመዘገበ መሆኑ ከተረጋገጠ የቀዳሚነት መብትን ለመጠቀም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418 መሰረት የሚቀርብ የመቃወም አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ
    በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418፣426፣445 

    Download here

  • ከሳሽ ወገን ክስ በሚሰማበት ወቅት ያላቀረበው ማስረጃ መኖሩን በበቂ ምክንያት በማስደገፍ ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት ባገኘበት ሁኔታ ተከሳሽ የመከላከያ መልሱን እንዲያሻሽል የሚያቀርበውን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ በተሟላ መልስ ባልተከራከረበት ሁኔታ ተከሳሽ ከሳሽ ባቀረበው ሰነድ ላይ አስተያየቱን በጽሁፍ ብቻ ያቅርብ ብሎ የመደመጥ መብቱ ሊታለፍ የማይገባው ስለመሆኑ
    የፌዴራል ህገ መንግስት አንቀጽ 37 ፤ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ91፤137(1) ፣223፣256 

    Download here

  • ተከራካሪ ወገኖች ጉዳያቸው በሽማግሌዎች እንዲታይ ወደውና ፈቅደው ከተስማሙ በኋላ ሽማግሌዎች የሰጡት ውሳኔ ባለበት ሁኔታ በሕጉ በተዘረጋው ሥርዓት ይግባኝ በመጠየቅ እንዲታረም ከማድረግ በስተቀር አዲስ ክስ ማቅረብ ተገቢ ስላለመሆኑ
    በፍ/ብ/ሕ/ቁ 3325፣የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 244/2/ረ/

    Download here

  • አንድ ተከራካሪ ወገን በፍ/ቤት ፈቃድ ክሱን የተወ እና አዲስ ክስ ባቀረበ ጊዜ በቀረበው አዲስ ክስ ላይ በግራቀኙ ተከራካሪ ወገኖች የቀረቡት እና በፍ/ቤቱ ትዕዛዝ መሠረት የቀረቡ ማስረጃዎች ተመርምረው እና ተመዝነው ውሳኔ የሚሰጥበት እንጂ አስቀድሞ በፍ/ቤት ፈቃድ በተዘጋው መዝገብ ላይ ቀርበው በነበሩ ማስረጃዎች መሠረት ውሳኔ የሚሰጥበት አግባብ ስላለመኖሩ
    የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 278

    Download here

  • አንድ በዉጭ አገር የተሰጠ ፍርድ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ለማስፈጸም በኢትዮጵያ እና ፍርዱን በሰጠዉ ፍርድ ቤት አገር መካከል ይህን አስመልክቶ የተደረገ ስምምነት (bilateral agreement) ባይኖርም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 458 ስር የተመለከቱት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸዉ ከተረጋገጠ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ፍርዱን ተቀብለዉ ማስፈጸም የሚችሉ ስለመሆኑ
    ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 456፣458

    Download

  • download

  • ለአንድ ክስ መሻሻል ወይም ለክርክሩ መለወጥ ቀደም ሲል የቀረበን የክስ ምክንያት በሌላ የክስ ምክንያት በመቀየር ለመሟገት ማቅረብ ነገሩን ይበልጥ የሚያብራራ ወይም ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት የሚረዳ ነው በሚል ክስ እንዲሻሻል የሚፈቀድበት የህግ ምክንያት ስላለመኖሩ
    /በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 91/1/2/

    Download

  • አንድ የመንግስት ሰራተኛ በተከሰሰበት የዲሲፕሊን ጥፋት ምክንያት ከስራ እንዲሰናበት ካልተወሰነበት በስተቀር ከሥራ በታገደበት ወቅት ሳይከፈለው የቀረው ደመወዝ የሚከፈለው ስለመሆኑ
    በፌዴራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 አንቀጽ 72 (4) 

    Download

  • ባንኮች ከሚሰጡት ብድር እና የመያዣ ውል ጋር በተያያዘ የሚነሱ ክርክሮች አዋጅ ቁ. 97/9ዐ”ን” ዓላማ እንዲሁም አዋጁን ለማስፈፀም በባንኮች የሚወጡትን የፎርክሎዥር መመሪያዎችና አግባብነት ያላቸውን ህግጋት ግምት ውስጥ በማስገባት እልባት ማግኘት ያለባቸው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 97/90 አንቀጽ 3 እና 4, አዋጅ ቁ. 216/92

    Cassation Decision no. 16218

  • አንድን ክስ በመጀመሪያ መቃወሚያ ዉድቅ በማድረግ የተሰጠን ዉሳኔ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ከሻረው በኋላ የስር ፍርድ ቤት በፍሬ ጉዳዩ ላይ ተገቢዉን እንዲወስን መመለስ ሲገባው ያን ሳያደርግ ፍሬ ጉዳዩን በተመለከተ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ራሱ የሚሰጠዉ ዉሳኔ ማስረጃን መዝኖ ፍሬ ነገርን ከማረጋገጥ ጋር በተያያዘ ሊፈጠር የሚችለዉን ስህተት ለማሳረም ይግባኝ የማቅረብ መብትን ከማስፋት አንፃር ታይቶ ተፈፃሚነት ሊኖረዉ የሚገባውን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ አንቀፅ 341 ድንጋጌን ትክክለኛ አፈፃፀም ያልተከተለ ስለመሆኑ
    የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ አንቀፅ 341

    download

  • አንድ የመንግስት የንግድ ቤት ኪራይ መብት ከልጅነት ጀምሮ በአውራሼ ዘንድ አድጌያለሁ እንዲሁም የኑዛዜ ወራሽ ነኝ በማለት በዉርስ ሊተላለፍና የንግድ ቤት የኪራይ መብት ተጠቃሚ ሊያደርግ የማይችል ስለመሆኑ
    በአ/አ/ከ/አስ/የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የመንግስት ቤቶች አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 4/2009 አንቀጽ 24 

    Download

  • አንድ የመንግስት የንግድ ቤት ኪራይ መብት ከልጅነት ጀምሮ በአውራሼ ዘንድ አድጌያለሁ እንዲሁም የኑዛዜ ወራሽ ነኝ በማለት በዉርስ ሊተላለፍና የንግድ ቤት የኪራይ መብት ተጠቃሚ ሊያደርግ የማይችል ስለመሆኑ
    በአ/አ/ከ/አስ/የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የመንግስት ቤቶች አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 4/2009 አንቀጽ 24 

    Download