Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • Cassation Decision no. 16455

  • በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዉስጥ የተቋቋሙ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ከሳሽ በመሆን የሚያቀርቧቸዉን ክሶች በተመለከተ የመዳኘት የሥረ ነገር ሥልጣን የከተማ አስተዳደሩ ፍርድ ቤቶች ሥልጣን ሳይሆን የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ስለመሆኑ
    በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 11(1/ለ) እና 14(2)፤የአዲስ አበባ ከተማ ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41(1/ረ)፤በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ቁጥር 46/2004
    /የፌ/ፍ/ቤቶችን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 454/1997 መሰረት በፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀደም ሲል በሰ/መ/ቁጥር 90421 ተሰጥቶ የነበረው የህግ ትርጉም ውሳኔ ተለውጧል፡፡/

    Download

  • አንድን ክርክር በመጀመሪያ ደረጃ ሲሰማ በነበረበት ፍርድ ቤት በከሳሽነትም ሆነ ተከሳሽነት ቁጥራቸው ከአንድ በላይ የሆኑ ተከራካሪዎች በቀረቡበት መዝገብ ላይ በሚሰጥ ውሳኔ ላይ እያንዳንዱ ተከራካሪ ወገን በተናጠል ይግባኝ ያቀረበ እንደሆነ በአንድ በይግባኝም ሆነ በሰበር ችሎት በቀረበ ጉዳይ ላይ በመዝገቡ ላይ ያልቀረቡት ቀድሞ የክርክሩ አካል የነበሩት አካላት በሌላ መዝገብ ላይ ቀርበው ከሆነ ተገቢ ማጣራት እና ክትትል ተደርጎ መዝገቦቹ ተጣምረው እንዲታዩ ማድረግ የሚገባ ስለመሆኑ
    የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 331 

    Download here

  • የአፈፃፀም ችሎት በፍርድ ባለመብትና በፍርድ ባለዕዳ መካከል አንድን ቤት በዓይነት ለመካፈል ስምምነት እንደሌለ በማረጋገጥ በሐራጅ እንዲሸጥ ትዕዛዝ የሰጠ እና ግራቀኙም በቀረቡት ተጫራቾች ሐራጁ እንዲቀጥል በፊርማቸው አረጋግጠው ቤቱ የተሸጠ ከሆነ የሐራጁ የሽያጭ ሥርዓት ተገቢ ባልሆነ መንገድ ወይም በማጭበርበር ተፈጽሟል ለማለት የሚያስችል ስላለመሆኑ 

    በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 445 

    Download here

  • አንድ የመንግስት መስሪያ ቤት ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ መሰረት ተወዳድሮ አሸናፊነቱ ተረጋግጦ ቅጥር የፈፀመ ሰራተኛ ቅጥሩ የቅጥር ስርዓት ለመግዛት የወጣው ህግን ባልተከተለ መንገድ የተፈፀመ መሆኑ ከተረጋገጠ ስህተቱ የቀጣሪው መንግስት መስሪያ ቤት ቢሆን እንኳን ቅጥሩ ፀንቶ የሚቆይበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ
    የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ 56/2010 አንቀፅ 94

    Download

  • በሐሰት ማስረጃ የተሰጠ ፍርድ እንዲነሳ የሚቀርብ ጥያቄ በዳግም ዳኝነት ጥያቄ ቀርቦ ከሚስተናገድ በቀር መደበኛ(አዲስ) ክስ በማቅረብ ውሳኔው እንዲሻር የሚጠየቅበት የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ
    የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/ 6

    Download

  • አንድ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የሥር ፍ/ቤት ውሳኔን በመሻር ጉዳዩ በድጋሚ እንዲታይ ነጥብ ለይቶ እስከመለሰ ድረስ የሥር ፍ/ቤቱ በበላይ ፍ/ቤቱ  ትዕዛዝ ወይም መመሪያ መሰረት ግራ ቀኝ ተካራካሪ ወገኖችን በማከራከር ፣ በመስማት፣ ተገቢውን ጭብጥ በመመስረት እና በማስረጃ በማጣራት ዉሳኔ የመስጠት ኃላፊነት ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.246-249፣341(1)    

    download

  • በፍርድ ክልከላ የተደረገበት ሰው ክልከላው እንዲወሰን ያደረጉት ምክንያቶች በቀሩ ጊዜና የተከለከለው ሰው ንብረቱን ለመምራትና ለማስተዳደር የሚችል የሆነ እንደሆነ በተደረገው ክልከላ ምክንያት ሌላ አዲስ ክስ ማቅረብ የማይችል ቢሆንም የተደረገው ክልከላ እንዲነሳለት አቤቱታ ማቅረብ የሚችል ስለመሆኑ
    በፍ/ህግ ቁጥር 351(1) ፣377፣378

    Download

  • አንድ የውርስ ንብረት ክፍፍል ጥያቄ ድርሻን መሰረት በማድረግ የቀረበ ሲሆን አመልካቹ በድርሻው ተመስርቶ ዳኝነት እስከጠየቀ ድረስ ከድርሻው ውጪ ያለውን ግምት መሰረት አድርጎ ዳኝነት እንዲከፍል የሚደረግበት የህግ አግባብ ስላለመኖሩ እና የውርስ ንብረቱ ጠቅላላ ግምት የፍርድ ቤቱን የስረ ነገር ስልጣን ለመወሰን የግድ የሚባልበት የሕግ መሰረት የሌለ ስለመሆኑና
    በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 14 ፣ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 17 እና 225

    Download

  • ተከራካሪ ወገኖች የሚያቀርቡትን ክርክር በቅን ልቦና እና እውነትነት ባለው ማስረጃ የማይከራከሩ በሆነ ጊዜ ፍ/ቤቶች የቀረበላቸው ነገር እውነት መሆኑን ባልተረዱ እና ፍፁም ድብቅ በሆነባቸው ጊዜ እውነት ላይ ለመድረስ  በሀሰተኛ ማስረጃ እና በሃሰተኛ ተከራካሪዎች ቅን ልቦና መጉደል ምክንያት እውነትን የያዙ ሰዎች ላይ ያልተገባ ፍርድ እንዳይሠጥ ተገቢውን ማጣራት በማድረግ ትክክለኛ ነው ያሉትን ውሣኔ መስጠት ያለባቸው ስለመሆኑ

    Download here

  • በይግባኝ ደረጃ ግራ ቀኝ ወገኖች ለክርክር በተቀጠረበት ቀን ባለመቅረባቸው ተዘግቶ የነበረ መዝገብ በይግባኝ ባዩ አመልካችነት ሲከፈት መልስ ሰጪው እንዲያውቀው ሳይደረግ በሌለበት ውሳኔ መስጠት እና መልስ ሰጪው በሌለበት የተሰጠው ውሳኔ እንዲነሳለት የሚያቀርበውን አቤቱታ በቂ ባልሆነ ምክንያት ውድቅ ማድረግ አግባብነት የሌለው ስለመሆኑ
    የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ አንቀጽ 233

    Download

  • በፍርድ ቤት ከቀረበ ክርክር ጋር በተያያዘ ከአስተዳደር ክፍል የሚሰጥ መግለጫ እንደየአግባብነቱ ለፍርድ ቤቱ ከቀረቡት ሌሎች የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች ይዘት ጋር ተገናዝቦ የሚወሰድ እንጂ በራሱ የመጨረሻ ማስረጃ ስላለመሆኑ  

    Download

  • ከመደበኛ ፍ/ቤት ውጭ አንድን ጉዳይ የማየት የዳኝነት ስልጣን የተሰጠው አካል ጉዳዩን ማየት እንደማይቻል ገልጾ ከመለሰው ጉዳዩን የማየት ስልጣን ለሌላ አካል ተሰጥቷል የሚል ክርክር እስካልቀረበበት ድረስ መደበኛ ፍ/ቤቱ ይህን ጉዳይ ማየት አልችልም በሚል መመለስ የማይቻል ስለመሆኑ

    የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ በኤጀንሲው የሚታይ ጉዳይ አይደለም በሚል አረጋግጦ የመለሰው ጉዳይ በስልጣኑ ላይ ሌላ ክርክር እስካልቀረበበት ድረሰ ፍ/ቤቶች ተቀብለው ማስተናገድ ያለባቸው ስለመሆኑ 

    የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀፅ 37፣78(2) እና 79(1) 

    download

  •  በህግ ግምት የሚሸፇንን የፌሬ ነገር ክርክር በሚመሇከት ተከራካሪ ወገኖች ባያነሱትም ፌ/ቤቱ የህግ ግምቱን ተፇፃሚ

    ስሇማዴረጉ
    የፌ/ብ/ህ/ቁ.1856 2ዏ24, የፌ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 89

    Cassation decison no. 17608

    '

  • የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚ/ር አጥንቶ ስራ ላይ ባዋለው በነጥብ የስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ዘዴ/JEG/ የመንግስት ሰራተኞች ድልድል አፈጻጸም መመሪያ መሰረት ለአንድ የሥራ መደብ የሚያስፈልገው የትምህርት ዝግጅት በግልጽ ተቀምጦ እያለ ተጨማሪ የትምሕርት ዓይነትን አካቶ ሰራተኞችን ማወዳደር የድልድል መመሪያውን የሚጥስ ስለመሆኑ 

    Download

  • አንድ ተከሳሽ ጥፋተኛ ቢባል በቀላል እሥራት፤ ከ12 ዓመት በታች በሆነ ጽኑ እሥራት ወይም ከአሥራ ሁለት ዓመት በላይ በሆነ ጽኑ እሥራት ሊቀጣ የሚችል በመሆኑ ተመራጭ የሚሆነው የፍርድ ሂደት ተከሳሹ በተከሰሰበት ድንጋጌ የተቀመጠው ከፍተኛ ቅጣት ሊቀጣ ይችላል ብሎ ከወዲሁ በማሰብ ጉዳዩን በሌለበት እንዲታይ ማድረግ ሳይሆን የተከሳሽ በችሎት ተገኝቶ የመከራከር መብት ከሚጣስ ይልቅ ተከሳሽ እስኪገኝ ድረስ የፍርድ ሂደቱ እንዳይካሄድ በማድረግ ስለመሆኑ
    የኢፌዲሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 20/4፣ ዓለም ዓቀፍ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት አንቀጽ 14፣የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 162(2) 

    Download

  • የአንድ ሃገር ፍ/ቤት በጉዳዩ ላይ ብሔራዊ የዳኝነት(judicial jurisdiction) ስልጣን አለው ለማለት ሊወሰዱ ስለሚገባቸው ዝርዝር ነጥቦች

    Download Cassation Decision

  • ውል ይጽደቅልኝ በሚል ለፍ/ቤት የሚቀርብ አቤቱታ የክስ ምክንያት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 231/1//ሀ/

    Cassation Decision no. 18380

  • በውርስ ሃብት ክፍፍል ላይ ተወላጅ የሆነ ሰው ከሩብ በላይ ጉዳት የደረሰበት እንደሆነ ክፍፍሉ እንዲቀር ለመጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ. 11/22,913,1060,1037-1051,942

    Download Cassation Decision

  • Download Cassation Decision

    በሃይማኖት ተቋም ውስጥ መንፈሳዊ(ሃይማኖታዊ) አገልግሎት የሚሰጥ ሰራተኛ ከተቋሙ ጋር ያለው የስራ ግንኙነት በአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ የሚሸፈን ስላለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96