በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 394/1፣ ቁጥር 404 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት በፍርድ አፈጻጸም መዝገብ ላይ ንብረት ለማስከበር በተሰጠ ትእዛዝ የፍርድ ባለእዳን የታክስ ከፋይ ንብረት ያስከበሩ የፍርድ ባለመብቶች ከሌሎች የቀደምትነት መብት አለኝ ብለው ለመጠየቅ እንደሚችሉ የተደነገገ ባለመሆኑ ንብረቱ ከመከበሩ ወይም ከመያዙ በፊት በንብረቱ ላይ መብት የነበራቸዉና በክርክሩ ዉስጥ የሌሉ ሦስተኛ ወገኖች በሕግ፣በፍርድ ወይም በዉል ንብረቶቹ ላይ ያቋቋሙት የቀደምትነት መብት የማይነካ ስለመሆኑ 

የፍርድ ባለእዳን ታክስ ከፋይ ንብረት ካስከበረ የፍርድ ባለመብት ይልቅ በሕግ የቀደምትነት ጥበቃ መብት የተሰጠዉ ታክስ ሰብሳቢ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት በታክስ ህግ መሰረት በታክስ ከፋዩ ሀብት ላይ ከፍርድ ባለመብቱ የቀደምትነት መብት ያለው በመሆኑ ከፍርድ ባለመብቱ ቀድሞ ንብረቶቹን ያስከበረ ስለመሆኑ ማስረጃ እንዲያቀርብ ሊጠየቅ የሚችልበት የሕግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ 

የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 418 

Download