 ከመሬት ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ መብቶች እና ግዴታዎች የሚመሩት በንብረት ህግ አጠቃላይ መርሆዎች በመሆኑ የከተማም ሆነ የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀምን አስመልክቶ የሚወጡ ህጎች/አዋጆች በንብረት ህግ ማዕቀፍ ዉስጥ የሚመደቡ በመሆኑ ከንብረት ጋር በተገናኘ ያሉ ጽንሰ ሃሳቦች፣ ህጎች እና መርሆዎች ከመሬት ጋር በተያያዘ ለሚቀርብ ክርክር እንደየአግባብነታቸዉ ተፈፃሚነት ያላቸው ስለመሆኑ 

 አንድን ንብረት አስመልክቶ የሚቀርበዉን ክስ ተከትሎ ንብረትን የሚመለከት የህግ ክፍል ተፈፃሚ የሚሆነዉ ከሳሽ ክሱን ያቀረበዉ ንብረቱን በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ በእጁ ካደረገ በኋላ በንብረቱ ላይ ያለዉ መብት እንዲከበርለት የተረጋገጠ ሲሆን በመሆኑ የተጠየቀዉ ዳኝነት ንብረትን የሚመለከት መሆኑ ብቻዉን ጉዳዩን የንብረት ክርክር የማያደርገው ስለመሆኑ 

Download