Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 2ዐ8 መሠረት በሥር ፍ/ቤት የተደረገ እርማትን መነሻ በማድረግ የይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት አስቀድሞ የሰጠውን ውሣኔ ለመለወጥ የሚያስችለው የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 208 209 320 (1) ,348(1)

    Download Cassation Decision

  • የንብረት ክፍፍል እንዲደረግ በፍርድ ቤት ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በውሳኔው ወቅት ንብረቱን በእጁ አድርጐ የሚገኘው ወገን የንብረቱን ስመ ሐብት ወደ ሌላ ሦስተኛ ወገን አዛውሮ ሲገኝ ፍርድ ቤቶች ሊከተሉት ስለሚገባው አካሔድ

    Download Cassation Decision

  • ለረጅም ጊዜ በመንግስት ቁጥጥር ሥር የነበረ ቤትን ይለቀቅልኝ በሚል አቤቱታ የሚያቀርብ ወገን ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 47/67 የተፈቀደለት ስለመሆኑ ወይንም ከአዋጅ ውጪ ተወስዶብኛል የሚል ከሆነም ለሚመለከተው አካል ጥያቄውን አቅርቦ ውሳኔ አግኝቶ ባለመብትነቱን ሳያረጋግጥ የሚያቀርበው ክስ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 47/67

    Download Cassation Decision

  • በክረምት ወቅት የማስተማር ሥራ እንዲሠራ የሚያዝ ግልፅ ደንብ ወይም መመሪያ የሌለ እንደሆነ ወይም አስተማሪው በክረምት ወራት ለማስተማር የገባው የውል ግዴታ (ስምምነት) በሌለ ጊዜ በክረምት ወቅት ሥራን ለመስራት ፈቃደኛ አልሆነም በሚል ከሥራ ሊሰናበት የማይችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 13(1)

    Download Cassation Decision

  • በትዳር ወቅት የተወሰደ ብድር የአንደኛው ተጋቢ ፈቃድ የሌለበት ቢሆንም ፈቃዱን ያልሰጠው ተጋቢ የብድር ስምምነቱ እንዲፈርስ ያላደረገ እንደሆነ ወይም ደግሞ ለትዳር ጥቅም አለመዋሉን ማስረዳት ያልቻለ ከሆነ ለትዳር ጥቅም እንደዋለ የህግ ግምት የሚወሰድ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 68(መ)

    Download Cassation Decision

  • ፍ/ቤቶች የቀረበላቸው አቤቱታ የክስ ምክንያት አለው ወይም የለውም ብሎ ለመወሰን በክስ ላይ የተገለፀው ነገር ቢረጋገጥ ከሳሽ የሆነው ወገን የጠየቀውን ዳኝነት ለማግኘት ህግ ይፈቅድለታል ወይስ አይፈቅድለትም የሚለውን ጥያቄ መመርመር ያለባቸው ስለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • በተጭበረበረ መንገድ ወራሽነትን አሳውጆ የውርስ ንብረት አካል የሆነን ቤት ስመ ሃብት ወደ ራሱ አዙሮ የሚገኝ ሰው ጋር የሽያጭ ውል በተደረገ ጊዜ የሸያጭ ውሉ እንዲፈርስ በሚል ትክክለኛ ወራሾች የሚያቀርቡት ጥያቄ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ የፍብ/ህ/ቁ. 2882 2884 997

    Download Cassation Decision

  • ፍ/ቤቶች ለቀረበላቸው ክስ ምክንያት የሆነው ነገር መቋረጡን ወይም ጨርሶ መቅረቱን በክሱ ሂደት በማንኛውም ደረጃ በቂ በሆነ ማስረጃ በተገነዘቡ ጊዜ ክሱን ሊዘጉት የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 280

    Download Cassation Decision

  • የወለድ አግድ ውል ህጋዊ ነው ሊባል የሚችለው የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ መቋቋምን የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን በመከተል የተደረገ እንደሆነ ስለመሆኑና በዚህ መሰረት ያልተደረገ መሆኑ ውሉን ፈራሽ ሊያደርገው የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3118,3045,3052

    Download Cassation Decision

  • ከእጅ በእጅ ሽያጭ ጋር በተያያዘ ገዢ የሸያጩን ዋጋ የከፈለበትን ደረሰኝ ይዞ መገኘቱ የገዛውን ንብረት እንደተረከበ የሚያሳይ የመጨረሻ (conclusive) ማስረጃ ነው ሊባል የማይቻል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2266 2278(1) እና (2)

    Download Cassation Decision

  • አንድ ወንድ ሁለት ሚስቶች ጋር ተጋብቶ በሚገኝ ጊዜ የንብረት ክፍፍል ሊደረግ የሚችልበት አግባብ የፌዴራል የተሻቫለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/92 አንቀጽ 102(1),86(1),62(1),63(1) የአማራ ብ/ክ/መ/የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 113(1),97(1),73(1),74(1)

    Download Cassation Decision

  • አንድ ወንድ ሁለት ሚስቶች ጋር ተጋብቶ በሚገኝ ጊዜ የንብረት ክፍፍል ሊደረግ የሚችልበት አግባብ የፌዴራል የተሻቫለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/92 አንቀጽ 102(1),86(1),62(1),63(1) የአማራ ብ/ክ/መ/የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 113(1),97(1),73(1),74(1)

    Download Cassation Decision

  • ፍ/ቤት ተከራካሪ ወገኖች ወለድን አስመልክቶ በውላቸው ካመለከቱት ሃሳብ ውጪ የራሱን ስሌት መሠረት በማድረግ ውሣኔ መስጠት ስላለመቻሉ የፍ/ብ/ህ/ቁ/. 1731 2478

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል ጉዳይ የቀረበ ክስ በዐቃቤ ህግ ምስክሮች ተሟልቶ አለመቅረብ የከሳሽ መዝገቡን የማንቀሳቀስ መብት ተጠብቆ መዘጋት በቀረበው ወንጀል ላይ ተፈፃሚ የሚሆነውን የይርጋ ጊዜ ተግባራዊ ከመሆን የሚያግደው ስላለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • የምትክ ወራሽነት ተጠቃሚዎችን ስለመለየት የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 842,843,844(3)

    Download Cassation Decision

  • በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ተከስሶ ጥፋተኛ መሆኑ የተረጋገጠ ተከሳሽ ስለሚጠየቅበት አግባብ የተመሰረተበት ክስ በዓቃቤ ሕግ በኩል እንደክሱ አመሰራረት ያልተረጋገጠበት ቢሆንም ተከሳሹ የቀረበው ማስረጃ ከቀረበበት ክስ ባነሰ የወንጀል ድርጊት የሚያስጠይቅ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ተከሳሹ በነፃ እንዲሰናበት ሊደረግ የሚችልበት አግባብ የማይኖር /የሌለ/ ስለመሆኑ በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ተከስሶ ጥፋተኛ መሆኑ የተረጋገጠ ተከሳሽ ስለሚጠየቅበት አግባብ የተመሰረተበት ክስ በዓቃቤ ሕግ በኩል እንደክሱ አመሰራረት ያልተረጋገጠበት ቢሆንም ተከሳሹ የቀረበው ማስረጃ ከቀረበበት ክስ ባነሰ የወንጀል ድርጊት የሚያስጠይቅ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ተከሳሹ በነፃ እንዲሰናበት ሊደረግ የሚችልበት አግባብ የማይኖር /የሌለ/ ስለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • ለተወሰነ ጊዜም ሆነ ላልተወሰነ ጊዜ የተቀጠረ ሠራተኛ ከውል ውጭ በሆነ ግንኙነት በሥራ ወቅት በሌሎች ሰዎች ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት አሠሪ ኃላፊነት ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2130 2131 2132

    Download Cassation Decision

  • ከሥራ ክርክር ጋር በተያያዘ አሰሪ ሠራተኛው የፈፀመውን ድርጊት መሠረት አድርጐ ለማሰናበት የሚችለው የሥራ ውሉን ለማቋረጥ ምክንያት የሆነው ነገር መከሰቱን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠሩ ሰላሳ ቀናት ውስጥ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 27(3)

    Download Cassation Decision

  • በሸሪአ ፍ/ቤት በሚካሄድ ክርክር ላይ ጣልቃ ገብቶ መከራከር በፍ/ቤቱ ለመዳኘት ስምምነትን እንደመስጠት የሚያስቆጥር ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 188(92) አንቀፅ 5(1)

    Download Cassation Decision

  • የልጆች ቀለብ አከፋፈል ሁኔታ ጋር በተያያዘ ክፍያ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችልበት አግባብ

    Download Cassation Decision