Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • ተከራካሪ ወገኖች ጉዳያቸውን በእርቅ ለመጨረስ የተሰማሙና ይሄንኑም ስምምነት ለፍ/ቤት በማቅረብ ያስፀደቁ በሆነ ጊዜ ስምምነቱ እንደ ፍርድ ቤት ውሣኔ ተቆጥሮ መፈፀም ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 277

    Download Cassation Decision

  • አስቀድሞ የተደረገ ነገር ግን ባለመታደሱ ምክንያት የተቋረጠ (ያበቃ)ን የመድን ውል መሠረት በማድረግ ሊጠየቅ የሚችል የጉዳት ካሣ ስላለመኖሩ የንግድ ህግ ቁ. 666(2) እና (3)

    Download Cassation Decision

  • የግልግል ዳኝነት ጉባኤ እንደ ፍ/ቤት የዳኝነት አካሄድ ሁልጊዜ ጥብቅ የሆነ የሙግት ሥርዓትን ተከትሎ ጉዳዩን ማየት የሌለበት ስለመሆኑ የግልግል ጉባኤ ጉዳዩን ለማየት ሊከፈል የሚገባውን የገንዘብ መጠን በተመለከተ ተገቢ ነው ብሎ ያመነበትን ያህል ሊወስን ስለመቻሉ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 318/5/, 317/1/ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 3345

    Download Cassation Decision

  • ወደ ሥራ እንዲመለስ ፍርድ የተሰጠ እንደሆነና በአሰሪው ችግርም ሆነ በሠራተኛው ፍላጐት በፍርዱ መሠረት ወደ ሥራ ለመመለስ ሠራተኛው ያልፈለገ ከሆነ ሠራተኛው የአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ በምትክነት በሰጠው መብት መሠረት በመመለሱ ፈንታ ካሣ እንዲከፈለው አፈፃፀሙን ለያዘው ችሎት ጥያቄውን ባቀረበ ጊዜ ሊስተናገድ የሚገባው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 43(3)

    Download Cassation Decision

  • መጥሪያ በጋዜጣ ጥሪ ሊደረግ የሚገባው ሌሎች አግባብነት ያላቸው የመጥሪያ አላላክ መንገዶች ቅደም ተከተላቸውን በጠበቀ መልኩ ከተከናወኑ በኋላ ስለመሆኑ መጥሪያ በአግባቡ ደርሷል ለማለት የሚላክለት ሰው ስም በተሟላ ሁኔታ ተገልጾ መላክ ያለበት ስለመሆኑ መጥሪያ በህጉ አግባብ እንዲደርሰው ሳይደረግ በሌለበት ጉዳዩ እንዲታይ ትዕዛዝ የተሰጠበት ወገን ትዕዛዙ እንዲነሳለት የሚያቀርበው አቤቱታ ተገቢነት ያለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 94-110, 7870/ሀ

    Download Cassation Decision

  • ኑዛዜ መኖሩን የማስረዳት ሸክም (ግዴታ) የተጠቃሚዎች ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 896,897

    Download Cassation Decision

  • በአሰሪና ሠራተኛ ህጉ ‹‹… ውሉ የሚቋረጥበት ምክንያት መከሰቱን ካወቀበት…›› በሚል የተመለከተው ሃረግ ሊተረጐም የሚችልበት አግባብ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 27(3)

    Download Cassation Decision

  • በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 418 አቤቱታ እንዲያቀርብ ተፈቅዶለት ክርክር ተካሂዶ ውሣኔ የተሰጠበት ወገን በድጋሚ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 447 ”ን” መሰረት በማድረግ የሚያቀርበው አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 418, 447, 354

    Download Cassation Decision

  • ለዋስትና የተያዘ ገንዘብን የአስያዡን ማንነትን ማረጋገጥ እስከተቻለ ድረስ ገንዘቡን ያስያዘበት ደረሰኝ ኮፒን ያቀረበ እንኳን ቢሆን የተያዘው ገንዘብ መመለስ ያለበት ስለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • በዋናው ክርክር ላይ በተሰጠ ፍርድ መብቱ የተነካበት ሰው በፍርድ አፈፃፀም ወቅት መብቱ ከተነካበት ሰው በተለየ ሥነ ሥርዓት ተቃውሞ ማቅረብ የሚገባው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358, 418, 419

    Download Cassation Decision

  • ከወንጀል ጉዳይ ጋር በተያያዘ ጥፋተኛ የተባለ ተከሳሽ የዘወትር ፀባይ መልካም የነበረ መሆኑ በተናጠል (በራሱ) ቅጣትን ለማቅለል የሚያስችል ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁጥር 82(1) (ሀ)

    Download Cassation Decision

  • በፍ/ቤቶች ጣልቃ ገብቶ እንዲከራከር ትዕዛዝ የተሰጠው ተከራካሪ ወገን ጥሪ ተልኮለት ቀርቦ መልሱን አልሰጠም በሚል ምክንያት ከክርክሩ ውጪ እንዲሆን የሚሰጥ ትዕዛዝ በክርክሩ ውስጥ ያሉ ሌሎች ወገኖችን መብት የሚያጣብብና የሥነ-ሥርዓት ህግን የሚጥስ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 70, 41/3/, 199

    Download Cassation Decision

  • እቃን ለመግዛት በጨረታ ማስታወቂያ ያወጣ ድርጅት ተወዳዳሪዎች በጨረታ ላይ ከተነገረው የተለየን ዕቃ በማቅረብ ከተወዳደሩ በኋላ ድርጅቱ ተወዳዳሪ የሆነው አካል በጨረታ ሰነዱ ላይ ሞልቶ ያቀረበውን እቃ መሰረት በማድረግ ውል የተዋዋለ እንደሆነ ይህንኑ ውል ለመፈፀም የሚገደድ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1695/2/

    Download Cassation Decision

  • የንግድ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ የሆነ ሰው የድርጅቱን አስተዳደራዊ ሥራ ለሌላ ሰው የወከለ መሆኑ ድርጅቱ ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ግብይት በመፈፀም ወንጀል ጥፋተኛ በተባለ ጊዜ ከሚቀርብበት የወንጀል ተጠያቂነት ነፃ የማያደርገው ስለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • ክስ ለመስማት በተቀጠረበት ዕለት ለመቅረብ ያልቻለው በቂ ሊባል በሚችል እክል /ችግር/ ምክንያት መሆኑን ያስረዳ ተከሳሽ በሌለበት ጉዳዩ እንዲታይ በሚል የተሰጠው ትዕዛዝ እንዲነሳለት የሚያቀርበው አቤቱታ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ “በቂ ምክንያት” በሚል የሰፈረው ሃረግ ሊተረጐም የሚገባው ተከሳሹ ቀና ልቦና ያለው መሆኑንና የተለያዩ አግባብነት ያላቸው ነባራዊ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ስለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • ክስ ለመስማት በተቀጠረበት ዕለት ለመቅረብ ያልቻለው በቂ ሊባል በሚችል እክል /ችግር/ ምክንያት መሆኑን ያስረዳ ተከሳሽ በሌለበት ጉዳዩ እንዲታይ በሚል የተሰጠው ትዕዛዝ እንዲነሳለት የሚያቀርበው አቤቱታ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ “በቂ ምክንያት” በሚል የሰፈረው ሃረግ ሊተረጐም የሚገባው ተከሳሹ ቀና ልቦና ያለው መሆኑንና የተለያዩ አግባብነት ያላቸው ነባራዊ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ስለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • በባህር ላይ እቃ አመላላሽ በእቃዎች ላይ ለደረሰ ጉዳት በኃላፊነት ሊጠየቅ ስለሚችልበት አግባብ፣ በባህር ላይ እቃን ለማመላለስ የውል ግዴታ የገባ ወገን ከእቃዎቹ መጐዳት ጋር በተያያዘ ስላለበት የኃላፊነት አድማስና ከኃላፊነት ነፃ ሊደረግ የሚችልበት አግባብ የባህር ህግ ቁ.196,138,205,197,180(3)

    Download Cassation Decision

  • በባህር ላይ እቃ አመላላሽ በእቃዎች ላይ ለደረሰ ጉዳት በኃላፊነት ሊጠየቅ ስለሚችልበት አግባብ፣ በባህር ላይ እቃን ለማመላለስ የውል ግዴታ የገባ ወገን ከእቃዎቹ መጐዳት ጋር በተያያዘ ስላለበት የኃላፊነት አድማስና ከኃላፊነት ነፃ ሊደረግ የሚችልበት አግባብ የባህር ህግ ቁ.196,138,205,197,180(3)

    Download Cassation Decision

  • አግባብነት ካለው የመንግስት አካል ፈቃድ ሳይኖር የከርሰ ምድር ቁፋሮ ሥራን ለመስራት የሚደረግ ውል ህጋዊና አስገዳጅ ሊሆን የማይችል ስለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • በማህበር አባላት ስምምነት የሚወጣ ደንብን አስመልክቶ በማህበሩ አባላት መካከል ብሎም በማህበሩ እና በአባላት መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን እልባት ለመስጠት በፍትሐብሔር ህጉ ውስጥ ስለ ውሎች በጠቅላላው የተመለከቱት ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ሊሆኑ የሚችሉ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1676/1/

    Download Cassation Decision