Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • ተከራካሪ ወገኖች በቅድሚያ ሊያቀርቧቸው ሲችሉ ሆነ ብለው ወይም በቸልተኝነት ያላቀረቧቸውን ማስረጃዎች በክርክር ሂደት ሁሉ እያንጠባጠቡ ሊያቀረቡ ወይም የማስረጃ ማሰባሰብ ሥራውን ፍርድ ቤት እንዲያከናውን ሊጠይቁ የሚችሉበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣  በፍ/ቤት እገዛ ማስረጃ የሚቀርበው ተከራካሪ ወገን አጠቃቅሎ ማቅረብ የማይችል ስለመሆኑ በቅድሚያ ሲረጋገጥ ስለመሆኑና ፍ/ቤቱ የተጠየቀው ማስረጃ ለተያዘው ጉዳይ ያለውን አግባብነት በተመለከተ የተቀበለው እንደሆነ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 234(1)

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ተከሣሽ ላይ የሚወሰነው የእስራት ቅጣት አፈፃፀም እንዲገደብ ለማድረግ ስለማይችልባቸው ሁኔታዎች፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 194(1) እና (2)¸190¸192

    Download Cassation Decision

  • አንድን ጉዳይ ለማየት በህግ ስልጣን በሌለው ፍ/ቤት ታይቶ የተሰጠ ውሣኔ በይግባኝ ታይቶ እንዲታረም ካልደተረገ በቀር በጉዳዩ ላይ አስገዳጅነት ያለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 212

    Download Cassation Decision

  • አንድን የተሰጠ ፍርድ ከማስፈፀም ጋር በተገናኘ የአፈፃፀም ስልጣን መሰረቱ ፍርዱን መስጠት ወይም ፍርዱን በሰጠው ፍርድ ቤት ፍርዱን ለማስፈፀም የሚያስችል ውክልና ማግኘት እንጂ የፍርድ ባለዕዳውን ወይም ባለመብቱ የሚኖርበት ክልል (ከተማ) ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 378

    Download Cassation Decision

  • ይርጋ በተመለከተ የሚቀርብ መቃወሚያ ከመልስ ጋር መቅረብ ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 234ሐእና 244ሠ

    Download Cassation Decision

  • አንድ ስምምነት በፍ/ቤት ሊፀድቅ የሚችለው ጉዳዩ ስልጣን ባለው ፍ/ቤት በመታየት ሂደት ላይ እያለ ተከራካሪ ወገኖች ጉዳዩን በስምምነት የጨረሱ መሆኑን ገልፀው ይኼው ስምምነት ለህግና ለሞራል ተቃራኒ ያለመሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ፣  ከፍርድ ቤት ውጪ በሚደረግ እርቅ ወይም ግልግል መሰረት ያለመግባባትን ያስቀሩ ወይም ለጉዳያቸው እልባት ያገኙ ሰዎች የእርቁን ወይም የግልግሉን ስምምነት በፍርድ ቤት ማስመዝገብ ወይም ማስፀደቅ የማያስፈልጋቸው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 277 የፍ/ብ/ህ/ቁ. 3312 እና 3324

    Download Cassation Decision

  • የአንድ እምነት ወይም ሐይማኖት ተከታይ ወይም አማኝ በመሆን በሐይማኖታዊ ተቋሙ ውስጥ የመቃብር ቤት ገንብቻለሁና የቤቱን ግምት ይከፈለኝ በሚል ከሚቀርብ ጥያቄ ጋር በተገናኘ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1179 ድንጋጌ ተፈፃሚ ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1179 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 11,27 (1-3) UDHR-Art. 18 ICCPR.Art. 18(1)

    Download Cassation Decision

  • ፍርድ ቤቶች ከሣሽ በክሱ ገልፆ በትክክል ዳኝነት የጠየቀበት ጉዳይ በቤት ላይ ያለውን የባለሀብትነት መብት ለማስከበርና የመፋለም ክስ ሆኖ እያለ ክሱ የቀረበው በአዋጅ የተወረሰ ቤት ወይም ከአዋጅ ውጪ በባለስልጣን ቃል ትእዛዝ ወይም በቀላጤ የተወሰደን ቤት ለማስመለለስ ነው በሚል ጉዳዩን የማየት ስልጣን የለኝም በማለት የሚሰጡት ውሣኔ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 47/67 የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2257

    Download Cassation Decision

  •  በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 418 መሠረት የሚቀርብ አቤቱታ መደበኛውን የሙግት ሥነ- ሥርዓት ተከትሎ መከናወን ያለበት ስለመሆኑ፣  በፍርድ አፈፃፀም ደረጃ ንብረት እንዳይያዝ ወይም እንዳይከበር በሚል የመቃወሚያ አቤቱታ በቀረበ ግዜ ጉዳዩን የያዘው የአፈፃፀም ችሎት በንብረቱ ላይ ተቀዳሚ መብት አለኝ በሚል የቀረበውን የመቃወም አቤቱታ በመደበኛው የሙግት ሥነ-ሥርዓት ሂደት ክርክሩን በማስተናገድ ንብረቱ እንዲያዝ ወይም እንዲከበር የሚያደርግ ህጋዊና በቂ ምክንያት መኖር ያለመኖሩን በማስረጃ በማጣራት ለጉዳዩ እልባት መስጠት ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 418, 419, 421

    Download Cassation Decision

  • ተከራካሪ ወገኖች በአንድ የሰነድ ማስረጃ ላይ የተመለከተን ፊርማ የማን ስለመሆኑ በሚመለከተው የመንግስት አካል ተጣርቶ ውጤቱ ከቀረበና ከታወቀ በኋላ ሰነዱ በውጭ አገር ተመርምሮ ውጤቱ እንዲታወቅ በማለት የሚያቀርቡት ጥያቄ በህግ አግባብ አጥጋቢና አሣማኝ ምክንያትን በመጥቀስና በማስረጃ አስደግፈው ያላቀረቡ እንደሆነ ጥያቄው ተቀባይነት ሊኖረው የማይቻል ስለመሆኑ፣  የፍ/ቤት የተሰጠ ትእዛዘ /ውሣኔ/ መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት የሚቻለው በተከራካሪ ወገኖች ፍትህ የማግኘት መብት ላይ መሠረታዊ ለውጥ የሚያስከትል እንደሆነ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2008, 2007, 2001, 2005

    Download Cassation Decision

  • በአሠሪው ንብረት ላይ ጉዳት በማድረሱ ያለማስጠንቀቂያ ከሥራ የተሰናበተ ሠራተኛ ጉዳቱን ያደረስኩት በሥራ መደራረብ እና ከልምድ ማነስ ነው የሚል ምክንያት አቅርቦ የተከራከረ መሆኑ ስንብቱን ህገ ወጥ ነው ለማለት የሚያበቃ (የሚያስችል) ስላለመሆኑ፣አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 27(1)(ሸ), 13(3)

    Download Cassation Decision

  • የንግድ ሥራ ፈቃድ ኖሮት ነገረ ግን በህግ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ፈቃዱ ሳይታደስ በንግድ ሥራ ላይ ተሰማርቶ የተገኘ ሰው የፀና የንግድ ሥራ ፈቃድ እንደሌለው ተቆጥሮ በወንጀል ኃላፊነት ጥፋተኛ ተደርጐ ሊያስቀጣው የሚችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 686/2002 አንቀጽ 2(10), 36, 60(1)

    Download Cassation Decision

  • የመቃወም አቤቱታ የሚመራው በመደበኛው የክርክር አመራር ሰርዓት ስለመሆኑ፡- - የመቃወም አቤቱታን የሚሰማው ፍ/ቤት ስላለው ስልጣን፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 222፣223፣234፣358፣359፣360(1) እና(2)

    Download Cassation Decision

  • በአንድ የቀረበ ክስ በተከሣሽነት የተሰየመ ወገን በከሳሽ ከቀረበበት ክስ ጋር በተገናኘ ክስ በቀረበበት ንብረት (ጉዳይ) ጋር በተያያዘ የሚያቀርበው የዳኝነት ጥያቄ በህጉ አግባብ የተከሣሽ ከሣሽነት ክሱን ተገቢውን ዳኝነት በመክፈል ያቀረበ ካልሆነ በስተቀር ዳኝነት ሊሰጥ የማይችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 234(1) (ረ)(ሠ), 215(2), 235(2)

    Download Cassation Decision

  •  ከሣሽ የሆነ ወገን የሚያቀርበውን የዳኝነት ጥያቄ አይነትና መጠኑን በክሱ ማመልከቻ በግልጽ በማስፈር ማቅረብ ያለበት ስለመሆኑ፣  ተከራካሪ የሆኑ ወገኖች በህግ የተፈቀደን መፍትሔ ለማግኘት በግልጽ ዳኝነት መጠየቅ የሚገባቸው ስለመሆኑ፣  የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 241 ድንጋጌ መሠረታዊ ዓላማ ተከራካሪ ወገኖች በጽሁፍ ያቀረቡት ክርክር ለማብራራት እና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 246-248 መሠረት ጭብጥ ለመመስረት እንዲያግዝ እንጂ በጽሁፍ ማመልከቻ ላይ ያልሰፈረን የዳኝነት ጥያቄ ተከራካሪዎች እንዲጠይቁ የሚያስችል ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 222, 234, 235, 236, 83, 224, 182, 241, 246-248, 251, 255

    Download Cassation Decision

  • አንድን ጉዳይ በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣኑ የሚመለከት ፍ/ቤት በህጉ አግባብ ክስ ተሻሽሎ ከፍ ያለ ዳኝነት ባልተጠየቀበት ሁኔታ በግምት ላይ ተቃውሞ ቀርቦ ግምቱ እንዲጣራ ሲደረግ የንብረቱ ግምት ከፍ ማለቱ በመረጋገጡ ብቻ ቀድሞ ከተጠየቀው ዳኝነት በላይ ዳኝነት የሚሰጥበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 182(1) ,92, 225, 226, 250,136

    Download Cassation Decision

  • ህጋዊ መከላከል (Legitimate self-defense) በወንጀል የማያስቀጣው የራስን ወይም የሌላን ሰው መብት ህገ ወጥ ከሆነ ጥቃት ወይም በቅርብ ከሚደርስ ህገ ወጥ ጥቃት ለማዳንና ጥቃቱ እንዳይደርስ ከማድረግ ሌላ አማራጭ (መንገድ) ሣይኖር ከሁኔታው መጠን ባለማለፍ የተፈፀመ ስለመሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 78 ,79

    Download Cassation Decision

  • ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር በተገናኘ ከሚመለከተው የገቢዎችና ጉምሩክ ጽ/ቤት ፈቃድ ሳያገኝ ተገቢ ያልሆኑ ፓዶችን (የVAT ደረሰኞችን) ማሳተምና መገልገል በወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል ስለመሆኑና የድርጅቱ ባለሀብት (ሥራ አስኪያጅ) ድርጊቱ ሲፈፀም በቦታው ያልነበረ መሆኑን በመግለጽ የሚያቀርበው መከራከሪያ ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችለው ማንኛውም በጐ አሳቢ ሰው ሊያደርገው የሚችለውን ጥንቃቄ ያደረገና ጥበብ በተሞላበት ሁኔታ ድርጅቱን በመምራት ኃላፊነቱን የተወጣ መሆኑን ማስረዳት የቻለ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 56(3),(ለ), 3(1)(ለ), 2(11), 3(1)(ሀ) አዋጅ ቁጥር 609/2001 አንቀጽ 2, 19(50) (ሐ)

    Download Cassation Decision

  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ ነጋዴ (ሠው) ያለ ተጨማሪ እሴት ታክስ ሽያጭን አከናውኗል በሚል በወንጀል ተጠያቂ ሊሆን ስለሚችልበት አግባብ፣ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 11(1)(2)፣ 22(1)(3) አዋጅ ቁጥር 609/2001 አንቀጽ 11(1) የወንጀል ህግ አንቀጽ 23(2)፣ 58(3) ደንብ ቁጥር 139/1999

    Download Cassation Decision

  • ከሠራተኛ ቅጥር ውል ጋር በተገናኘ የዋስትና ግዴታ የገባ ሰው የሠራተኛው የቅጥር ውል እንዲሻሻል ወይም እንዲለወጥ ከተደረገ በኋላ ሠራተኛው ከተሻሻለው ወይም ከተለወጠው የቅጥር ውል ጋር በተያያዘ ያለበትን ተጠያቂነት አስመልክቶ አስቀድሞ በገባበት የዋስትና ግዴታ መሰረት ተጠያቂ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1827(1)

    Download Cassation Decision