Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • ከአስጐብኚና የጉዞ ወኪል የንግድ ሥራ ፈቃድ ጋር በተያያዘ ከቀረጥና ታክስ ነፃ የሚገቡ መኪኖችን በተመለከተ የሚቀርብ ክርክርን መደበኛ ፍ/ቤቶች በቀጥታ ክስ ለማስተናገድ የሥረ ነገር ስልጣን ያልተሰጣቸው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 622/2001 አንቀጽ 87(1), (5), (9), (10), ደንብ ቁጥር 146/2000

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሰው በስራው ስልጣን መሠረት በአደራ የተሰጠውን ወይም ሊጠብቀውና ሊከላከለው የሚገባውን የህዝብ ወይም የመንግስት ጥቅም የሚጐዳ ተግባር የፈፀመ እንደሆነ በወንጀል ህግ አንቀጽ 411 መሠረት በወንጀል ሊጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 411(ሐ), 407Download Cassation Decision

  • የማይንቀሣቀስ ንብረት ተከራይ የሆነ ሰው ንብረቱን በሙሉ ወይም በከፊል ለ3ኛ ወገን በኪራይ ሊሰጥ የሚችለው ተከራዩ አስቀድሞ ለአከራዩ አሳውቆ አከራዩ የማይቃወም መሆኑ ሲታወቅ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2957(1)(2), 1731 በአ.አ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ አስተዳደር ልማት ቢሮ ደንብ ቁጥር 3/2004, 4/2004

    Download Cassation Decision

  • በፍ/ብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ የተመለከተው 60 ቀን የይግባኝ ማቅረቢያ ግዜ ታሳቢ የሚያደርገው እና ተፈፃሚ የሚሆነው ተከራካሪ ወገኖች ባሉበት ውሣኔ መሰጠቱን ወይም ለውሣኔ የሚያበቃ ክርክር የተደረገ መሆኑን ተረድተው ቀርበው ለመከታተልና የዳኝነቱን ውጤት ለመስማትና ለማወቅ ያልፈለጉትን ወይም ደግሞ የተከራካሪዎችን የመደመጥ መብት ማክበር ይቻል ዘንድ በህጉ በተዘረጋው ሥርዓት መሠረት በአግባቡ ጥሪ ተደርጐላቸው በጥሪው መሠረት ክርክራቸውን በአግባቡ ለመምራት ባልቻሉ ወገኖች ላይ ስለመሆኑ፣

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሠራተኛ ከሥራ መቅረቱ በህመም ምክንያት መሆኑ እንደበቂ ምክንያት ሊወሰድ የሚችለው በህጉ አግባብ፣ በህመሙ ምክንያት ስለመቅረቱ ለአሰሪው ያሳወቀና ፈቃድ ያገኘ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 85(4)

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሠራተኛ የቅጥሩ ውል አይነት ቋሚም ይሁን ግዜያዊ ለሠራተኛ በህጉ በተፈቀዱ ጥቅሞች የመጠቀምና ህጉ የሰጣቸውን ከለላዎች የማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 162 የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 42(2)

    Download Cassation Decision

  • የቤተ ዘመድ ስም እንዲለወጥ በፍ/ቤት ጥያቄ ለማቅረብ የሚቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 42 , 33(1) , (2)

    Download Cassation Decision

  •  ተከራካሪ ወገኖች ለክርክራቸው ምክንያት ሊሆን የሚችለውን ጉዳይ ወይም ያከራከራቸውን ጉዳይ በእርቅ ስምምነት የጨረሱ እንደሆነ የእርቅ ስምምነቱ ግብ ተከራካሪዎቹ (ታራቂዎቹ) በግላቸው ያላቸውን መብትና ግዴታ እንደሁኔታው በማስተካከል ለክርክሩ መንስኤ የሆነውን ጉዳይ በስምምነት ማስቀረት ስለመሆኑና የእርቅ ስምምነቱ ውጤትና ተፈፃሚነቱ እርቁን ባደረጉት ተከራካሪ ወገኖች መካከል ብቻ ተገድቦ የሚቀር እንጂ የሌሎች 3ኛ ወገኖች መብትና ግዴታ ሁሉ በማካተት የ3ኛ ወገኖች መብትና ግዴታን አብሮ በእርቅ እንዳለቀ የሚያስቆጥር ስላለመሆኑ፣  የተከራካሪ ወገኖች የእርቅ ስምምነት በፍ/ቤት ትእዛዝ (ውሣኔ) መጽደቅና መመዝገብ መብቴን ወይም ጥቅሜን ይነካል በሚል 3ኛ ወገኖች የሚያቀርቡት የመቃወም አቤቱታ ህጋዊና ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 3311 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358

    Download Cassation Decision

  • የመንግስት የልማት ድርጅት ወደ ግል ይዞታነት፣ ወይም ወደ አክስዮን ማህበር፣ በሚለወጥበት ወይም ወደ ቀድሞ ባለሀብቱ በሚመለስበት ጊዜ ወደ አዲሱ ባለቤት የማይተላለፉ ሒሣቦችን ለመሰብሰብ ዕዳዎችን ለመረከብና የፍርድ ቤት ጉዳዮችን ለመከታተል ስልጣን የተሰጠው የመንግስት የልማት ድርጅቶች ባለአደራ ቦርድ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 208/92 አንቀጽ 5፣6

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሰው ለሌላ ሰው ለማስተላለፍ የሚችለው በህግ ጥበቃ የሚደረግለትንና ያለውን መብት እንጂ የሌላውን መብት ስላለመሆኑ፣  በህግ ጥበቃ የሚደረግለት መብት ሣይኖር በስሙ የተመዘገበ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት የምስክር ወረቅተ ከያዘ ሰው ንብረቱን በመንደር ውል የገዛ ገዢ ተገቢውን ማጣራት በማድረግና፣ በጥንቃቄ፣ የገዛና የቅን ልቦና ያለው ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣  የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ የተሰጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ደንብና አሰራርን መሠረት ያላደረገ እንዲሁም ከስልጣን ውጪ የተሰጠና በህግ ፊት የማይፀና ስለመሆኑ በማናቸውም ማስረጃ ለማረጋገጥ የተቻለ እንደሆነ በተሰጠው የምስክር ወረቀት የተፈጠረውን የህጉን የህሊና ግምት ማፍረስ የሚቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1195, 1196, 2884, 2882-2884 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 40(1)(2)

    Download Cassation Decision

  • የመድን ሥራ የሚሰሩ የመድን ኩባንያዎች በመድን ፖሊሲ ውስጥ ፖሊሲውን ተጠያቂነትን አያስከትልም ወይም በፖሊሲው መሰረት የካሳ ክፍያ ጥያቄ መነሻ የሆነው ክስተት ከደረሰ በኃላ የተወሰነ ድርጊት ከተፈፀመ ወይም ሳይፈፅም ከቀረ ኃላፊነቱ ቀሪ ይሆናል የሚል የውል ሁኔታ ተፈፃሚነት የሌለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 559/2000 በአንቀፅ 6 ንዑስ አንቀፅ 1

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሠው በሰራው ሥራ ወይም በፈፀመው ድርጊትና ድርጊቱ በሌሎች ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳያስከትል ተገቢውን ጥንቃቄ ባለማድረጉ ምክንያት በ3ኛ ወገኖች ላይ ለሚደርሰው ጉዳት በፍ/ብሔር ኃላፊነት ተጠያቂ የሚሆን ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2069

    Download Cassation Decision

  • አንድ የግብር ውሳኔ በግምት ስለሚወሰንበት አግባብ የግብር ህግ አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀፅ 69

    Download Cassation Decision

  • ፍ/ቤቶች የገንዘብ መቀጫን ሲወስኑ ከግምት እና ግንዛቤ ውሰጥ ሊያስገቡዋቸው የሚገቡ የተከሳሽ ግላዊና የወንጀሉን ሁኔታዋችን በማገናዘብና ፤ በወንጅል ህጉ እና በቅጣት መመሪያው ላይ የተቀመጡ መሰፈርቶችን መሰረት በማድረግ መወሰን ያለባቸው እንጂ በደፈናው የገንዘብ መቀጮ መወሰን ተገቢ ሰላለመሆኑ ፤ የወ/ሕ/ቁ 88 /2/ እ 90 90 (2)፤ የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2000

    Download Cassation Decision

  • ከመንግስት የተከራየውን ቤት ከአከራዩ ፈቃድ ውጪ ለ3ኛ ወገኖች አከራይቶ ሲገለገል የነበረ ሰው በመንግስት መመሪያ መሠረት ቤቱ ተከራይቶ ሲሰራበት ለነበረው ሰው በመተላለፉ ምክንያት የመጀመሪያው ተከራይ በመመሪያው መሠረት ቤቱ የተላለፈለት ሰው ላይ የሚያቀርበው የሁከት ይወገድልኝ ክስ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣

    Download Cassation Decision

  • በአንድ የፍርድ ባለእዳ ንብረት ላይ ፍርድ እንዲፈፀምላቸው የሚጠይቁ የፍርድ ባለገንዘቦች ያሉ እንደሆነ አፈፃፀሙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 403 መሠረት ሊስተናገድ የሚገባ እንጂ በሌላ የፍ/ባለመብት ምክንያት በሌላ የአፈፃፀም መዝገብ ላይ የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተነስቶ የአፈፃፀም ጥያቄው ካልቀረበ በስተቀር ሊቀጥል አይችልም ለማለት የማይችል ስለመሆኑ፣  አፈፃፀሙ በሚካሄድበት ወቅት በንብረቱ ላይ የመያዣ ውልን መነሻ በማድረግ የቀዳሚነት መብት አለን የሚሉ ወገኖች ያሉ እንደሆነም ጥያቄው በቀረበ ጊዜ እንደየአግባብነቱ ታይቶ ሊወሰን የሚገባው ስለመሆኑ፣  አፈፃፀሙን የያዘው ፍ/ቤት በንብረቱ ባለቤት ላይ የገንዘብ ክፍያ ፍርድ አሰጥተው እና ገንዘቡም እንዲከፈላቸው ጥያቄ ያቀረቡ የፍርድ ባለገንዘቦችን አስቀርቦ ጥያቄያቸውን በመመርመር ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 403 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ አኳያ አገናዝቦ በመመልከት አፈፃፀሙ ሊመራ የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 403, 378

    Download Cassation Decision

  • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር በከተማው ክልል ውስጥ የሚገኘውን መሬትና የተፈጥሮ ሀብት የማስተዳደር ሥልጣን ያለው ስለመሆኑ፣  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በህግ የተሰጠውን የማስተዳደር ስልጣን መሠረት በማድረግ በከተማው ክልል ውስጥ የሚገኘውን መሬት በተመለከተ የከተማዋን መሪ ፕላን እንዲሁም የከተማውን ማህበረሰብ ፀጥታና ደህንነት ታሣቢ በማድረግ በከተማው የሚገኝ ቦታ (መሬት) ለምን ለምን አገልግሎት መዋል እንዳለበት የመወሰን ስልጣንና ኃላፊነት ያለው ስለመሆኑና ይህንን ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያደርገው እንቅስቃሴ እንደ የሁከት ተግባር ሊቆጠር የማይችል ስለመሆኑ፣  አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 11(2)(ለ)(ሰ), 38

    Download Cassation Decision

  • ለፍርድ አፈፃፀም ከተያዘ የሀራጅ ጨረታ ሽያጭ ጋር በተገናኘ ለሁለተኛ ጊዜ በወጣው ጨረታ የተያዘው ንብረት ሊሸጥ የሚገባው ባለሙያ ካቀረበው የንብረቱ ግምት ዋጋ በላይ በተገኘ ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች ብቻ ሣይሆን የባለሙያው ግምት ሳይጠበቅ በሁለተኛው ጨረታ ከተወዳዳሪዎች መካከል ከፍተኛ የሆነውን ዋጋ ላቀረበው ተጫራች ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 428(1)

    Download Cassation Decision

  • የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለይዞታ የሆነ ሠው ባለማቋረጥ ለ 15 ዓመታት ግብር በስሙ መክፈሉ ከተረጋገጠ የዚሁ ንብረት ባለቤት መሆን ስለመቻሉ፣ የፍ/ህ/ቁ 1168(1)

    Download Cassation Decision

  • የፍርድ ቤትን እገዛ በመጠየቅ ማስረጃ ማስቀረብ የሚቻለው ጠያቂው ተከራካሪ ወገን እንዲቀርብ የተጠየቀውን ማስረጃ ትክክለኛ ግልባጭ በቅርብ ግዜ ለማምጣት የማይችልበትን ወይም ለማስገልበጫ የሚያስፈልገውን ወጪ ለመክፈል የማይቻል መሆኑን እንዲሁም ማስረጃው ለክርክሩ ምን ያህል ጠቃሚነት እንዳለውና ትክክለኛ ፍርድን ለመስጠት የሚያስችል ስለመሆኑ በጽሁፉ ገልፆ ለማስረዳት የቻለ እንደሆነ ስለመሆኑ፣

    Download Cassation Decision