Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • የስጦታ ዉል ውስጥ ተቃራኒ የሚሆን ቃል ከሌለ በቀር ስጦታ ከተደረገ በኋላ ልጅ መወለዱ ስጦታውን ለመሻር ምክንያት የማይሆን ስለመሆኑ፣ ፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2450

    Download Cassation Decision

  • ውዝፍ ያልተከፈለ ደሞዝ ከስራ ስለተሰናበተ ሠራተኛ የሚከፈል ሳይሆን ወደ ስራ እንዲመለስ ለተወሰነበት ሰራተኛ ስለመሆኑ

    አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 43(5)

    የሰ/መ/ቁ. 116002

    ቀን 6/3/2008 ዓ.ም

    ...
  • አንድን ሰራተኛ የሥራ መሪ ነው ሊባልበት ስለሚቻልበት አግባብ፡- የሥራ መሪን በተመለከተ ክርክር ሲነሳ ተግባራዊ ሊሆኑ ስለሚገባቸው ህጎች፡- የስራ መሪ የሚያቀርባቸው የመብት ጥያቄዎች ቀሪ ስለሚደረጉበት የይርጋ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀፅ 2(!)፣ 3(2(ሐ) የፍ/ሕ/ቁ.1677(1)፣1845፣2512፣2593

    Download Cassation Decision

  • በአባት በኩል ያለን መወለድ መቃወም የሚቻለው የልጁ አባት ነው ተብሎ በህግ ግምት የሚሰጠው ሰው እሱ የሞተ ወይም ችሎታ ያጣ እንደሆነ ከተወላጆቹ አንዱ የመካድ ክስ በማቅረብ መቃወም የሚችል ስለመሆኑ፣ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/1992/አንቀጽ 167፣174 እና 179

    Download Cassation Decision

  • የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በተደራጀባቸውና ባልተደራጀባቸው ክልሎች ከአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ የሚነሱ ይግባኞች መቅረብ ያለባቸው ከፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ጋር አቻ ስልጣን ላላቸው በየክልሉ ላሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎቶች ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 154 የዒ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80/2/ አዋጅ ቁ. 322/95

    Download Cassation Decision

  • በጊዜያዊ ትእዛዝ ላይ በሚሰጥ ብይን ቅር የተሰኘ አካል የስረ ነገሩ ክርክር የመጨረሻ የፍርድ ውሳኔ እስካልተገኘ ድረስ ይግባኝ (የሰበር) አቤቱታ ሊቀርብ የማይችል ስለመሆኑ

    የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.320(3)

     

    የሰ/መ/ቁ. 116209

    በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ሥርዓት ህግ መሰረት ክስ እንዲሻሻል መፍቀድ የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብትን የሚያጣብብ ነው የሚባል ስላለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 188፣119 ኢፌድሪ ሕግ መንግስት አንቀጽ 20(1)

    Download Cassation Decision

  • ከሳሽ ወገን ያለፍርድ ቤት ፈቃድ በተወው ወይም በሰረዘው ነገር ሌላ ክስ ለማቅረብ የማይችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.፤278፤ 279/1/

    Download Cassation Decision

  • እድሜው ያልደረሰ ልጅ የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ የሚያስችል የሞግዚት ስልጣን ይሰጠኝ ጥያቄ ፍ/ቤቶች የህፃንን መብትና ድህንነት ቅድሚያ እንዲሰጠው በማደረግ ሲወሰኑ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የቀረበውን መሰረታዊ ጥያቄ እና አማራጭ መፍትሔ መኖሩን አለመኖሩን በማጣራት መወሰን ያለበት ሰለመሆኑ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግሰት 36 (2) ፣ ፍ/ብ/ሕ/ቁ 280 እና 289(1) የቤተሰብ ህግ አዋጅ 213/1992 አንቀፅ 43

    Download Cassation Decision

  • በፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 2472 ላይ ገንዘብ ሰለመከፈሉ ማሰረጃን በተመለከተ የተደነገገው ፤ ከብድር ውጭ ለሆነ ግንኙነት ከተከፈለ ገንዘብ ጋር በተያያዘ ተፈፃሚነት የሌለው ሰለመሆኑ ፤

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሰው በወላጅ አባቴ ስም መጠራቴ ቀርቶ በአሳዳጊዬ ስም እንድጠራ ብሎ የሚያቀርበው የዳኝነት ጥያቄ በሕጉ ስለስም ለውጥ የተጠቀሱትን ድንጋጌዎች የማያሟላ በመሆኑ ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ.32(1)፣36(1)

     

    የሰ/መ/ቁ 116977

     

    የካቲት 25 ቀን 2008 ዓ/ም

     

    አንድ ዕቃ ለመሸጥ /በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ለማስረከብ/ የተዋዋለ ወገን ከዕርሱ አቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ውሉን መፈጸም ባልቻለ ጊዜ በቅድሚያ ለዚሁ ስራ የተቀበለውን ገንዘብ ከወሰደበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር ከመመለስ ውጭ ውሉን ባለመፈጸሙ ምክንያት ለደረሰው ኪሳራ እንዲከፍል የማይገደድ ስለመሆኑ፣ ፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2356/1/

    Download Cassation Decision

  • ማንኛውም እቃ ወይም መጓጓዣ ሊወረስ በሚችል ወንጀል በተከሰሰ ሰው ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተሰጠ ተጨማሪ ትእዛዝ መስጠት ሳያስፈልግ እቃው ወይም መጓጓዣው እንዲወረስ የሚደረግ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 622/2001 አንቀፅ 104(1)

     

    የሰ/መ/ቁ. 117065 የካተት 30 ቀን 2008ዓ/ም

    ዳኞች፡-ተሻገር ገ/ስላሴ

    ተዋዋይ ወገኖች በስራ ውል ስምምነታቸው በግልፅ ኮሚሽንን የደሞዝ አካል አድርገው እስከተዋዋሉ ድረስ ቅራኔ በተነሳ ሰዓት ኮሚሽንን እንደ ደመወዝ አይደለም በማለት መውሰድ ተገቢ ስላለመሆኑ አዋጅ ቁ.377/1996 አንቀፅ 53(2(መ)

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሠራተኛ የሥራ መሪ ሆኖ የሚቆጠረው እንደ ድርጊቱ የሥራ ፀባይ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንጻር መታየት ያለበት ስለመሆኑ፣

    አዋጅ ቁጥር 377/96 አዋጅ ቁጥር 494/1998 አንቀጽ 3/2/ሐ/

    የሰ/መ/ቁ.117076

    ...

  • የአንድ ሰው መብትና ግዴታ ለተወላጆቹ በውርስ ሊተላለፍ የሚችለው በሟቹ ምክንያት የሚቋረጡ ካልሆነ በቀር ሟቹ በሞተበት ቀን የነበሩት መብቶችና ግዴታዎች ስለመሆናቸው፣

    Download Cassation Decision

  • በወ/መ/ህ//አ/ቁ. 676(1) የእምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል የተከሰሰ ሰው የዋስትና መሰጠት (መፈቀድ) ጥያቄ የሚሰጠው በጉዳዩ ላይ በአግባቡ ተመርምሮ እንጂ ከወዲሁ ስላለመሆኑ አዲሱ የፀረ ሙስና ህግ አዋጅ ቁ. 881/2007 አንቀፅ 31

     

    የሰ/መ/ቁ 117383

    ቀን 6/03/2008 ዓ.ም

    ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ

     

    በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ስራቸውን የሚያከናውኑት ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ጋር የሚመሰረቱት የሥራ ግንኙነት ስምምነት ያለ እንደሆነ ጉዳዩ የሚዳኘው በዓለም አቀፍ ስምምነቱ መሠረት ስለመሆኑ፡-

     

    የሰ/መ/ቁ.117390

    ታህሳስ 21 ቀን 2008 ዓ.ም

    ዳኞች፡- አልማው ወሌ

     

    ዓሊ መሐመድ

    ...
  • በአንድ ሰው ላይ ለደረሰ ጉዳት ኃላፊነትን በሚጥሉ የተለያዩ የህግ ድንጋጌዎች ምክንያት ከአንድ በላይ የሆኑ ሰዎች ለጉዳቱ በአንድነትና በነጠላ ኃላፊ በሚሆኑበት ጊዜ ኃላፊ ከሆኑት ሰዎች አንዱ ብቻ ጥፋት የሰራ እንደሆነ በመጨረሻ የተወሰነውን ዕዳ እርሱ እራሱ ብቻ የመቻል ኃላፊነት ያለበት ስለመሆኑ፣ ፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2157

    Download Cassation Decision

  • አሰሪው በሰራተኛው ህይወት ላይ አደጋ ሊያደርስ በሚችል አኳኋን እንዲሰራ ማድረግ ህገ ወጥ ተግባር ሲሆን ይህም ሰራተኛው የስራ ውሉን ያለማስጠንቀቂያ ለመቋረጥ በቂ ምክንያት ነው ይህ ከተረጋገጠ ደግሞ ሠራተኛው በአዋጅ መሰረት የተለያዩ ክፍያዎችን የማግኘት መብት  ያለው ስለመሆኑ

    አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 14 (1) (ሠ)፣32(1)(ለ)