Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • የውርስ ንብረት የመከፋፈል ጥያቄ ንብረቱ በአይነት ተለይቶና ተገምቶ እስከቀረበ ድረስ በቀረበው ግምት መሰረት የፍርድ ቤቶችን የስረ ነገር ስልጣን ሊወሰንበት የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 18፣23

    Download Cassation Decision

  • በአጭር ስነ ሥርዓት ክስ ሊቀርብ ስለሚችልበት አግባብ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 284

    Download Cassation Decision

  • በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት ተይዞ የሚሸጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት ሁለት /ከሁለት በላይ የሆኑ ሰዎች በህብረት የያዙት እና ያልተከፋፈሉት በሆነ ጊዜ ከተከፋዮቹ አንዱ ንብረቱን ለመግዛት በጨረታ ተወዳዳሪ ሆኖ የቀረበ እንደሆነ የፍርድ ባለእዳው እንደቀረበ ተቆጥሮ የተቀዳሚነት መብት የሚሰጠው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 443፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 126/1/፣ 1386-1409

    Download Cassation Decision

  • በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት ተይዞ የሚሸጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት ሁለት /ከሁለት በላይ የሆኑ ሰዎች በህብረት የያዙት እና ያልተከፋፈሉት በሆነ ጊዜ ከተከፋዮቹ አንዱ ንብረቱን ለመግዛት በጨረታ ተወዳዳሪ ሆኖ የቀረበ እንደሆነ የፍርድ ባለእዳው እንደቀረበ ተቆጥሮ የቀዳሚነት መብት የሚሰጠው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 443፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 126/1/፣ 1386-1409

    Download Cassation Decision

  • ተከራካሪ ወገኖች ባላነሱት የመከራከሪያ ነጥብ ወይም የግራ ቀኙ ወገኖች ባልተለያዩበት ጉዳይ እንዲጣራ በማድረግ ውሳኔ መስጠት ተገቢ ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 241፣242

    Download Cassation Decision

  • የዝውውር ውሳኔን ተከትሎ ሰራተኛው ለአምስት የሰራ ቀናት የሰራ ቦታ ላይ አልተገኘም በማለት የማሰናበት እርምጃ ተገቢነት ለማጣራት ፤ ከነባራዊ ሁኔታ እንዲሁም ሰራተኛው የሰራ ቦታ ላይ መገኘት ከሚችልበት ሁኔታ አንፃር እንዲሁም ከቀረበው ማስረጃ አንፃር በመመዘን የሚወሰን ስለመሆኑ ፤

    Download Cassation Decision

  • አሰሪ ሰራተኞችን ከማሰናበቱ በፊት በትክክል አጣርቶ እርምጃ መውሰድ ሲገባው ፤ክርክር ከተጀመረ በኃላ ከስንብት ደብዳቤ ሌላ ደብዳቤ መፃፉ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁን ዓላማ እና መንፈስ የማያሟላ ሰለመሆኑ ፤ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91 (1) (3) አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27 (1) (ሸ) ( ቀ)

    Download Cassation Decision

  • የ ሙከራ ጊዜ ቅጥር ሲፈጸም ሰራተኛው በግልጽ እንዲያውቀው ሳይደረግና ስምምነት ሲደረግም በጽሁፍ ተደርጎ በሁለት ምስክሮች ባልተረጋገጠበት አሰሪው ሠራተኛው ለተቀጠረበት የሥራ መደብ ተስማሚ ሆኖ አልተገኘም በሚል የቅጥር ውሉን ያለምንም ማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ በህጉ መብት ያልተሰጠው ስለመሆኑ፣ የአ/ቁ. 377/96 አንቀጽ 1/1/ /2/ እና /3/

    Download Cassation Decision

  • ለጡረታ አፈፃፀም ተብሎ የመንግሰት ሰራተኛን የግል ማህደር በኤጀንሲው እንዲላክ ተጠይቆ፤ሰራተኛው የመንግስት ብረት አልመለሰም በማለት ማህደር አልክም ማለት ህጋዊ ሰላለመሆኑ ፤ የጡረታ አበል የማግኘት መብት የዕዳ መያዣ ሊደረግ ወይም በውርስ ወይም በማናቸውም መንገድ ሊተላለፍ የማይችል ሰለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 345 /97 አንቀፅ 47 (2) ፣ 44 እና 55 (2)

    Download Cassation Decision

  • በሁለት ወገኖች መካከል የተፈረመ ሰነድን እንደ ህጋዊ ስምምነት ለመውሰድ የፈራሚ ወገኖችን ሃሳብና ፍላጐት መመርመር አስፈላጊ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1734, 1952/1/

    Cassation Decision no. 12719

  • የሥር ፍ/ቤት በጭብጥነት ይዞ በአግባቡ ባጣራው ፍሬ ጉዳይ ላይ በይግባኝ ፍርዱን የሚመለከተው ፍ/ቤት ያለበቂና ህጋዊ ምክንያት የተጣራውን ፍሬ ነገር በድጋሚ እንዲጣራ ወደ ሥር ፍ/ቤት መመለስ ተገቢ ስላለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.136(1)፣343(1)

    Download Cassation Decision

  • አንድ የግልግል ዳኝነት ጉባኤ መቀመጫ አዲስ አበባ ከተማ ኢትዮጵያ ከሆነ፤ጉዳዩም ታይቶ ዉሳኔ የተሰጠበት በኢትዮጵያ ሕግ መሰረት ከሆነ፤የዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና የአገሮች ልምድ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሕጎች እና የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሠበር ሰሚ ችሎት ከዚህ በፊት ከሰጣቸዉ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም አንጻር ተከራካሪ ወገኖች “የግልግል ዳኝነት ጉባኤው ዉሳኔ የመጨረሻ ዉሳኔ ነዉ” ብለው ቢስማሙም ዉሳኔዉ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ከሆነ በሰበር ከመታየት የሚከለከልበት የሕግ መሰረት የሌለ ስለመሆኑ፤ 

     በተንኮል የተደረገ ዉል ፈራሽ የሚሆነዉ ከተዋዋዮቹ አንደኛዉ ወገን ዉሉ እንዲደረግ ያደረገዉ በሁለተኛዉ ተዋዋይ ላይ ተንኮል ባይደርስበት ኖሮ ዉል የማያደርግ እንደነበረ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ፤ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1704(1)፤1808(1)
     የአንድ ዉል በፍ/ቤት ዉሳኔ የፈረሰ እንደሆነ የዉሉ መፍረስ የሚያስከትለዉ ዉጤት ተጣርቶ መወሰን ያለበት ስለመሆኑ
    በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1704(1)፤ 1808(1)፤1815

    Download here

  • የ ማይፀናና ህገ ወጥ የሆነ የቤት ሽያጭ ውል ፈራሽ ሆኖ ግራ ቀኙ ወገኖች ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ ውሳኔ ሲሰጥ በህገ ወጥ በመንገድ በተገኘው ባዶ ቦታ ላይ ቤት የገነባው ወገን ቤቱን በራሱ ወጪ በማፍረስ ለባለይዞታው እንዲያስረክብ ከማድረግ ባለፈ ለግንባታው ያወጣውን ወጪ ባለይዞታ የሆነው ወገን እንዲከፍለው ሊደረግ የማይገባ ስለመሆኑ፡- የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕ/መ አንቀፅ 40(3) እና የፍ/ብ/ህ ቁ 1815Download Cassation Decision

  • የ ኦዲት ሪፖርት የሚያሻማና ግልጽነት የሌለው በሆነበትና በሪፖርቱ የቀረበውን ሀሳብ ይዘት እንዲያስረዱ ሪፖርቱን ያዘጋጁ የሂሳብ ባለሙያዎች ቀርበው እንዲያስረዱ ባልተደረገበት ሁኔታ ፍርድ ቤቶች የኦዲት ሪፖርቱን ራሳቸው በተረዱት አግባብ ተርጉመው የሚሰጡት ውሳኔ ስነ ስርዓታዊ ነው ሊባል የማይችል ስለመሆኑ የፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 133 (3)

    Download Cassation Decision

  • በፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ ማናቸውም ንብረት በሐራጅ እንዲሸጥ በሚወሰንበት ጊዜ የሚሸጠው ንብረት ከትክክለኛው የዋጋ ግምት አላግባብ ከፍ ወይም ዝቅ ተደርጎል ብሎ የሚያስበው ወገን የጨረታው ቀን ከመድረሱ በፊት የጨረታውን ትዕዛዝ ለሰጠው ፍ/ቤት ግምቱ ተጋኗል በማለት መቃወሚያ ማቅረብ የሚጠበቅበት ሥለመሆኑ በሁለተኛው የጨረታ ማስታወቂያ በተወሰነው ቀን ተጫራች ያልቀረበ እንደሆነ ለጨረታ የቀረበውን ንብረት የፍርድ ባለገንዘቡ ተረክቦ እንዲይዝ ትዕዛዝ ሊሰጥ የሚችለው የፍርድ ባለገንዘቡ ንብረቱን ለመረከብ ፈቃደኛ ከሆነ ብቻ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 423/(1)(2)፣የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 428/2

    Download Cassation Decision

  • በህገወጥ መንገድ ተይዘው በተገኙ የቁም እንስሳት ላይ አግባብ ያለው አካል በሚወስደው እርምጃ ላይ በቀጥታ ክስ ስልጣን ላለው ፍ/ቤት ማቅረብ የሚቻል ስለመሆኑ፣ የቁም እንስሳት ግብይት አዋጅ ቁጥር 819/2006 አንቀጽ 15/5/ እና 8 ደንብ ቁጥር 341/2007 አንቀጽ 19/4/ እና 5

    Download Cassation Decision

  • የ ይዞታ ክርክርን በተመለከተ አንድ ተከራካሪ ወገን ካርታዉ እንደተሰረዘ እና በዚያ ካርታ ይዞታዉን ለመጠየቅ መብት እንደሌለዉ ዉሳኔ ተሰጥቶ እያለ ተከራካሪ ወገን በመቀየር ክስ ስላቀረበ ብቻ የክርክሩ ጭብጥና ተከራካሪ ወገን ስለሚለያይ ከዚህ ቀደም ዉሳኔ ተሰጥቷል የሚያስብል አይደለም በማለት አዲስ ክስ ማቅረብ የማይችል ስለመሆኑ፡- የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5(1)

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሠራተኛ የሥራ መሪ ሆኖ ሥራውን ሲመራ በፈጸማቸው ማናቸውም ክንውኖች ምክንያት በተወሰደበት እርምጃ ሊያነሳቸው የሚችላቸው የመብት ጥያቄዎች የሥራ መሪው በሂደት ወደ ሠራተኛ የሥራ መደብ የተዛወረ ቢሆንም እንኳን በፍትሐብሔሩ ድንጋጌዎች የሚገዙ ስለመሆናቸው አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 3/1፣3/2/ሐ

    This cassation decision deals with the application of labor proclamation on managers.

    Download Cassation Decision

  • በኮንትራት /በጊዜያዊነት/ የተሰጠ አገልግሎት ለጡረታ ተግባር ስለሚያዝበት አግባብ ዋጅ ቁጥር 345/1995 ፤በአዋጅ ቁጥር 907/2007

    Download Cassation Decision

  • በ አፈፃፀም ሂደት ንብረቴ አላግባብ ተሸጠ ወይም መብቴ ተጎዳ የሚል ሰው ፤ አቤቱታውን አፈፃፀሙን ለያዘው ፍርድ ቤት ወይም አፈፃፀሙን የያዘው ፍርድ ቤት ስህተት የፈፀመ ነው በማለት በይግባኝ እንዲታረም ማድረግ እንጂ የአፈፃፀሙ መዝገብ ከተዘጋ እና አመታት ካለፉ በኃላ መብቴ ይከበረልኝ በማለት አዲስ ክስ ማቅረብ የማይችል ስለመሆኑ፤ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 404 እና 231(1) (ሀ)

    Download Cassation Decision