Labor dispute
Absence for 5 consecutive days
Termination of contract of employment
Art. 27 of Proclamation no. 377/2004
አንድ ሰራተኛ በመደዳው ለአምስት የስራ ቀናት ካለበቂ ምክንያት ከስራ መቅረቱ የተረጋገጠ እስከሆነ ድረስ አሰሪው በዚሁ ምክንያት ሰራተኛውን ካለማስጠንቀቂያ ከስራ ያሰናበተው ስለመሆኑ በደብዳቤ ሳይገልፅ መቅረቱ የሥራ ውሉ በሕግ አግባብ አልተቋረጠም ወደሚል መደምደሚያ የሚያደርስ ስላለመሆኑ
አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 27(1) (ለ)
የሰ/መ/ቁ.104862
መጋቢት 3 ቀን 2007 ዓ.
ዳኞች፡- መድሕን ኪሮስ
አልማው ወሌ
ሡልጣን አባተማም
ሙስጠፋ አህመድ
ተኽሊት ይመስል
አመልካች፡-አቶ መልካሙ አረጋ - ቀረቡ
ተጠሪ፡-ተስፋዬ ለገሠ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ - ጠበቃ ይትባረክ መኮንን ቀረቡ
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል፡፡
ፍ ር ድ
ጉዳዩ የአሰሪና ሰራተኛ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ አመልካች በአሁኑ ተጠሪ ላይ
...