Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • የማይንቀሣቀስ ንብረት ሽያጭ ጋር በተገናኘ ንብረትነቱ ከአገር የወጡ ኤርትራዊያን የሆነ ቤትን ለማስተዳደር ውክልና የተሰጠው ሰው የመሸጥ ውክልና በባለቤቱ ያልተሰጠ ቢሆንም እንኳን በሚመለከተው የመንግስት አካል በተሰጠ (በተላለፈ) መመሪያ መሠረት ከተወካዩ ቤቱን የገዛ ገዥ ተወካዩ ቤቱን የሸጠለት በሌለው የውክልና ስልጣን ነው በሚል ገዝቶ ስመ ንብረቱ ከተላለፈለት በኋላ የሽያጭ ውሉ ፈርሶ ቤቱ ለባለቤቱ ሊመልስ ይገባል ለማለት የማይችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 334/1995 አንቀጽ 2(1), 4(1), 5(1)(ሀ)

    Download Cassation Decision

  • የሥራ ውል ወይም በሌላ ሠነድ ሠራተኛው ስምምነቱን ባልሰጠበት ሁኔታ አሰሪ የሆነው አካል እህት ድርጅት ወደ ሆነ ተቋም (ድርጅት) ሰራተኛውን አዛውሮ ለማሰራት አሠሪ መብት የሌለው ስለመሆኑ፣

    Download Cassation Decision

  • በአንድ ጉዳይ ተከሣሽ የሆነ ወገን የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ ካቀረበ ፍ/ቤቱ ከቀረቡት ክሶች መካከል በሥረ-ነገር ስልጣኑ ሥር ያሉትን መርጦ ለማየትና ከሥረ-ነገር ስልጣኑ በላይ የሆነውን ጉዳይ ስልጣን ላለው ፍ/ቤት ይቅረብ በማለት የከሣሽን ክስና የተከሣሽን የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ ተነጣጥለው እንዲታዩ በማድረግ የሚሰጠው ትዕዛዝ ተገቢ ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 30(1)¸324(1) (ሀ),215(2)¸17(3)

    Download Cassation Decision

  • የግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ መብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የሚቀርብ ክርክርን ለማየት ስልጣን ያለው አካል የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ስለመሆኑ፣  የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በህግ የዳኝነት ስልጣን የተሰጣቸው አካላት የቀረበላቸውን ጉዳይ በህጉ አግባብ ያስተናገዱና ውሣኔ የሰጡ መሆኑን የማረጋገጥና የመቆጣጣር ኃላፊነትና ስልጣን ያለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.9,231 አዋጅ ቁ. 25/88 አንቀጽ 10(22) አዋጅ ቁ. 454/97 አንቀጽ 2(1) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3)(ሀ) አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 142, 147 አዋጅ ቁ. 345/95 አዋጅ ቁ. 209/55 አዋጅ ቁ. 715/2003

    Download Cassation Decision

  • በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የመንግስት ቤቶች ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ከወጣው መመሪያ ቁ.3/2004 አፈፃፀምጋር በተገናኘ የንግድ ቤቱን በማከራየት ከሚያገኙት ገቢ ውጪ ሌላ ገቢ የሌለውና በእድሜ አዛውንት የሆነ ተከራይ የኪራይ ውል ሊቋረጥ የማይገባ ስለመሆኑ፣ መመሪያ ቁ.3/2004 አንቀጽ 6(1)

    Download Cassation Decision

  • አበዳሪ የሆነ ባንክ ለተበዳሪው ላበደረው ገንዘብ በመያዣነት ለያዘው ንብረት የመድን ሽፋን የገባለት እና የአርቦን ክፍያን ለመክፈል የተስማማ እንደሆነ ለመድን አስገቢው ተቋም የአረቦን ክፍያውን ለመክፈል የሚገደድ ስለመሆኑ፣  የንግድ ህግ ቁጥር 657, 675

    Download Cassation Decision

  • በፍ/ቤት በመካሄድ ላይ ከነበረ ክርክር ጋር በተገናኘ በተከራካሪዎቹ ወገኖች አመልካችነት ጉዳይ በእርቅ በማለቁ የተከራካሪዎቹን የእርቅ ስምምነት ተቀብሎ በማጽደቅ እንዲመዘገብ በማለት በፍ/ቤት የተሰጠ ትእዛዝ ላይ መብቴ ወይም ጥቅሜ ተነክቷል የሚል ወገን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358 መሠረት የሚያቀርበው የመቃወሚያ አቤቱታ ህጋዊና ተቀባይነት ያለው በመሆኑ ትእዛዙን የሠጠው ፍ/ቤት አቤቱታውን ተቀብሎ ሊያስተናግደው የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358,360,277(1)(2)

    Download Cassation Decision

  • የውርስ ሀብትን እንዲያጣራ የተመደበ የውርስ ሀብት አጣሪ የንብረትነቱ የሟች የግል ሀብት መሆን በተመለከተ በሪፖርቱ ገልጿል በሚል ምክንያት ከንብረቱ ጋር በተገናኘ የባለሀብትነት ክርክር ያቀረበውን ወገን ጥያቄ በአግባቡ ባለማስተናገድ ውሣኔ ላይ መድረስ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መግስት አንቀጽ 40(1), 37 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 1206

    Download Cassation Decision

  • አንድ ውል (ስምምነት) ህግ በጽሑፍ እንዲሆን ሲያስገድድ ውሉ በጽሁፍ መደረግ ያለበት እና በተዋዋይ ወገኖችና በሁለት ምስክሮች ፊርማ ሊረጋገጥ የሚገባ ስለመሆኑና መሀይማንና ማየት የተሳናቸው ሰዎች የሚያደርጉት ውል በአዋዋይ ወይም በዳኛ ፊት የተደረገ ካልሆነ በቀር በውሉ የማይገደዱ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1727, 1728(3), 2005

    Download Cassation Decision

  • የወጪና ኪሣራ ክፍያ ጉዳይ ሊስተናገድ ሊወሰን የሚገባው በዋናው ጉዳይ ፍርድ (ውሣኔ) በተሰጠበት መዝገብ ስለመሆኑ፣  ወጪና ኪሣራ ክፍያን በተመለከተ ማን መክፈል እንዳለበት በዋናው ጉዳይ ላይ ተለይቶ ከተወሰነ በኋላ ምን ያህል መከፈል እንዳለበት በተመለከተ ደግሞ ዋናው ፍርድ ባረፈበት መዝገብ የወጪና ኪሣራ ዝርዝር ቀርቦ ሌላኛው ተከራካሪ ወገን ስለቀረበው የወጪና ኪሣራ አስፈላጊነት ስለመጠኑ እና በእርግጥም ወጪና ኪሣራ ስለመውጣቱ በተመለከተ የበኩሉን ክርክር ካቀረበ በኋላ የወጪና ኪሣራ ልኩ ሊወሰን የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 183, 378, 462-464

    Download Cassation Decision

  • በተከራካሪ ወገኖች ክርክር በሚካሄድበት ወቅት በፍ/ቤት ትእዛዝ በተከራካሪ ወገን ስም በባንክ የሚገኝ ገንዘብ ታግዶ እንዲቆይ ተደርጐ ትእዛዙ ፀንቶ በነበረበት ግዜ በገንዘቡ ላይ ወለድ ሊታሰብ ይገባል ወይስ አይገባም በሚል ክርክር የተነሣ እንደሆነ ከጉዳዩ ልዩ ባህሪ ጋር በተገናኘ ፍ/ቤቶች የልዩ አዋቂ ምስክርነትና የባለሙያ ማብራሪያን አስቀርበው በማጣራት ሊወሰኑ የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 136

    Download Cassation Decision

  • የክስ አቀራረብ ሥርዓቱን አሟልቶ ያልቀረበ ክስን ፍ/ቤቶች ሌላኛውን ወገን ሳይጠሩ ለመዝጋት ስለመቻላቸው፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ. 33, 80, 222, 225, 226 እና 231 83915 አቶ ዩሐንስ በቀለ እና የቦንጋ ከተማ ማዘጋ

    Download Cassation Decision

  • አንድን በጽሁፍ የተደረገ ውል ዋና ሰነድ ጠፍቷል በማለት ክርክር በቀረበ ጊዜ ፍ/ቤት በማስረጃነት በቀረበው የውሉ ሰነድ ኮፒን ተቀብሎ በውሉ የተመለከቱትን ምስክሮች ሊሰማ የሚገባው ጠፍቷል የሚለው ወገን ዋናው ሰነድ ስለመጥፋቱ በተመለከተ በአግባቡ ያስረዳ እንደሆነና የውሉንም ኮፒ አግባብነት ያለው አካል ዋናው የውል ሰነድ ጋር ትክክለኛነቱን ያረጋገጠው እንደሆነ ስለመሆኑ፣  የምስክሮቹ ቃል ሊሰማ የሚገባውም የውሉ ቃል ምን እንደሆነ ለማረጋገጥ አስፈላጊ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2011(1),2003 ,1730(1)

    Download Cassation Decision

  • ለተሰጠ የብድር ገንዘብ አመላለስ በመያዣ የተያዘ በኪሣራ የፈረሰ ማህበር (ድርጅት) ንብረት በሀራጁ ጨረታ የተሸጠ በመሆኑ ሽያጩ ሊፈርስ ይገባል በሚል የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ እና ፍ/ቤቶችም ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ያልተሰጣቸው ስለመሆኑ፣  በመያዣ የተያዘውን ንብረት በባንኩ በሀራጅ የተሸጠ በመሆኑ በባለዕዳው በኩል ቢሸጥ የተሻለ ዋጋ ያስገኝ ስለነበረ ሽያጩ ሊፈርስ ይገባል በማለት የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣  በህግ የተቋቋመ ባንክ በብድር የሰጠው ገንዘብ በአዋጅ ቁ.97/90 እና 216/92 መሠረት አስቀድሞ ለብድሩ አመላለስ ዋስትና ይሆን ዘንድ ከያዛቸው መያዣዎች መካከል አንዱን በመምረጥ በሐራጅ ሊሸጥ ይገባል፣ ለመሸጥ የተንቀሳቀሰበትን የመያዣ ንብረት ከመሸጥ ድርጊት ይታቀብ ይህም በፍ/ቤት ትዕዛዝ ይሰጥልን በሚል የሚቀርብ ክስ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑና በአሻሻጡ ሂደት ባንኩ ህግን ባለመከተል የፈፀመው ስህተት ቢኖርና በባለዕዳው ላይ ጉዳት ቢደርስ ግን ለዚህ ጉዳት ባንኩ ለባለዕዳው ካሣ የመክፈል ኃላፊነት የሚኖርበት ስለመሆኑ እና ፍ/ቤቶችም ሀራጁን ለማስቆም ስልጣን ያልተሰጣቸው ስለመሆኑ፣  የሰበር ችሎት የሚሰጠው አስገዳጅነት ያለው የህግ ትርጉም አንድ ክርክር የቀረበበት ጉዳይ (ድርጊት) ከተፈፀመ በኋላ ስለሆነ የተሰጠው የህግ ትርጉም በጉዳዩ ላይ ተፈፀሚነት የለውም በሚል የሚቀርብ ክርክር ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 394-449,224 አዋጅ ቁ.97/90 አንቀጽ 3,4 አዋጅ ቁ.216/92 አዋጅ ቁ.98/90 አዋጅ ቁ.2584

    ...

  • የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 5 ተፈፃሚነት በተከራካሪ ወገኖች መካከል በዋናው ጉዳይ ላይ ከላይ ወደ ታች በተዋቀሩት ፍ/ቤቶች ከተደረገ ክርክርና ከተሰጠ ውሣኔ ጋር በተገናኘ እንጂ በአፈፃፀም ከተሰጠ ትእዛዝ (ውሣኔ) ጋር በተያያዘ ተፈፃሚ ነው ሊባል የማይችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 5, 32

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሰው ለመንግስት ሊከፍል የሚገባውን ግብር ባለመክፈሉ በወንጀል ተግባር ሊጠየቅና ጥፋተኛ ተብሎ ሊቀጣ የሚችለው ግብሩን ላለመክፈል በማሰብና ግብር አስገቢው መ/ቤትም ንብረቶቹን በመያዝና በመሸጥ የግብር ገንዘቡን ገቢ እንዳያደርግ ለማድረግና ግብር የመክፈል ኃላፊነቱን ለማምለጥ ንብረቶቹን ለማሸሽ፣ የመሰወር ወይም ሌሎች ተገቢነት የሌላቸው ህገ ወጥ ተግባራትን በመፈፀም ግብርን ያልከፈለ መሆኑ ሲረጋገጥ እንጂ በሌሎች በህግ ተቀባይነት ባላቸው ምክንያቶች ግብሩን ለመክፈል ሳይችል የቀረ እንደሆነ ስላለመሆኑ፣  ማንኛውም ሰው በፍ/ብሔር ጉዳይ ያለበትን እዳ ለመክፈል ባለመቻሉ ምክንያት ብቻ በወንጀል ጉዳይ ጥፋተኛ ተብሎ ሊቀጣ የማይገባ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 285/94 አንቀጽ 49 አዋጅ ቁ. 286/94 አንቀጽ 96, 162 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 13(2) ደንብ ቁጥር 78/94 ICCPR- አንቀጽ 11

    Download Cassation Decision

  • የሥራ መሪ የሆነ ሠራተኛ ያለ አግባብ ከሥራ መሰናበቱ ተረጋግጦ ሲወሰንና የአሰሪው የመተዳደሪያ ደንብ የሚፈቅድለት ከሆነ በአዋጅ ቁ. 377/96 መሠረት ኪሣራ ታስቦ ሊከፈለው የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ.2574(2) አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 43(4) (ሀ

    Download Cassation Decision

  • የህብረት ሥራ ማህበራት ንብረት እንደ የአባለቱ የጋራ ሀብት (ንብረት) ተቆጥሮ ንብረቱን ለመሸጥ የሁሉም አባላት ስምምነት ያስፈልጋል ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣  የህብረት ሥራ ማህበራት አሰራር ጋር በተያያዘ ውሣኔ ለማሳለፍ የሚችለው የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 147/91 አንቀጽ 21, 18, 32, 19 ደንብ ቁጥር 106/96 አንቀጽ 20(2) 123

    Download Cassation Decision

  • የኑዛዜ ህጋዊነት ጋር በተያያዘ በተካሄደ ክርክር ተሣታፊ ሆኖ ተቀባይነት ያጣና ኑዛዜው በፍርድ ቤት የፀደቀበት ሰው በሌላ ጊዜ የኑዛዜውን ህጋዊነት አስመልክቶ በመቃወሚያነት የሚያቀርበው ክርክር ወይም አዲስ ክስ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣  የይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በቀረበለት ጉዳይ ላይ ዳኝነት መስጠት የሚገባው በስርዓቱ መሠረት የቀረበለትን የይግባኝ አቤቱታ መሠረት በማድረግ እንጂ ቀድሞ ስልጣን ባለው ፍ/ቤት የተሰጠ ውሣኔ ተገቢ አልነበረም በሚል ምክንያት ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 5,212 የፍ/ብ/ህ/ቁ. 881

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሠው በአንድ ወንጀል ድርጊት ክስ ቀርቦበት የመጨረሻ የሆነ ውሣኔ ተሰጥቷል በማለት በድጋሚ ልከሰስ አይገባም በሚል የሚያቀርበው ክርክር ከዚህ ቀደም ተጣርቶ ክስ የቀረበበትና የመጨረሻ ውሣኔ የተሰጠበት የወንጀል ድርጊትን በድጋሚ (ለሁለተኛ ጊዜ) ክስ ቀርቦበታል ከተባለው የወንጀል ድርጊት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለመሆኑ ተገናዝቦ ሊታይ የሚገባው ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 2(5), 678, 696(ሐ) እና 378 ህገ መንግስት አንቀጽ 23

    Download Cassation Decision