Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • አንድን ጉዳይ አስመልክቶ በፍርድ ሊወሰን የሚገባው እስከሆነና ጉዳዩን ለማየት በህግ በግልጽ የዳኝነት ስልጣን የተሰጠው ሌላ አካል እስከሌለ ድረስ ጉዳዩ በቀጥታ በፍ/ቤት ቀርቦ ሊስተናገድና ውሣኔ ሊሰጥበት የሚችልና የሚገባ ስለመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 37(1), 79(1) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 4

    Download Cassation Decision

  • የሁከት ይወገድልኝ ክስ ለማቅረብ የሚቻለው አቤቱታ አቅራቢው ለክርክሩ መነሻ በሆነው ነገር በቀጥታ ወይም በጥበቃ ሥር የሆነ ይዞታ ሲኖረው ስለመሆኑ፣  የይዞታ ክስ የሚቀርበው ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ንብረት በወቅቱ ለመያዝ ምንም አይነት መብት በሌለው ሰው ላይ ስለመሆኑ፣  የሁከት ይወገድልኝ ክስ የሚያቀርብ ሰው ንብረቱ በይዞታው ሥር የነበረና የሁከት ድርጊት ፈፃሚዉ የኃይል ተግባር በመጠቀም ወይም በሚስጥር ንብረቱን የወሰደበት መሆኑን ማስረዳት ያለበት ስለመሆኑ፣ የሁከት ተግባር ተፈጥሯል ለማለት ባለይዞታ የሆነው ሰው በይዞታው ሥር በሚገኘው ንብረት እንዳይገለገልበት ሌላ ሰው ጣልቃ ገብቶበት መሰናክል ወይም ረብሻ የፈጠረበት ስለመሆኑ መረጋገጥ ያለበት ስለመሆኑ፣  በህግ አግባብ በተደረገ የኪራይ ውል መነሻነት ይዞታን በእጁ ያደረገ ሰው (ተከራይ) ላይ አከራይ የሚያቀርበው የሁከት ይወገድልኝ ክስ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣

    Download Cassation Decision

  • የውጭ ምንዛሬ ከአገር ውስጥ ወደ ውጭ አገር ያለህጋዊ እውቅናና ፈቃድ ማስወጣት የወንጀል ኃላፊነትን የሚያስከትል ስለመሆኑ፣  የወንጀል ድርጊትን የፈፀምኩት ባለማወቅ ነው በሚል የሚቀርብ ክርክር ተቀባይነት የሌለውና ህግን አለማወቅ ይቅርታ የማያሰጥ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 622/2001 አንቀጽ 99 አዋጅ ቁ. 591/2000 አንቀጽ 20(3) የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 22(1) የወንጀል ህግ አንቀጽ 2(2),25,23(2),81(1)(3)

    Download Cassation Decision

  • አንድ የመንግስት ሠራተኛ መ/ቤቱን በመወከል ተቋሙ ከ3ኛ ወገን ጋር ካለው አለመግባባት ጋር በተገናኘ በግልግል ዳኝነት ጉባኤ አባልነት በዳኝነት ተሰይሞ ለጉባኤው የሚከፈለውን አበል ክፍያ መወሰኑ የዲሲፕሊን ጥፋት ፈጽሟል ሊያስብለው የሚችል ስላለመሆኑ፣  በግልግል ዳኝነት ጉባኤ ዳኝነት የተሰየመ ዳኛ በህግ ስላለበት ኃላፊነት፣  የግልግል ዳኛ ሆኖ የተሰየመ ሰው በግልግል ዳኝነቱ የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ ካልተወጣ በወንጀል ተጠያቂነት የሚኖርበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 351(2)(መ), 317, 318(መ) የወንጀል ህግ አንቀጽ 399 የአ.አ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አዋጅ ቁ. 6/2000 አንቀጽ 31

    Download Cassation Decision

  •  አንድ ሠራተኛ በሥራ ላይ እያለ የደረሰበትን የአካል ጉዳት በተመለከተ የጉዳት ካሣ ክፍያ እንዲከፈለው ለመጠየቅ የሚችለው በአማራጭ አንድም በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጁ መሠረት አሰሪውን ያለጥፋት በሥራ ክርክር ችሎት ከሶ በመጠየቅ ወይም የአሰሪውን ጥፋት መነሻ በማድረግ የጉዳት ካሣ ክፍያ ከውል ውጪ ኃላፊነትን የተመለከቱ ድንጋጌዎችን መሠረት በማድረግ በፍ/ሔር ችሎት በአሠሪው ላይ ክስ ለማቅረብ የሚችል ስለመሆኑ፣  በሥራ ላይ ጉዳት የደረሰበት ሠራተኛ የጉዳት ካሣን ለመጠየቅ በህጉ የተመለከቱትን መብቶች በአግባቡና በትክክል ተገንዝቦ እንደ ጉዳቱ ሁኔታ፣ አይነትና አግባብነት በተሻለ ሁኔታ የሚጠቅመውን የመብት አድማስ አውቆ በመለየት ተገቢው መብቱ ከመነጨበት የህግ አግባብ አንፃር ክሱን ሊያቀርብ የሚገባ ስለመሆኑ፣  የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.5 ድንጋጌ ይዘት አድማሱ በግልጽ በተወሰኑ ጭብጦች ላይ ብቻ ሣይሆን በተከራካሪ ወገኖች ቢነሱ ኖሮ ሊወሰኑ ይችሉ የነበሩ ጭብጦችን ጭምር የሚያካትት ስለመሆኑ፣

    Download Cassation Decision

  • ከሥራ ቅጥር ግንኙነት ጋር በተገናኘ አንድ ሥራ ""ቀጣይነት ያለው"" ነው ለማለት ስለሚቻልበት አግባብ፣  አንድ ሥራ በባህሪው ""ቀጣይነት ያለው"" ነው ለማለት ስራው ረዘም ላለ ጊዜ መስራቱን ብቻ ሣይሆን የሥራው ባህሪ ከአሠሪው ድርጅት (ተቋም) አይነተኛ ሥራ ጋር የሚሄድና በመደበኛነት የሚከናወን መሆኑን ጭምር ማረጋገጥ የሚያስፈልግ ስለመሆኑ፣

    Download Cassation Decision

  • አንድ ውል የአስተዳዳር ውል ነው ለማለት በህግ ወይም በተዋዋይ ወገኖች ግልጽ በሆነ ቃል የአስተዳደር መ/ቤት ውል ነው የተባለ እንደሆነ ወይም ደግሞ ተዋዋዮቹ ውል ያደረጉበት ጉዳይ ከህዝብ አገልግሎት ሥራ ጋር ተያያዥና ለሥራ ውሉ አፈፃፀም የአስተዳዳር አካልን (ፍ/ቤትን) ተካፋይነት ያለማቋረጥ የሚጠይቅ መሆኑን እንዲሁም በአጠቃላይ የውሉን አይነትና ባህሪ፣ የውለታውን አይነተኛ ጉዳይ ብሎም የተዋዋዮችን ማንነት መመልከት የሚያስፈልግ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.3132 አዋጅ ቁ. 361/95 አንቀጽ 41(1)(መ)

    Download Cassation Decision

  • አንድ የንግድ ማህበር (ድርጅት) የሚጨበጥና የማይጨበጥ እንዲሁም የሚንቀሣቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረት መብቶች ምን ምን እንደሆኑ በማህበሩ የመመስረቻ ጽሁፍና መተዳደሪያ ደንብ የሚወሰን ስለመሆኑ  አንድ የንግድ ማህበር (ድርጅት) ሥራውን የሚያከናውንበት የንግድ ቦታ ኪራይ መብት የማህበሩ ህልውና ጋር የሚያያዝ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣  የንግድ ድርጅቱ የፈረሰ ቢሆንም የንግድ ሥራውን ሲያከናውንበት የነበረውን ቦታ በሌላ ጉዳይ በፍርድ እንዲለቅ በተወሰነ ጊዜ የማህበሩ ሒሳብ ተጣርቶ አለመጠናቀቅ ቦታውን ላለማስለቀቅ ምክንያት ሊሆን የማይችል ስለመሆኑ፣

    Download Cassation Decision

  • በአንድ ውል የተመለከተን እዳ ለማረጋገጥ ሲባል አዲስ ሰነድ በተዋዋይ ወገኖች የማደራጀት ተግባር የውል መተካት አድራጐት ነው ለማለት የሚቻለው በሁለተኛው ውል በግልጽ የተመለከተ እንደሆነ ስለመሆኑ፣  በባህር ላይ የሚደረግ የማጓጓዣ ውልን አስመልክቶ አጓዡ ለውሉ ምክንያት የሆነው እቃ (ንብረት) ጋር በተያያዘ የሚያቀርበው አቤቱታ ዕቃውን ከተረከበበት ቀን አንስቶ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በስተቀር በይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ፣ የባህር ህግ ቁ.146,203 የፍ/ብ/ህ/ቁ.1826,1828,1829(ሀ)

    Download Cassation Decision

  • ተዋዋይ የሆኑ ወገኖች በመካከላቸው የሚነሣን አለመግባባት (ክርክር) በግልግል ዳኝነት እንዲያይ በሚል በውሉ የተሰየመ አካል በከሰመ ጊዜ ተዋዋዮች በጋራ ስምምነት ጉዳያቸውን በግልግል ዳኝነት የሚያይ አዲስ አካል ለመሰየም ከሚችሉ በቀር አስቀድሞ የተሰየመው አካል በመክሰሙ ምክንያት ፍ/ቤት ጉዳዩን በግልግል ለማየት የሚችል አካል ለመሰየም ስልጣን የሌለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.3336(1),3328(2),3337,3331,3325-3344,3329

    Download Cassation Decision

  • አንድ መዝገብ ላይ የተከሰሱ ሰዎች የኃላፊነት ምንጩ ከተለያየ የህግ ማዕቀፍ (ክፍል) በሆነ ጊዜ አንደኛው ወገን የተነሣው የይርጋ ክርክር በሌላኛው ወገን እንደተነሣ የማይቆጠር ስለመሆኑ፣  በአንድ ክስ (መዝገብ) ተጣምረው በአንድነት እና በነጠላ ኃላፊነት አለባችሁ ተብለው ከተከሰሱ ወገኖች መካከል አንደኛው ወገን የሚያነሣው የይርጋ መቃወሚያ ያለቅድመ ሁኔታ በሌላኛው ተጣምሮ የተከሰሰው ወገን ላይ ተፈፃሚነት አለው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣  በፍ/ብሔር ጉዳይ የአንድነትና የነጣላ ኃላፊነት ከተለያዩ የህግ ክፍሎች እና ከተለያዩ ምክንያቶች ሊመነጭ የሚችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1852 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.244(3),36

    Download Cassation Decision

  • ከሟች በስጦታ ወይም በኑዛዜ የተሰጠን ንብረት ወደ ውርስ መልሶ ማግባት (Collation) ስለሚከናወንበት ሥርዓት፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1065-1078

    Download Cassation Decision

  • ከጡረታ መብት አበል ተጠቃሚነት ጋር በተገናኘ የእድሜ አቆጣጠርና ውጤቱን በተመለከተ የሚቀርብ አቤቱታን አይቶ ለመወሰን ስልጣን ያለው የማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ተቋም ስለመሆኑና በውሣኔው ቅሬታ ያለው ወገን ለኤጀንሲው ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የይግባኝ አቤቱታ ለማቅረብ መብት ያለው ስለመሆኑ፣  በኤጀንሲው ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የሚሰጥ ውሣኔ በፍሬ ነገር ደረጃ የመጨረሻ ስለመሆኑና በውሣኔው ላይ መሠረታዊ የህግ ስህተት አለው በማለት አቤቱታ ያለው ሠራተኛ ቅሬታውን ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የማቅረብ መብት ያለው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 714/2003 አንቀጽ 4(1),54(3),56(4) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 343, 9, 231

    Download Cassation Decision

  • የመሬት አስተዳዳር ጽ/ቤት ቀድሞ የተሰጠን የቤትና ቦታ ካርታና ፕላን ጠፍቷል በሚል ሲጠየቅ በምትኩ ሌላ ሊሠጥ የሚገባው በ3ኛ ወገኖች ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ለማስወገድ በቅድሚያ ጠያቂው በቂ ዋስትና እንዲሰጥ በማድረግ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1197(2)

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሰው የሌላ ሰው ንብረት ይዞ ሲጠቀም ከቆየና ንብረቱን በሚጠቀምበት ጊዜ ንብረቱን ከጥፋት ወይም ከብልሽት ለማዳን ሲል ተገቢውን ወጪ ያወጣ እንደሆነ ይኸው ወጪ በህጋዊ ባለሀብቱ እንዲተካለት ለመጠየቅ የሚችለው ወጪው የግድ አስፈላጊ ከሆነና በቅን ልቦና የተደረገ መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ ስለመሆኑ፣  ወጪው በክፉ ልቦና የተደረገ ስለመሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ ግን እቃውን (ንብረቱን) እንዲመልሰ የተደረገው ሰው እንዲተካለት የጠየቀውን ወጪ መጠን ዳኞች ሊቀንሱት ወይም ጭራሹንም ሊያስቀሩት የሚችሉ ስለመሆኑ፣  በንብረቱ (እቃው) ላይ የተደረገው ወጪ «በክፉ ልቦና የተደረገ ነው» የሚባለው ወጪው በተደረገበት ጊዜ (ወቅት) ወጪው እንዲተካለት የሚጠይቀው ሰው ንብረቱን (እቃውን) ለባለቤቱ ለመመለስ ግዴታ ያለበት መሆኑን ያወቅ እንደነበር ወይም ማወቅ ይገባው የነበረና ርትዕም ሲያስገድድ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ 2172(1),2171(1),2168,2169

    Download Cassation Decision

  • አስቀድሞ በተደረገ የኪራይ ውል መነሻነት አንድን የአከራይ ንብረት ይዞ ሲጠቀም የቆየ ተከራይ የኪራይ ውል ግዜው ካለቀበት ጊዜ ጀምሮ አከራዩ የኪራዩን ዋጋ በመጨመር አዲስ የኪራይ ዋጋ እንዲከፈል ገልፆ እያለ ተከራዩ በቀረበው አዲስ የኪራይ ዋጋ ሳይስማማ ወይም እየተቃወመ በንብረቱ መገልገሉን በቀጠለ ጊዜ ተከራይ ለአከራዩ ሊከፍለው የሚገባውን የኪራይ ዋጋ ለመወሰን የሚቻልበት አግባብ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2950(1) (2), 1687

    Download Cassation Decision

  • የአንድ ደርጊት ወይም ግድፈት ወንጀልነት በህግ በግልጽ ተደንግጐ በማይገኝበት ሁኔታ የድርጊቱን ወይም የግድፈቱን ፈፃሚ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ የማይቻል ስለመሆኑ፣  በወንጀል ጉዳይ የሚቀርብ ክስ ስለ ድርጊቱና አፈፃፀሙ የሚሰጠው መግለጫ ድርጊቱን ወንጀል ከሚያደርገው ህግ አነጋገር በጣም የተቀራረበ መሆን የሚገባው ስለመሆኑ፣  በንግድ ሥራ ለተሰማሩ ወይም ሌሎች ሰዎች በግለሰብ ደረጃ መጠኑ በርካታ የሆነ ገንዘብን በተደጋጋሚ በብድር የመስጠት ተግባር በህግ የተከለከለ ወይም በወንጀል የሚያስቀጣ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 2, 23(2), 3, 61 የወ/መ/ህ/ሥሥ/ቁ. 112 አዋጅ ቁጥር 83/86 አንቀጽ 59(1), (ሸ), 2(ሀ),

    Download Cassation Decision

  • በባንክ በመያዣነት የተያዘ ተሽከርካሪ በሌላ በኩል የጉምሩክ ደንብ በመተላለፍ ወንጀል ባለቤቱ ጥፋተኛነቱ ተረጋግጦበት ተሽከርካሪውም በመንግስት እንዲወረስ ውሣኔ የተሰጠበት እንደሆነ በህግ ፊት ቅድሚያ ተሰጥቶት ሊፈፀም ስለሚገባው ጉዳይ  በባንክ በመያዣነት የተያዘ ተሽከርካሪ ከመያዣው በኋላ በኮንትሮባንድ ወንጀል ምክንያት ለመንግስት ውርስ እንዲሆን በፍ/ቤት የመጨረሻ ፍርድ ባረፈበት ጊዜ ባለመያዣው በተሽከርካሪው ላይ ያለው የቀዳሚነት መብት እንዲሁም የውርስ ትዕዛዙ (ውሣኔው) ተፈፃሚ ሊደረጉ ስለሚችልበት አግባብ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ 2828, 2857(1), 3059 አዋጅ ቁ. 97/90 አንቀጽ 3 የወንጀል ህግ አንቀጽ 98(1)

    Download Cassation Decision

  • አንድን ጉዳይ በተመለከተ ተከራካሪ ወገኖች በየበኩላቸው በተለያዩ ፍ/ቤቶች (ችሎቶች) አንድ አይነት ወይም ተመሳሳይ የሆኑ ክሶች ባቀረቡ ግዜ (የክርክሮቹ ደረጃ ምንም ይሁን ምን) ክሶቹ ተጣምረው ታይተው ሊወሠኑ የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 8(1),11,244, 245

    Download Cassation Decision

  • የጥብቅና ሙያ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃድ ያለው የህግ ባለሙያ በሙያው አገልግሎት ለመስጠት ከ3ኛ ወገን ጋር በሚያደርገው ውል የሚፈጠረው ግንኙነት በእውቀት ሥራ ውል ላይ የተመሠረተ እንጂ ሠራተኛውን እንደ የስራ መሪ ወይም ተቀጣሪ የማያስቆጥረው ስለመሆኑ፡ በአዋጅ ቁ.377/96 የማይገዛ ስለመሆኑ፣

    Download Cassation Decision